Get Mystery Box with random crypto!

የፍቅር አለም LOVES WORLD

የቴሌግራም ቻናል አርማ silefikrr — የፍቅር አለም LOVES WORLD
የቴሌግራም ቻናል አርማ silefikrr — የፍቅር አለም LOVES WORLD
የሰርጥ አድራሻ: @silefikrr
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.98K
የሰርጥ መግለጫ

"💞ፍቅር💞
❤ገደብ የሚባል ነገር❤
አያውቅም አይቀበልም
መሰናክል እና አጥር ዘሎ ግንብ ደርምሶ
መድረስ ያለበት ቦታ ይደርሳል
ምክንያቱም💕ፍቅር💕እውነት ነው
እውነትም አሸናፊ ነውና::”
ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት
@manda0 @silefikirbot
Twitter account @mandelafikre
For stickers
https://t.me/addstickers/Mandua

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-02 06:45:50 እውነተኛ ፍቅር

እውነተኛ ፍቅር ፈጣሪ ከገነት በታች ለሰው ልጆች የሰጠው ስጦታ ነው•••

ለፍቅር ሁነኛ ማረጋገጫ #እምነት ነው•••

ማንም ሰው አይናችን ውስጥ ሊገባ ይችላል ፤ ነገር ግን ልባችን ውስጥ ዘልቆ የሚገባው አንድ ልዩ ሰው ነው•••

ራስህን እንድትሆን ለማይፈቅድልህ የፍቅር ወዳጅነት ራስን አሳልፈህ አትስጥ•••

በሌሎች የመፈቀርን ሀሰብ ከመውደድ በፊት ፤ መጀመሪያ ራስን መውደድን ተማር•••

በማይረባ ድንጋይ ጊዚያቸውን እንዳባከኑ ሲገባቸው በእጃቸው የነበረው እንቁ እንደነበር ይገነዘባሉ•••

አንድን ሰው ለመልኩ ብቻ አናፈቅረውም ፣ ለአለባበሱ ወይም ለምርጥ መኪናውም ልናፈቅረው አይገባም ፤ የምናፈቅረው እኛ ብቻ ልንሰማው የምንችለውን ዜማ ስለሚያቀነቅኑ ነው•••

ፍቅር ማለት ወሲብ አይደለም ፣ ወይም ጥሩ ምሽቶችን በጋራ ማሳለፍም አይደለም ፣ ወይም ተቃቅፎ መታየም ሳይሆን ማንም ሊያስደስታችሁ በማይችልበት መንገድ ደስታን ሊፈጥርላችሁ ከሚችል ሰው ጋር አብሮ መሆን ነው•••

ፍቅር እውር አይደለም ፣ ሌሎች በቀላሉ ሊያዩትን ያልቻሉትን ነገር እንዲያዩ የሚያስችል እንጂ•••

ፍቅር ይሻለናል

@silefikrr @manditua
32 views03:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 21:02:35 ማርፈድ ከትምህርት ይልቅ በህይወት ላይ ትልቅ ዋጋ ያስከፍላል
326 views18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 23:25:38 #የተሰጠንን_ብናውቅ_የጎደለን_የለም!

ሁለት የሚዋደዱ ጓደኛሞች ጉዞ ላይ ሳሉ አንደኛው ያማረ ቪላ ቤቶችን ያይና ለጓደኛው እንዲህ አለው።

«ፈጣሪ ይህን ሁሉ ሀብት ለእነዚህ ሰዎች ሲያድል እኛ የት ነበርን?»

ጓደኛውም አጠገቡ ነበረና ና ብሎ ወደ ሆስፒታል ይዞት ሔዶ እንዲህ አለው።

«ለእነዚህ ሰዎች ሁሉ ፈጣሪ በሽታን ሲያድል እኛ የት ነበርን?»

"የተሰጠንን ብናውቅ የጎደለን የለም!!
ምንግዜም ባለን ነገር እናመስግን።"
369 views20:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 09:00:22 የትኛው ንግግር ልብ ይሰብራል?

1, ሁለተኛ አጠገቤ ድርሽ እንዳትል
2, ከአንተ የተሻለ ሌላ ወድጃለሁ
3, አንተ ለኔ አትመጥንም
4, ላይህ አልፈልግም አስጠልተኸኛል
468 views06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 09:13:51 "ጨለማን መተቸት ብርሃን አያመጣም ክፋትን መኮነንም ደግነት አይሆንም ኋላቀርነትን ማጥላላት ሥልጣኔ አያመጣም ጦርነትን መፍራትም ሠላም አይሆንም እንዲሁም ረሃብን አለመፈለግ ጥጋብ አያመጣም ። ዕውቀትና በጎ አመለካክት ግን ማህበረሰብን መቀየር ይችላሉ ፡፡"

JOIN AND SHARE FOR MORE!! @silefikrr
1.2K views06:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 09:11:33 የማንነትህ መለኪያ ስኬት አይደለም

“በቅርጫ ኳስ ጨዋታ ዘመኔ 9 ሺህ ኳሶችን ሞክሬ ስቼአለሁ፡፡ 300 ውድድሮችን ተሸንፌአለሁ፡፡ ባስቆጥረው ቡድኔን ለዋንጫ የሚያበቃውን ኳስ እንድወረውር አምነው ሰጥተውኝ ስቼ አውቃለሁ፡፡ በሕይወቴ ደግሜና ደጋግሜ ወድቄአለሁ፡፡ ለዚህ ነው ስኬታማ የሆንኩት” - Michael Jordan

አብዛኛው ሰው ውስጡን የሚነዳው አንድ ጥማት አለው፡፡ ይህ ጥማት የተመሰከረለትና ጥንቅቅ ያለ ስኬታማ ሆኖ ለመታየት ያለው ጥማት ነው፡፡ “እንደዚህ ባደርግ፣ ይህኛውና ያኛው ነገር ቢኖረኝ፣ እዚያኛው ደረጃ ብደርስ ኖሮ … እረካና ሙሉ ስኬት ውስጥ እገባ ነበር” የሚል የውስጥ ጩኸት በብዙ ሰዎች ውስጥ ሲያስተጋባ ይሰማል፡፡ ስለዚህም፣ አንዳንድ ሰዎች ይህንን ጥማት ለማርካት ምንም ነገር ከማድረግና የትኛውንም ድንጋይ ከመፈንቀል አይመለሱም፡፡

