Get Mystery Box with random crypto!

ማስታወቂያ በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፓሬሽን  የ14ኛውን | Skyline media

ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፓሬሽን  የ14ኛውን ዙር የ20/80 እና የ3ኛውን ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት  እድለኞችን ከጥር 1/2015 ዓ.ም ጀምሮ ውል ማዋዋል  መጀመሩ ይታወቃል።

በመሆኑም እስከአሁን በተቀመጠላቸው  የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ቅፅ 09ን የወሰዱ የቤት ባለ እድለኞች ቁጥር 23,373 ሰዎች ሲሆኑ ቅፅ 09 ከወሰዱት መካከል ከሚኖሩበት ቀበሌ የሚጠበቅባቸውን ያሟሉ እና የክፍያ ማዘዣ ቅፅ 03 በመውሰድ ውል የተዋዋሉ 7,855 ያህል ናቸው።

ይሁንና ውል ማዋዋል ከተጀመረ አንድ ወር ያለፈው ቢሆንም ቅፅ 09ን  በመውሰድ ከመኖሪያ ቀበሌያቸው አስፈላጊውን መረጃ በሟሟላት ወደ አንድ ማእከል መመለስ እና የክፍያ ማዘዣ ቅፅ 03 ወስደው መዋዋል ላይ መዘግየት ተስተውላል። 

ስለሆነም ተዋዋዮች የመዋዋያ ጊዜው እየተገባደደ ስለሆነ ከመኖሪያ ወረዳችሁ አስፈላጊውን መረጃ ፈጥናችሁ በማምጣት የክፍያ ማዘዣ ቅፅ 03ን እየወስዳችሁ ውል መዋዋል እንዳለባችሁ እያሳሰብን ወረዳዎችም ለባለጉዳዮቹ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ለስራው መቃናት ተገቢውን ትብብር እንድታደርጉ እናሳውቃለን።

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን