2021-03-09 10:06:31
ባሌ በ50 ብር ሸጠኝ !
ክፍል 9
.
.
.
ሚሚ ቂጦ ቤት አመት ከምናምን እንደሰራሁኝ ፣ አንድ ኤልያስ የሚባል በሱስ ሰውነቱ ያለቀ ፣
እንኳን ልብሱ ቀርቶ ቆዳው የሰፋው ፣ ረዥም ፣ ቀይ ፣ ቂጡ እንደጣውላ የተጠፈጠፈ ልጅ ቤቱ
ደንበኛ መሆን ጀመረ። ያንን ቤት ከረገጠበት ቀን አንስቶ በመጣ ቁጥር ከኔ ውጪ ሌላ ሴት ጋር
አይሄድም ነበረ። ሁልጊዜም ልክ ወደ ውስጥ ሲገባ በጥናንጥ አይኖቹ እኔን ከዛ ሁሉ ከሰው ጫካ
ውስጥ ፈልጎ ይመነጥረኝና ጥግ ላይ ተቀምጦ ሜንቱን አዝዞ በሲጋራው ጭስ እየተጫወተ ፍሪ
እስክሆን ድረስ ይጠብቀኝና ለአዳር በሀይሲ ታክሲው ወደ ቤቱ ይዞኝ ይሄዳል። ቤቱን ቤት ብዬ እኔ
ልጥራት እንጂ በጣም አስቂኝ ነበረች። መሬት ላይ ከተነጠፈችው አንሶላ ከምታህለው ፍራሽ ይልቅ
እንደ ተራራ የተከመሩት የሲጋራ ቡሾች ፍራሽ ይመስላሉ። ሌላ ዕቃ ከተባለ አንድ ሽንት ሽንት
የሚሸት ሰባራ ማስታጠቢያ አለ ፣ ከዛ ውጪ እንደ ቄጤማ የጫት ገረባ በብዛት ተጎዝጉዟል። የራሱ
ታክሲ ያለው ሰውዬ ቤቱ እንዲህ ይሆናል ብሎ ማንም አይገምትም። ባለ አንድ መኝታ
ኮንዶሚኒየም ቤት ውስጥ አንድ ፍራሽ ና ማስታጠቢያ ይዞ ቤት አለኝ ብሎ ማውራት ያሳፍር
ይሆናል። እውነታው ግን ይሄ ነበር።
እቤቱ ከወሰደኝ በኋላ እንደሌሎቹ ወንዶች አያመነጫጭቀኝም። ልክ እንደ አዲስ ሙሽራ
ይንከባከበኛል። ወደ ኦና ቤቱ እንደደረስን አንድ ስቲክ ጋንጃ ይስብና ሙድ ውስጥ ሆኖ ገላዬን እንደ
ህፃን ልጅ ያጥበኛል።። ወሲብ ማድረግ መፈለጌንና አለመፈለጌን በጨዋ ቋንቋ ይጠይቀኛል።
ጥቂት ቀናቶች እየፎገረኝ ከሆነ ብዬ 'ዛሬ ማረፍ ነው የምፈልገው' ስለው እንደ እህቱ እቅፍ
አድርጎኝ ይተኛል። Sex ያደረግን ቀንም ምኔን ምኔን እንደሚነካካኝ እሱ አንድዬ ይወቅለት በዘመኔ
ሁሉ ቀምሼው የማላውቀውን እርካታ ይሰጠኛል። ወንዴ ሴት ሆነህ ስትፈጠር ትልቁ ችግር ምን
መሰለህ? ያንተን እርካታ ጠብቆ የሚረካ ወንድ አለማግኘት ነው። አብዛኛው የሀበሻ ወንድ ገጣጣ
ሆዱን አንከርፍፎ ሴቷ ላይ ከላይ ሆኖ ያለከልክና ገና እሷ መጋል ስትጀምር እሱ ቀድሞ ጨርሶ
'እንዴት ነበር?' እንኳን ብሎ ሳይጠይቃት ጀርባውን ሰጥቷት ያንኮራፋል።አቤት ይሄንን ስቃይ ሴት
ሆነህ ካልቀመስከው በወሬ ብቻ ለማስረዳት በጣም ከባድ ነው። በዚህ የተነሳ በትዳራቸው ላይ
በግልፅ የሚወያዩ ጥቂት የሀበሻ ሴቶች ብቻ ናቸው ከወሲብ ሙሉ በሙሉ እርካታን የሚያገኙት ፤
ሌሎቻችን የወንዶች ስሜታቸውን ማስታገሻ ፓራሲታሞሎቻቸው ነን።
ኤልያስ ግን የሴት ልጅ የsex ባህሪን በደንብ የተረዳ ሰው ነው። እኔ በመርካቴ ነበር እሱ
እርካታውን የሚጎናፀፈው ፤ብታየው'ኮ ቆይ እንደውም ፎቶውን ላሳይህ( የሱ ፎቶዎች ብቻ ያለበትን
አልበም ሰጠችኝ) አየኸው አይደለ? የሆነ ሲምቢሮ አንጀት የራቀው ልጅ'ኮ ነው። ግን እዛ ነገር ላይ
ምንም ብቀጥን ጠጅ ነኝ እንደሚሉት ዓይነት ሰው ነው። ደግሞ'ኮ በጣም የሚገርመኝ ነገር
ማንኛዋንም ሴት ማርካት ይቻል ይሆናል ፣ ግን በቀን ከአስሩ ወንድ ጋር የምጋደመውን እኔን
ሸሌዋን ማርካት ከባድ ነው ፤ ምክንያቱም ወንድ ልጅ ማለት ለኔ በብልቱ የሚያስብ ዋሌት ብቻ
ነው። እኔ ብሩን እንጂ ሌላ ነገሩን ፈልጌ አላውቅም። እሱ ግን አሸነፈኝ። ይቺን ዓለም እዛ አትክልት
ተራ ገንዳ ስር ተጥዬ ከተቀላቀልኩበት ዕለት አንስቶ ማንም ሰጥቶኝ የማያውቀውን እውነተኛ ፍቅር
ሰጠኝ።
እንደምታየኝ ከሆነ ቆንጆ አይደለሁም። ፉንጋ ከመባል ለጥቂት የተረፈ መልክ ነው ያለኝ ፣ ትንሽ
ሰውነቴ ሞላ ያለ ስለሆነና በጭፈራ ቤት መብራት ሁሏም ሴት ቆንጆ ስለሆነች ያኔ አምሬው ይሆን?
ብዬ ቀን ቀን የሚይዘው ታክሲ ውስጥ ጋቢና አብሬው ተቀምጬ መዋል ጀመርኩ። እሱ
እንደጠበኩት አመሉ እንደቂጣ ሊገለባበጥ አልቻለም። አንዴ ታዲያ እሱ ቤት እየቃምን ለምን
እንዲህ እንደሚንሰፈሰፍልኝ ጠየኩት ያው የሀበሻ ወንዶች ስትባሉ ስትጠጡና ስትቅሙ ፈላስፋ
ፈላስፋ ያጫውታችሁ የለ? እንዲህ አለኝ፡፡ "ሰውን ለመጥላት እንጂ ለመውደድ ምን ምክንያት
ያስፈልገዋል? ክርስቶስ ዓለምን እንዲህ እንደወደድኳት እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ አይደል ያለው?
ስለዚህ አንቺን ለመውደዴ የምደረድረው ምንም ዓይነት ምክንያት የለኝም! እንዲሁ እወድሻለሁ!!
እንዲሁ አፈቅርሻለሁ!!! እንዲሁ የግሌ ጣኦት አድርጌሽ አመልክሻለሁ!!!! ምን መሰለሽ ሪችዬ እኔ
ሴት ብርቄ አይደለም ኢትዮጵያ ውስጥ የታክሲ ሹፌርና የቪዲዮ ቤት ባለቤት መሆን ትርፍሽ
የሚሆነው እውነቱን ንገረኝ ካልሽኝ እ*ስ ብቻ ነው። በዚህ የተነሳ ብዙ ሴቶችን አውጥቼያለሁ።
እነርሱ ግን በልቤ ውስጥ ያንቺን የሩብ ሩብ ቦታ ያህል አላገኙም። ሁሉም የስሜቴን ውጥረት
ማስተንፈሻ ተራ ቀዳዳዎች ብቻ ናቸው። አንቺ ግን ከነዛ ትለይብኛለሽ። በምን ብለሽ ብትጠይቂኝ
መልስ ላልሰጥሽ እችል ይሆናል ፣ ግን በቃ ለኔ አንደኛዬ ነሽ" አለኝ። ከልምዴ በመነሳት የወንዶችን
ስሜት መረዳት አይከብደኝም። ወንድን ልጅ ዓይኖቹን ሳላይ ማጅራቱን ብቻ ተመልክቼ
እንደሚፎግረኝና እንደማይፎግረኝ በቀላሉ መለየት እችላለሁ። ኤልያስ ከልቡ እንዳለኝ የነፍሴ ጆሮ
ሰምቶ አረጋግጦልኛል፡፡
እንዲህ እንዲያ እያልን ተላመድን ፣ በደንብ ተዋወቅን ፣ በፍቅር ወደ ላይ ፀባኦት ድረስ ከነፍን
ወደታችም እንጦሮጦስ ድረስ ዘልቀን በሲኦል የነበልባል ባህር ውስጥ ምስክር ሳያሻን እርስ
በርሳችን ተጠማምቀን ፣ ከሰይጣን የፊት ጥርስ የተሰራ ቀለበት አጥልቆልኝ ፣ እኔም አጥልቄለት
የቃልኪዳናችንን ሰማንያ በዲያቢሎስ ጭራ ማህተም አስመትተን አንድ አካል አንድ አምሳል ሆንን!
