Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ በሚካሄደዉ የአፍሪካ ሕብረት ጉባዔ  ላይ 35 ፕሬዝዳንቶችና 4 ጠቅላይ ሚኒስትሮች  | Skyline media

በአዲስ አበባ በሚካሄደዉ የአፍሪካ ሕብረት ጉባዔ  ላይ 35 ፕሬዝዳንቶችና 4 ጠቅላይ ሚኒስትሮች  ይሳተፋሉ ተባለ፡፡

በአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ ላይ የ51 አገራት ልዑካን ቡድኖች   እንደሚሳተፉ ታዉቋል፡፡ በመድረኩ ላይ  35 ርዕሰ-ብሔሮች፣ አራት ጠቅላይ ሚኒስትሮች፣ 11 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ 13 ቀዳማዊ እመቤቶችና 10 የዓለም አቀፍ ድርጅት ኃላፊዎች ይታዳማሉ  ተብሏል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ ከነገ ጀምሮ 36ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ  መካሄድ ይጀምራል፡፡
ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ጉባኤው የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና ጉዳይ ላይ በስፋት እንደሚመክር ተናግረዋል።

በጉባኤው የፀጥታ ምክር ቤት ማሻሻያ እና የተለያዩ የሕግ ሰነዶች ይጸድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። ቀጣዩ የአፍሪካ ሕብረት ፕሬዝዳንት ኮሞሮስ ከሴኔጋል ትረከባለች ብለዋል።