የዚህ አመለካት ምንጩ፣ “ሙሉ ማንነት እንዲኖረኝ በኑሮዬ ስኬታማ መሆን አለብኝ” የሚለው አመለካከት ነው፡፡ የዚህ አመለካከትና የሕይወት ዘይቤ ውጤቱ ደግሞ “ስውር” ፍርሃት ነው፡፡ ሙሉ ማንነት እንዲኖረው ስኬታማ መሆን እንዳለበት ያመነ ሰው አለመሳካትን፣ ስህተትንና መውደቅን እጅግ የሚፈራ ሰው ነው፡፡ የሚሰራው ማንኛውም ስራ ስኬታማ የመሆኑና ያለመሆኑ ጉዳይ ከማንነቱ ዋጋ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው ባለማወቁ ምክንያት ለብዙ ስነ-ልቦናዊ ጥቃት ራሱን ያጋልጣል፡፡

የአንድ ሰው ማንነት የሚለካው በተሳካለትና ባልተሳካለት ነገር ከሆነ፣ ለዚያ ሰው ሩጫ ማቆሚያ፣ ለውድድሩም መጨረሻ የለውም፡፡ ይህ አይነቱ የሕይወት ዘይቤና አመለካከት የሚያስከትለው ዋነኛ መዘዝ የመውደቅ ወይም ስኬት የማጣት ፍርሃት ነው፡፡ ከዚህ የተዛባ የማንነት መመዘኛ ቀውስ ለመውጣት በስኬት ላይ ያለንን አመለካከት መቃኘት አስፈላጊ ነው፡፡

1. ስኬት ዘርፈ-ብዙ ነው
ለምሳሌ፣ አንድ ሰው በስራው ወይም በንግዱ አለም የተዋጣለት ሆኖና ያሰበው ደረጃ ደርሶ፣ በማሕበራዊውም ሆነ በቤተሰባዊው ኑሮው የተበላሸ ሁኔታ ውስጥ ራሱን ሊያገኘው ይችላል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ፣ አካላዊም ሆነ ስሜታዊ ጤንነቱን ችላ ብሎ እውቀትን ወይም ንብረት ሲሰበስብ የሚኖር ሰው በቀኑ መጨረሻ “ስኬታማ ነኝ” ብሎ እንዲናገር የሚያደርገው ነገር ምንድን ነው? ስለዚህም፣ ስኬት የብዙ መሰረታዊና አስፈላጊ እውነታዎች ጥርቅም ነች እንጂ አንድ ገጽታ ብቻ የላትም፡፡

2. ስኬት የሂደት ጉዳይ ነው
ስኬት የአንድ ጊዜ ክስተት ሳይሆን የሂደት ጉዳይ ነው፡፡ ስኬት፣ “አንድ ደረጃ ካልደረስኩ አልረጋጋም” ማለት ሳይሆን ጉዞውን በመጀመራችንና በሂደት ላይ በመሆናችን መርካትና መረጋጋት ማለት ነው፡፡ ዘርፈ-ብዙ የሆነው የስኬት ምስጢር ዘርፈ-ብዙ የሆነ ጥረትና ትጋት ይጠይቃል፡፡ ስኬታማ ሰው በሁሉም አቅጣጫ በአንድ ጊዜ ጥሩ ደረጃ ላይ የደረሰ ሰው ነው ብሎ ማሰብ ከእውነት እንድንርቅ ያደርገናል፡፡

3. ስኬት ተለዋዋጭ ነው
ትናንት ቀለል ያለው ሁኔታ ዛሬ ከበድ ሲል፣ ዛሬ የጨመረው ሁኔታ ነገ ሊቀንስ፣ ዛሬ የተነሳሳውና የጋለው ፍላጎት ነገ ቀዝቀዝ ሊል ይችላል፡፡ እንደ ሁኔታውና እንደ እለቱ ስሜት ጥረቱን የሚቀያይር ሰው እንደዚያው አይነት ውጤትን ያተርፋል፡፡ እንደ እለቱ ሁኔታና ስሜት ሳይሆን ከዓላማው አንጻር የሚሰራ ሰው ደግሞ ከዚያው አንጻር ስኬታማ ይሆናል፡፡ ይህ በፍጹም የማይለወጥ ሕግ ነው፡፡

JOIN AND SHARE FOR MORE!! @silefikrr
1.1K views06:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 10:43:04 ሆነ ማለት ነው።
ስለዚህ ወንድ ል

ጅ አይቸግረው! ወንድ ልጅ አይጣ!!
.
ከዛልህ እሱ አቅሙ ተሟጦ ምንም ማድረግ የማይችልበት ደረጃ ላይ ሲደርስ ፣ የሚላስ የሚቀመስ
ከቤት ሲጠፋ.......እኔም መቼም በቁማችን በረሀብ ስንምት ዝም ማለት የለብኝምና ውሻ ወደ
ትፋቱ ሲመለስ እንደሚያስጠላ ሁሉ......በእግርህ እየረገጥክ የወጣኸውን መሰላል በእጅህ
እየጨበጥክ መውረድ ደስ እንደማይል ሁሉ እኔም ወደመጀመሪያዬ ተመለስኩ።
እዛ ማሲንቆና ሴትነት የሚገዘገዝበት ፣ ከበሮ እንደ አውሊያ ዲቤ የሚደለቅበት ሚሚ ቂጦ ቤት
ተመልሼ ገባሁ"
'እንደገና!?!?!?'
"እና ምን አማራጭ አለኝ!"
'እሺ ከዛስ?'
:
:
:
ይቀጥላል

╔═══❖• •❖═══╗
@silefikrr
╚═══❖• •❖═══╝
4 any comment
@silefikirbot
❥❥________⚘_______❥❥
1.1K views07:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 10:41:41 ባሌ በ50 ብር ሸጠኝ !

ክፍል 13

ወንድማገኝ ለማ

=====================
"ያው አበሳዬን ሊያሳየኝ አይደል የፈጠረኝ?......ልጃችን እንደ ሌሎች ህፃናት እያለቀሰ ቤታችንን
ሊያደምቅልን አልቻለም። እስከ ስድስት ወር ድረስ እስኪ ትንሽ እንጠብቀው እየተባባልን ካሁን አሁን
ለውጡን ብንናፍቅም አቢ ግን ሲርበው እንኳን ሊጮህ አልቻለም። የሚያውቁን ሰዎች ኧረ እስኪ
ይሄን ልጅ ለሀኪም አሳዩት እያሉ ሲጨቀጭቁን በሰባተኛው ወር ይመስለኛል ጤና ጣቢያ
ወሰድነው። ዶክተሮቹም ህመሙ በደንብ ተለይቶ የሚታወቀው አንድ አመት ከሞላው በኋላ ነው ፣
ስላሉን አምስት የጭንቅ ወራትን አሳልፈን ዓመት ሲሞላው ይዘነው ሄድን።
.
ጤና ጣቢያው ከአቅሜ በላይ ነው ብሎ ለጳውሎስ ሪፈር ፃፈልን። ጳውሎስ ያሉ የአእምሮ
ስፔሻሊስት ሀኪሞች ከዚህ በፊት እንደነገርኩህ አቢ የአእምሮ ዝግመት ያለበትና የስሜት ህዋሳቶቹ
ምንም ነገር ሴንስ ማድረግ እንደማይችሉ አረዱን።
.
የሀኪሞቹን ንግግር ሲሰማ ሲምቢሮዬ የሚይዝ የሚጨብጠውን አጣ። በጣም ከመረበሹ የተነሳ
የመንግሥት ሀኪሞች ዝም ብለው ነፈዞች ናቸው ፣ ልጄን በገንዘቤ አድነዋለሁ ብሎ ያን ሰሞን
በቲቪ ይተዋወቅ የነበረ ትልቅ ጭራቅ ዶክተሮች የተሰባሰቡበት ሆስፒታል ይዞት ሄደ። እነዚህ የነፍስ
ደላላ የሆኑ ዶክተሮች ብዙም ሳያካብዱ 'የህክምናው ወጪ ውድ ነው እንጂ ይድናል' አሉን።
ሁለታችንም ሙሉ አፍሪካ የናንተ ግዛት ናት የተባልን ይመስል ፈነደቅን። የፈጠረኝ ጌታ ጥሎ
አይጥለኝም ብዬ የሞተ የተቀበረ ተስፋዬ ላይ እፍ እፍ ብዬ ነፍስ ዘራሁበት።
.
ሲምቢሮዬ በቅድሚያ ከዕለት ጉርሳችን ቀንሶ ያጠራቀማትን ሳንቲም አሟጦ ጨረሰ። ቀጥሎ
ከሚያውቁትና ከሚያውቃቸው ሰዎች ፊት እስኪነሱት ድረስ ተበደረ። በመጨረሻም አማራጭ
ሲያጣ ከልጄ አይበልጥብኝም ብሎ ለአቢ ማሳከሚያ የገቢ ምንጫችን የነበረውን ሀይሲ ታክሲውን
ሸጠው። ከመቶ ምናምን ሺህ ብር በላይ የሆነውን በህክምና ጨረሰው።
.
ያን ሰሞን በጭንቀት ብዛት ብቻውን ሳይቀር ማውራት ጀምሮ ስለነበር እንደገና ወደቀድሞ ህይወቱ
ቀስበቀስ ተመለሰ። በርግጥ ሱሱን አስትቼው እያለም የሀሽሹ ተፅዕኖ ከፍተኛ ስለነበር የባሰበት
የባሰበት ቀን እንዲጠቀም እፈቅድለት ነበር። አሁን ግን ከበፊቱ በባሰ ሁኔታ እንደ ሲጋራ ጋንጃውን
መጠብጠብ ጀመረ። ጨርቅ እስኪሆን ድረስ ደረቅ የሀበሻ አረቄ እየጠጣ ይመጣ ጀመር። እቤት
ሲገባ እንደሌላው ሞዛዛ ሰካራም አይለፈልፍ ፣ አይጮህ በቃ ዝም ብሎ ጃንኪናውን እየተወጋ ልክ
እንደ ሴት ማልቀስ ሆነ ስራው......ሳባብለው እኔን ላለማስጨነቅ ለጊዜው ዝም ይልና ሽንት ቤት
ገብቶ አሊያም እኛ ስንተኛ ለሊት ተነስቶ ማልቀስ የዘወትር ተግባሩ ዓይኖቹ ሟሙተው አብጠው
ሊጠፉ ደረሱ።
.
እኔ ከልጄ ህመም በላይ የሲምቢሮዬ እንዲህ መሆን ሠላሜን ነሳኝ። ሁለታችንም ስራ ስለማንሰራ
ታክሲው የተሸጠበት ብር ቀስበቀስ እየተመናመነ መጣ። ያ የሳቅና የጫጫታ ቤተ መንግሥት
የነበረው ቤታችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ፀጥታው የሚያስፈራ ኦና ሆነ! ልጄ ቢያመው እላዩ ላይ ሸንቶ
ዳይፐር ሳልቀይርለት ጭኑን ቢያቃጥለው አይለማ አይሰማ ፀጥ!!
.
እንደነገርኩህ እነዚህ አሳማ የሆኑ የሀገሬ ዶክተሮች ለገንዘባቸው ሲሉ ትንሽ ታገሱ እንትና የሚባል
ዶክተር ከውጭ አስመጥተናል እያሉ አራቆቱን። ሲምቢሮዬ ሙሉ በሙሉ ተበላሸብኝ። ያለመታከት
ይቅማል.......አረቄውን ይልፋል.....ደግሞ ይጦዝና ያገኘበት ያድራል። ቤቱ እሱ ሳይኖር የባሰ ባዶ
ስለሚሆን ከአራት ሰዓት በላይ ሲቆይብኝ ልፈልገው እወጣለሁ። የሆነ መንገድ ላይ ራሱን እስኪስት
ድረስ ሰክሮ ተዘርሮ እያለቀሰ አገኘዋለሁ። ሚዛኔን እስክስት ድረስ ደግፌው ወደቤት እገባለሁ። ብቻ
ከዚህ በኋላ ያለው ላይፋችን በህይወቴ ካሳለፍኳቸው ቀፋፊ ዘመናት ሁሉ በጣም አስከፊዎቹ
ናቸው። ለነገሩ ፃድቃኔ ደርሰን ተመልሰን አቢን እስክንወልድ ድረስ ባለችው ሁለት አመት የማትሞላ
ጊዜ ውስጥ ነው በዘመኔ ሁሉ በደስታ የኖርኩት ፣ ሌላው ሰላሳ ሶስት አመት ና ካሁን በኋላ ያለኝ
ህይወት ዝም ብሎ ዕድሜ እየቆጠሩ መባከን ነው።"
.
"እሺ ከዛ በኋላ ምንድነው የተፈጠረው?"
"ምን ያልተፈጠረ ነገር አለ ብለህ ነው ወንዴ.......ዓለም ክብ አይደለች? ይዘገያል እንጂ
ሁላችንም ወደ መጀመሪያችን መመለሳችን አይቀርም። ያ መጀመሪያችን ደግሞ መጨረሻችን
ነው።"
"ምን ለማለት ፈልገሽ ነው አልገባኝም"
"ቀላል ነገር'ኮ ነው የነገርኩህ እንዴት አይገባህም?.....እኛ ከአፈር ነው አይደል የተፈጠርነው? ያው
ከጊዜያት በኋላ ወደ መጀመሪያችን ተመልሰን አፈር እንሆናለን ፣ ስንወለድ ህፃን ሆነን ነው አይደል?
ከጊዜያት በኋላም ወደ መጀመሪያችን ተመልሰን ስናረጅ እንደገና ህፃን እንሆናለን። ይቺ ምድር
ከአለመኖር ወደ መኖር ስለመጣች ቀኗ ሲደርስ ወደ አለመኖርነቷ ትቀየራለች። እኔም ዕድለ ቢስ
ለደስታ ያልፈጠረኝ ሰው አይደለሁ? እግዜርም ሰይጣንም የተመቻቸ ህይወት ስኖር ይከፋቸዋል
መሰለኝ ተባብረው ወደ መጀመሪያዬ ወደ ጨለማው ህይወቴ መለሱኝ። እኔ'ኮ ግርም የሚለኝ
የሰይጣንስ እሺ ይሁን ፈጣሪ ግን የቁጣ በትሩን ይሄን ያህል እኔ ላይ ያሳረፈው ምን አድርጌው
ነው? በድዬውም ከሆነ ሌሎቹን እንደሚታገሰው እኔንም ለምን አይታገሰኝም! ገራሚ አምላክ እኮ
ነው!! በፈጠረን ፍጡሮቹ ላይ የሚያዳላ!!!"
'ኧረ ሪች እባክሽ እንደዚህ አትበይ'
"ለምንድነው የማልለው?! ከዚህ በላይ እንዳይቀጣኝ ፈርቼ ነው ዝም የምለው? አሁንም
እደግምልሀለሁ አምላክማ ያደላል። እስቲ ላንድ ምሽት ቺቺኒያ ብቻ ናና ተመልከት። የ15 የ16
ዓመት የሚሆኑ የሀብታም ልጆች አንድ ፐብ ለብቻቸው አዘግተው ሲጠጡ ያድራሉ ፣ እዛው በር ላይ
ደግሞ የነሱ እኩያ ቀኑ ጨልሞበት ቡትቶ ለብሶ ስቲኪኒና ሶፍት የበዛበት ትርፍራፊ ምግብ በልቶ
ራሱን ለመርሳት በማስቲሽ ሲጦዝ ታየዋለህ ፣ እና ይሄንን ዝም ብሎ የሚያየው ባያዳላ ነው ብለህ
ነው? ቀላል ያዳላል እንዴ! አንዱን ያለጥፋቱ ዕድሜውን ሙሉ ይቀጣዋል ሌላውን ግን በየሰከንዱ
ሀጢያት ሲሰራ እያየው በደስታ ያንበሸብሸዋል! ጓደኞቼን እንዲህ ስላቸው ሰማይ ቤት ይክሰናል
ይሉኛል። እዚህ ምድር ላይ ሲከፋኝ ላሽ ያለኝን ጌታ ጊዮርጊስን ነው የምልህ ነይ ገነት ግቢ ቢለኝ
አልፈልግም ነው የምለው! እዛም እየተሰቃየሁለት ደስ እንዲለው እፈልጋለሁ። ኤኒሀው እሱን
ተወውና ወደ ጨዋታችን እንመለስ...
.
ቀስበቀስ ቤታችን ውስጥ ወይዘሪት ድህነት ከንፈሯ ላይ ጉበት የመሰለ ሊፒስቲኳን
ለድፋ......ዓይኖቿን ስር ኩል ተቀብታ.....ፀጉሯን አቮካዶ ቅባት ተለቅልቃ.......የሆነ ሸፋፋ ሹል
ጫማ አድርጋ ነገሰችበት። የሲምቢሮዬ ኪስ ትናንት ማንም ሲቸግረው ብር እንደቆሎ
እንዳልዘገነበት ዛሬ ነፋስ የሚያወዛውዘው ሸረሪት ያደራበት ሆነ።
.
ወንድ ልጅ ከሚቸገር የፈለገ ሌላ ነገር ቢደርስበት ይሻለዋል። በተለይ ባል ሆኖ ሚስትና ልጆቹ የሱን
እጅ እንደሚጠብቁ ሲያውቅ ምን ያህል ግርማ ሞገሱ እንደሚገፈፍ በሲምቢሮዬ ስላየሁ ዛሬም
ወንዶችን እየጠላኋቸውም ቢሆን ተቸግረው እንዳያቸው ግን አልፈልግም። ወንዴ የርግማኖች ሁሉ
ርግማን አግኝቶ ማጣት ብቻ እንዳይመስልህ? የትዳር ራስ የሆነው ፣ የጎጆ መከበሪያ የሆነው ፣
የልጁና የሚስቱ ኩራት የሆነው ባል ቤሳቤስቲን ሲያጣ ያ ነው ታላቅ ርግማን! እኛ ሴቶችስ ያንንም
ያንንም አምታተን ገንዘብ እናመጣለን። እናንተ ወንዶች ግን ምንም ማድረግ ስለማትችሉ ቶሎ ነው
ተስፋ የምትቆርጡት። ወንድ ልጅ ተስፋ ቆረጠ ማለት ደግሞ የቤተሰቡ ማፈሪያ
1.0K views07:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-01 21:28:55 ባሌ በ50 ብር ሸጠኝ !

ክፍል 12

ወንድማገኝ ለማ
.
.
.
=====================
"አየህ ወንዴ....ሴት መሆን እንግዲህ ጥቅሙ እዚህ ጋር ነው። ምን መሰለህ? የወንድ ልጅ
ጉልበቱ ጡንቻው ሲሆን የኛ የሴቶች ደግሞ ዕንባችንና ብልጠታችን ነው። አንተ ምን ጠንካራ
ብትሆን አንዲት ሴት ሀይል ሳትጠቀም በዕንባዋ ብቻ ታሸንፈሀለች።
እኔም የሚያውቀው ቢሆንም እያለቀስኩ እስከዛሬ ድረስ በስቃይ እንደኖርኩ ፣ የሴተኛ አዳሪ ህይወት
እንዳንገሸገሸኝ ፣ ከሱ ውጪ የሌላ ወንድ እቅፍ ውስጥ መግባት እንደማልፈልግ ፣ ከውልደቴ
ጀምሮ የተናኩትን ሚስት ተብዬ በማህበረሰቡ ዘንድ መከበር እንደምፈልግ ዕያነባሁ ነገርኩት። ክብር
አሰጠኝ ብዬ እግሩ ስር ተደፍቼ ለመንኩት። በፍቅሬ ስለታወረ ስሜታዊ ሆኖ እሺ አለኝ።
.
አቤ..........................................................
............................................................
..............................ት የተደሰትኩት ደስታ!!!!!!!!!!!!
!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!! ነፍስሽ ከሲኦል ውስጥ ምህረት አግኝታ መንግስተ ሰማያት ልትገባ ነው
እንኳን ብባል እንደዛች ቀን የምደሰት አይመስለኝም! እንደ አይኔ ብሌን የምሳሳለትን አቢን የወለድኩ
ጊዜ እንኳን እንደዛች ቀን አልፈነጠዝኩም! ዓለም በቁጥጥሬ ውስጥ የሆነች መሰለኝ። እንዴት
አልደሰት ወንዴ? ከልጅነቴ ጀምሮ በስቃይ ኖሬ ዛሬ ክብር ሳገኝ ያልፈነጠዝኩ መቼ ልፈነጥዝ ነው?
ከሲምቢሮዬ አፍ የእሺታን ቃል ስሰማ ማመን አልቻልኩም። ቅዠት መሰለኝ። ወራቱ ሀምሌ መጨረሻ
አካባቢ ስለነበር
'ነገውኑ መሄድ አለብን' አልኩት በደስታ እንደ ቁንጫ እየዘለልኩ
"ወዴት?" አለኝ። እኔ ደስተኛ በመሆኔ መላ አካላቱ ጥርስ በጥርስ ሆኖ
'ፃድቃኔ ማርያም ሄደን ሀጢያታችንን ሁሉ ተናዘን ፍልሰታን እዛው ሱባኤ ይዘን አዲስ ህይወት
መጀመር አለብን' ፃድቃኔ ማርያም ከዛ በፊት ሄጄ አላውቅም። ነገር ግን ብዙ የማውቃቸው ሴቶች
እዛ ሄደው ሲመጡ ጥቂቶች ሴተኛ አዳሪነታቸዉን እርግፍ አድርገው ስለተዉ ነው ወደዛ እንሂድ
ያልኩት። ምንም ሳያንገራግር በሀሳቤ ተስማማ።
.
በበነጋታው አውቶቢስ ተራ ሄደን ሰላ ድንጋይ በሚሄድ ካቻማሌ ተሳፍረን ሸገር ለቀን ወጣን።
ዕቃችንን ተሸክመን የገዳሙ ማደሪያ ቦታ ጋር ስንደርስ ፍስለታን ሱባዔ ለመያዝ ከተለያዩ ቦታዎች
የመጡ ሰዎች የሸራ ቤት ሰርተውና የሸራ ቤት እየሰሩ አገኘን። እኛም እሱ የወንዶች ማደሪያ ጋር
እኔም የሴቶች ማደሪያ ጋር አጠናና ሸራ ገዝተን ጊዜያዊ ቤት አሰራን።
.
ፃድቃኔ ማርያም ሄደህ ካላወክ በስተቀር የቦታውን መንፈሳዊነትና ለነፍስህ የሚሰጣትን እርካታ
በቃላት ለመግለፅ መሞከር ከንቱ ልፋት ነው። ያኔ በቃ ጥሩ መንፈሳዊ ሆንን።
ጠዋት ተነስተን ፀበል እንጠመቃለን....ከሰዓት እናስቀድሳለን....ከቅዳሴ መልስ ቆሎ ና በሶአችንን
በቀን አንዴ ብቻ ቀምሰን ማታ ዋሻ ሄደን ፀሎት እናደርጋለን። ደግሞ በጣም የሚገርምህ ነገር
ወንዴ እዚህ በቀን ሶስቴ ና አራቴ እየበላህ ሲርብህ እዛ ግን እፍኝ ቆሎና አንድ ኩባያ በሶ በቀን
አንዴ ብቻ ቀምሰህ የረሀብ ስሜት በጭራሽ አይሰማህም። ከዛ ጥቂት ቆይተን ወደ ፀበሉ መሄጃ
ያለ ዋሻ ጋር የሚኖሩ አንድ ባህታዊ አግኝተን ሀጢያታችንን ተናዘን ንሰሀ ገብተን ፍፁም መንፈሳዊ
ሆንን። ሐምሌ መጨረሻ ላይ ሄደን ሐምሌ መጨረሻ ላይ ሄደን ፍልሰታ ሲያልቅ እንመጣለን ብለን
አስበን የነበርነው ሰዎች እስከ መስከረም 21 ቀን ድረስ እዚያው ነበርን።
.
ሁለታችንም ማርያምን ምስክር አድርገን ቃል ኪዳን ተገባባን ፣ አጫፋሪ ሳያስፈልገን ቀለበት
አሰርን። ሲምቢሮዬ አርግዞኝ አምጦኝ እንደገና የወለደኝ መሰለኝ። ዕድሜ ዘመኔን ያለጥፋቴ
የበደለኝን አምላኬን አልሜውም አስቤውም የማላውቀውን ትቢያ ከሆነው ከሴተኛ አዳሪ ህይወት
አውጥቶ ለትዳር ዙፋን ስላጨኝ የሚስትነትን ዘውድ እንድጭን ስላደረገኝ በመዝሙር
እያመሰገንኩት ወደ አዲስ አበባ መጣን።
.
አዲስ አበባ እንደደረስን ቤቴ ዝም ብለሽ አትገቢም ብሎ መጠነኛ ድግስ ደግሶ የኔና የሱ ጓደኞች
በተገኙበት የእወቁልን ግብዣ አደረግን። ሴተኛ አዳሪ የሆኑ ጓደኞቼ በማግባቴ በደስታ እያነቡ
መቋቋሚያ ብለው ሴትነታቸውን አርክሰው ከሸቀሉት ገንዘብ ላይ የአቅማቸውን አዋጥተው ሰጡኝ።
የሱም ሹፌርና ወያላ ጓደኞቹ እንዲሁም ትርፍ ሲጭን ቤልት ሳያስር ሲቀር የማይቀጡት ጉቦ
የሚሰጣቸው ሁለት ሀይገር ባስ ሀይገር ባስ የሚያካክሉ ትራፊኮችም የቻሉትን አንድ አንድ የቤት
ዕቃ ገዙልን። እኔ እየተፈጠረ ያለውን ነገር ማመን ስላልቻልኩ መጠጥ ሳልቀምስ እንደ ሰከረ ሰው
ጎረቤት እስኪገረም ድረስ እጮህ ነበር። ዕንባዬን መቅጣጠር አቅቶኝ አይኔን እስኪለበልበኝ ድረስ
አለቅሳለሁ.......ወንዴ ያኔ ያደረኩትን አብዛኛውን ነገር አላስታውሰውም።
.
ያው አዲስ ሙሽራ አይደለሁ? ለሊት ባሌ ከእንቅልፉ ሳይነሳ ቁርስ ሰርቼ ቀስቅሼ አበላዋለሁ። ያን
ሰሞን ደግሞ በነፃ ሲያገኘው ብርቅ ሆኖበት አብረን መተኛት አብዝተን ነበርና እንዲወፍርልኝ ብዬ
የቡላ ገንፎ.....አጥሚት...
..ቅቅል....ብቻ የተገኘውን ምግብ ባፍባፉ እጎሰጉስበት ነበር። እኔን ደስታ ሆዴን ሞልቶኝ ስለነበር
እሱን በማብላት እጠግብ ነበር። ከሰአትም ፒያሳ ታክሲ ተራ ድረስ ጎላ ብረት ድስት የሚያክል ምሳ
ዕቃ ተሸክሜ እሄድና አበላዋለሁ። ጓደኝቹ እስኪቀኑበት ድረስ ሙሉ በሙሉ ለወጥኩት። ስራ ለሊት
ስለሚወጣ 12:00 እንዲጨርስ አደርገውና ሲኒማ አምፒር ገብተን በግድ ሊያስቁን
የሚለማመጡን ተዋንዋያን የሚሰሩትን ፊልም አለማሳቁ እያሳቀን እናያለን....ሲኒማ ቤት መግባት
ሲሰለቸን ወይናችንን ገዝተን ግማሽ ኪሎ ስጋችንን ጠብሰን ቤታችን ውስጥ እየበላንና እየጠጣን
ጋቢያችንን ደረብ አድርገን ሶፋችን ላይ ተጋድመን ሮማንስ ፊልም እናያለን። ለመኖሪያችን
የሚቀርቡንን ቤተ ክርስቲያኖች የወር በአላቸው ሲሆን ጧፍ እያበራን ጉባኤ ላይ እንታደማለን።
ሳንቲም የሸቀለ ሰሞን እሁድን ከከተማ ወጥተን አየር ለውጠን እንመለሳለን። ከዚህ በላይ ምን
እፈልጋለሁ? አበድኩልህ!
.
የኔ ሲምቢሮም ሰውነቱ መለስ እያለ መጣ። ቤታችንን በሚያስፈልገን ዕቃ አሟላን። ከዛ ጭቃ
ህይወት አላቆ ይሄንን ክብር የሰጠንን አምላካችንን ጠዋት ማታ ያለመታከት ማመስገን ጀመርን።
ከዚህ በኋላ ልጅ መውለድ አለብን ተባባልን። አረገዝኩለት። አቤት እንክብካቤ! እንዴት አባቱ
አሞላቀቀኝ መሰለህ!?
ዘጠኝ ወር ሙሉ ቅብጥ ብዬ የእርግዝና ጊዜዬን ጨርሼ አቢን ወለድኩ። አቢ ሲወለድ ስራ መስራት
እስከማይችል ድረስ ቤቴ ቤቴ ማለት አበዛ። በብቸኝነት ገንዳ ላይ የተጣልኩት፣ የዝንብ ትራፊ እበላ
የነበርኩት ፣ የአባቴ መለመኛ ብቻ የነበርኩት ፣ ባመንኳት በመአዛ ለዛች ለደዘደዝ የተሸጥኩት እኔ
መከረኛዋ ራሔል ዓይኔን ባይኔ አየሁ።
"አድረግህልኛልና በቸርነትህ
አመሰግንሀለሁ እልል እልል
ለዓለም ለዓለም አማኑኤል
እገዛልሀለሁ መድሀኒዓለም" እያልኩ እኔና ሲምቢሮዬን ከሁለት ወደ ሶስት ያሸጋገረኝን ጌታዬን
አመሰገንኩት።
.
ይሄ የኔም የባሌም ደስታችን ግን ከስድስት ወር በላይ ሊቀጥል አልቻለም" አለችና ትንሽ አሰብ
አደረገች
'ለምን?' አልኳት
" ያው አበሳዬን ሊያሳየኝ አይደል የፈጠረኝ....
:
:
:
ይቀጥላል

╔═══❖• •❖═══╗
@silefikrr
╚═══❖• •❖═══╝
4 any comment @manditua
1.6K views18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-11 22:37:12 ባሌ በ50 ብር ሸጠኝ !

ክፍል 11



==========================
"አዎ ምን መሰለህ? የሱ ትልቁ ችግር.....እኔም እንዳላገባው ያስፈራኝ የነበረው ፣ ሲበዛ ለሱሱ
ሟች ነው። ምድር ላይ ሳይደነዝዝ መኖር አይችልም። ሱስ እየተጠቀመ ከሚደርስበት አካላዊና
አእምሮአዊ ጉዳት በላይ ሱሱን ቢያቆም የሚደርስበት ስቃይ ይበልጣል። የሌለበት የሱስ አይነት
አልነበረም። ጃንኪና ይወጋል(( የመርፌውን ሀሽሽ)).....በጋንጃ ይጦዛል.....በሲጋራ ጭስ ስሙን
መፃፍ እስኪችል ድረስ ቼን ስሞከር ነው....ኤልያስ ጥርሱ ይግላል እንጂ አይመረቅንም እስኪባል
ድረስ በርጫውን ያደቃል.....ጠርሙስ ውስጥ የተወለደ ይመስል ሀሞቱን እስኪተፋ ድረስ ሜንት
አረቄ ይጠጣል.......በርግጥ እኔም እሱ የሚጠቃመቸውን ማደንዘዣዎች በሙሉ እጠቀማለሁ። እኔ
ግን ሴት ነኝና ትዳር ውስጥ ከገባሁኝ የተከበረች ሚስት መሆን ስለምፈልግ ሱሶቼን በሙሉ
እተዋለሁ ብዬ ወስኜ ነበረ። እሱ ግን በተለይ ሳይጠጣና ሳይጦዝ መዋልና ማደር አይችልም። ይሄ
አመሉ አግብቼው አብሬው እንዳልኖር ያስፈራኝ ነበር።
.
ወንዴ ትዳር ማለት አፈቅርሀለሁ አፈቅርሻለሁ ፣ ያላንቺ አልኖርም ያላንተ መኖሬ ትርጉም የለውም
እየተባባልክ እንደፍቅረኝነት ዘመንህ ስለተፎጋገርክ ብቻ ጎጆ አይመሰረትም። ተጋባህ ማለት
የራስህን ግዛት ፣ የራስህን ትንሽዬ ሀገር መሰረትክ ማለት ነው። ባልየው የቤቱ ራስ ስለሆነ ጠቅላይ
ሚኒስተር ፣ የገቢ ምንጭ ስለሆነ ገንዘብ ሚኒስተር ፣ ሚስትና ልጆቹን ከአደጋ ስለሚከላከል
መከላከያ ሚኒስተር ይሆናል ፤ ሚስትየዋ ደግሞ ለልጆቿ ትምህርት ሚኒስተር ፣ ቤተሰቡ
ከህብረተሰቡ ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲኖረው ስለምታደርግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፣ ባሏና ልጆቿ
እንዳይራቡ ግብርና ሚኒስትር ትሆናለች። ይሄንን የሚያህል ትልቅ ተቋም ውስጥ ስለተፋቀርክ ብቻ
ዘው ብለህ አትገባም። የነገ ህይወትህ ላይ ዛሬ ቆም ብለህ የማያዳግም ውሳኔ መወሰን አለብህ።
.
እኔም ለብዙ ጊዜ የኤልያስን የእንጋባ ጥያቄ እየደጋገምኩ አሰብኩበት። ለራሴ እንዲህም
አልኩት......
'ትሰሚኛለሽ ሪች ተጋባችሁ ማለት አንቺ ሴተኛ አዳሪ እርግፍ አድርገሽ ታቆሚያለሽ ፣ ያ ማለት
በፓኪስታንኛ የቤቱ ኢኮኖሚካል ጥያቄ በሙሉ የሚሸፈነው እሱ በሚያገኘው ገቢ ይሆናል ማለት
ነው። በገንዘብ በኩል የራሱ ታክሲ ስላለው ፣ የሚኖርበት ኮንዶሚኒየም የግሉ ስለሆነ ስጋት
አይግባሽ። ያ ማለት ግን ምንም ችግር የለም ማለት አይደለም። እሱ ቢያንስ ቢያንስ በቀን ለሱሱ
ብቻ ከ300-400 ብር ድረስ ያጠፋል። ስለዚህ አብረሽው ለመኖር የምትፈልጊ ከሆነ ኤልያስን
ከሱሱ እንዲላቀቅ ማድረግ አለብሽ። አንድ ባል ሱሰኛ መሆን የሚገባው የሚስቱና የልጆቹ ብቻ
ነው።
.
ሴት ስትሆን ትልቁ ፀጋህ ፈጣሪ ሲፈጥርህ ብልጥ የሆነና ከብዙ አንግሎች አንፃር ማሰብ የሚችል
አእምሮ ይኖርሀል። እናም ኤልያስን አሁን ከሚያፈቅረኝ በላይ ከነፍሱ እንዲያመልከኝ አደረኩት።
እስኪገረም ድረስ እየተንከባከብኩት ካለኔ መተንፈስ እስከማይችል ድረስ ሁሉ ነገሩ ሆንኩለት።
ነፍሱ ከአምላኩ በላይ በኔ ቁጥጥር ስር ሆነች። አምላክ ለሙሴ ከሰጠው አስርቱ ትዕዛዛት በላይ ፣
ኢየሱስ በምድር ላይ ሳለ ከተናገራቸው ስድስቱ ቃላተ ወንጌላት ይበልጥ የኔን ቀጭን ትዕዛዝ
ያከብርና ይፈፅም ነበር። አምላካችሁን በቀን ውስጥ አንዴ ወይ ሁለቴ ልታስቡት አሊያም ከነጭራሹ
ትዝ ላይላችሁ ይችላል ፣ ስለኛ ግን ሳታስቡ መዋልና ማደር አትችሉም። በየሰአቱ በየደቂቃው
በየሰኮንዱ ሽርፍራፊ ሁሉ ስለሴት ልጅ ስለምታስቡ እናንተን በቁጥጥራችን ውስጥ ለማዋል ልክ
ክሬም ኬክ እንደመቁረስ ያህል ለኛ ቀላል ነው።
.
እዛች አንሶላ የምታህል ፍራሽ ላይ ጋደም ብለን እንዲህ አልኩት....
'የኔ ሲምብሮ'
"ወይዬ የኔ ጣኦት" አለኝ። በቃ የዛን ሰሞን በፍቅሬ ደንዝዞ ስለነበር ወሬው ሁሉ ልቦለዳዊ ነበር
የሚመስለው።
'ከኔ ጋር አብረህ መኖር ትፈልጋለህ አይደል?'
አብረን እንኑር ያልኩት ይመስል ከተጋደመበት ፍንጥር ብል ተነሳና እላዬ ላይ ወጥቶ ዓይን ዓይኔን
እያየኝ.......
"የኔ ጣኦት! እዚች ምድር ላይ ብቻ መሰለሽ እንዴ አብሬሽ መኖር የምፈልገው? ሞቼ ስጋዬ ምስጥ
ሆኖ እንኳን(( እዚች ጋር እኔ ጣልቃ ልግባማ....እኛ ከአፈር ከተሰራን ስንሞት ለምንድነው ምስጥ
የምንሆነው? ሰው ማለት በትናንሽ ምስጦች የተገነባ ፍጡር ነው እንዴ? ፈረንጆቹም ሲሞቱ እንደኛ
ምስጥ ይሆናሉ? ወይንስ ሀበሻ ብቻ ነው በህይወት እያለ ትልቅ ምስጥ ሲሞት ትናንሽ ምስጥ
የሚሆነው?))(ፍልስምና)
....በአጥንቴ ብቻ ቀርቼ የምፅአት ቀን ሲደርስ መለከት ሲነፋ......ምድር ከመኖር ወደ አለመኖርነት
ስትቀየር.....ሀጥያን በግራ ፃድቃን በቀኝ ሲቆሙ......ልክ ምግባራችን የተመዘገበበት መዝገብ
ከመገለጡ በፊት......ጌታን እኔ እንዲህ እለዋለሁ
'ይቅርታ.....ይቅርታ.....አንድ ጊዜ ለማውራት ቢፈቀድልኝ?' ጌታም ቀና ብሎ አጥንታም ነፍሴን
ያይና በዝምታው ተናገር ይለኛል።
'እኔ ከጣኦቴ ተለይቼ መንግስተ ሰማያት ከምገባ የእሳት ባህር ወዳለበት ገሀነም ብጣል ይሻለኛል!
ጌታ ሆይ እባክህ ስለ ጭንቅ አማላጇ ስለ እናትህ ብለህ ከራሔል አትለየኝ?' ብዬ አጥንታሙ ፊቴ
ላይ የአጥንት ዕንባ እያነባሁ ፊቱ ተደፍቼ ስለምነው የነገሩትን የማይረሳ የለመኑትን የማይነሳ የኔ
ጌታ.....እስከዛሬ ድረስ በሰው ልቦና ያልታሰበ አዲስ ዓለም ይፈጥርና እኔና አንቺን ብቻ
ወደተዘጋጀልን የክብር ስፍራ ይልከናል። እኔና አንቺም አዲሱ ሰማይ ቤታችን ላይ ሚጢጢ ሚጢጢ
ልጆች ወልደን በደስታ በተድላ እንኖራለን......እሜቴ ይሄን ያህልማ አይመሰጡ.....በሉ ተረቴን
መልሱ አፌን በከንፈርዎ ያብሱ!' ብሎ ያው እንደለመደው ብዙ ማውራት እየፈለኩኝ ከንፈሬን ትንፋሽ
እስኪያጥረኝ ድረስ መጠመጠኝና አይሆኑ አይሆኑ ቦታ ነካክቶኝ ቅንዝርዝ
.
ጥቂት ቆይቼ ዓይን ዓይኑን እያየሁት
'...የኔ ሲምቢሮ ዘላለም አብረኸኝ መኖር ከፈለክ ሱስህን በሙሉ እርግፍ አድርገህ መተው አለብህ'
ስለው ፊቱ ላይ የቅሬታ ስሜት አነበብኩ።
.
አውቃለሁ ያለሱሱ መኖር እንደማልችል! ይገባኛል ለዘመናት በብቸኝነቱ ዋሻው ውስጥ ተመሽጎ
ሲኖር ከሰዎች ይልቅ ሱሶቹ ቀድመው ደርሰውለት አጫዋች ጓደኛ ፣ ሀዘኑን መርሻ እንደሆኑት!!
አሁን ግን እኔ በህይወቱ ስለመጣሁ መደንዘዝ አያስፈልገውም። ሊያገባኝ ከፈለገ ለጎጆው ሲል
በተቃራኒው መንቃት አለበት። እሱ ካለሱሶቹ ከሚኖር እየተጎዳም ቢሆን እኔን ቢያጣ እንደሚመርጥ
ሳይመረኝ የምውጠው ሀቅ ነው።" አለችኝና ከተቀመጠችበት ተነስታ ከቁምሳጥኗ ውስጥ የሺሻ
ዕቃዋን አወጣች ፣ ስቶቭ ላይ ደቃቃ ከሰሎችን አቀጣጠለች ፣ ውሀውን ቀየረች ፣ ቡሬው ውስጥ
አዲስ መዋሰል ከትታ በአልሙኒየም ሸፈነችው ፣ የከሰል ፍሙን በመርፌ በሳሳችው አልሙኒየም
ላይ አድርጋ ሺሻዋን ማንደቅደቅ ጀመረች። ለኔም ቀዝቀዝ ያለ ቢራ ሰጠችኝ። የጉሮሮዬን ድርቀት
ጎንጨት ብዬ አለሰለስኩት። ጥቂት ፋታ ከወሰድን በኋላ.......
.
"እና ሱሱን እንዲያቆም አደረግሽው ወይስ አልሰማሽ አለ?" አልኳት በድጋሚ እንደ'ሷ ህይወት
የሚጎመዝዘውን ቢራ እየተጎነጨሁ..
"አየህ ወንዴ....ሴት መሆን እንግዲህ ጥቅሙ እዚህ ጋር ነው.......ምን መሰለህ...........
:
:
:
ይቀጥላል

╔═══❖• •❖═══╗
@silefikrr
╚═══❖• •❖═══╝
4 any comment
@manditua
❥❥____
1.6K views19:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