እሱ ጨርቁን ጥሎ ሊያብድልኝ ደረሰ ፣ እኔም ዓለም ሁሉ ከእሱ ውጪ እስኪያስጠላኝ ድረስ ልቡ
ላይ እንደተባይ ተጣበኩበት። የሱን ሀይሲ ታክሲ ቀን ቀን መፈረሺያ ማታ ማታ ቤርጎአችን
አደረግናት። እኔም አንገት ማስገቢያ ላመል ያህል አንድ ሁለት ሾርት ከሰራሁኝ ጉያው ስር
ለመሸጎጥ ፣ ጎረምሳ ጎረምሳ የሚል ለኔ ግን ከከርቤ በላይ ለአፍንጫዬ መልካም መዓዛ
የሚሆንልኝ ጠረኑን ለመታጠን ፣ ሌላ ቦታ ሰምቼያቸው ፈገግ እንኳን ያላስባሉኝን ቀልዶች እሱ
ሲያወራ ስሰማው ግን ጥርሶቼ እስኪረግፉ ድረስ ለመሳቅ ፣ ስንቱን ወንድ በብልጠቴ ገመድ ጠልፌ
የጣልኩት ሴትዮ ከርሱ ጋር ለመጃጃል ፣ ለመላፋት በክብር ለመሳም ወዳለበት ቦታ እየበረርኩ
እሄዳለሁ። ርግጠኛ ነኝ አስፋልት ላይ እንዲያ ስከንፍ ትራፊክ ቢያየኝ ቤልት አላሰርሽም ብሎ
ይቀጣኝ ነበር፡፡
ማታ ማታ በጋንጃ ጦዞ ሚሚ ቂጦ ቦት የኔ ሲምብሮ ሲመጣ ፣ እኔ ከማንም ሆዱም ማሰቢያውም
በአምቡላ ከተሞላ ለፍዳዳ ሰካራም ጋር ለገንዘብ ብዬ ሴትነቴን ሳራክስ እሱ ጥግ ላይ ተቀምጦ
በሲጋራው ጭስ እየተጫወተ ቅናቱን ውስጡ ቀብሮ ሜንት እየጠጣ ሲመለከተኝ ሳይ ሆዴ
ይንቦጫቦጭብኛል። ስፍስፍ እልለታለሁ። አፍቃሪው አንጀቴ ሌላ ወንድ እቅፍ ውስጥ ለመግባት
አቅሙ ይከዳዋል። እርሱን የሚሰማው የቅናት ቁስል አጥንቴ ድረስ ዘልቆ ይሰማኛል። ሲብስብኝ
'ሌላ ቦታ ጠጣ እዚህ አትምጣ' አልኩት።
"ሁለታችንም እንዲህ ከምንሰቃይ ለምን አታገቢኝም?" አለኝ።
ለዚህ ጥያቄው መልስ ለመስጠት ምላሴ አቅሙ ያጥረዋል። ብዙ የማውቃቸው ሸሌውች
አግብተው የተፈራረሙበት የስኪብርቶ ቀለም ሳይደርቅ ሲፋቱ ስላየሁ ትዳርን እፈራለሁ። ሙሉ
በሙሉ በቁጥጥሩ ስር ሲያደርገኝ አመሉ ቢቀየርስ? እያልኩ እሰጋለሁ። እንዲህ እንደጣኦቱ
የሚያመልከኝ ልክ እንደ ታክሲው ሁሉ የራሱ ንብረት ስላላደረገኝ ቢሆንስ? ራሔልን የግሌ
አደርጋታለሁ ብሎ ከራሱ ጋር እልህ ተያይዞ ቢሆንስ? እያልኩኝ
ሌሎች 'ቢሆንስ'
5.3K views07:06