Get Mystery Box with random crypto!

ባሌ በ50 ብር ሸጠኝ ! ክፍል 13 ወንድማገኝ ለማ ===================== ' | የፍቅር አለም LOVES WORLD

ባሌ በ50 ብር ሸጠኝ !

ክፍል 13

ወንድማገኝ ለማ

=====================
"ያው አበሳዬን ሊያሳየኝ አይደል የፈጠረኝ?......ልጃችን እንደ ሌሎች ህፃናት እያለቀሰ ቤታችንን
ሊያደምቅልን አልቻለም። እስከ ስድስት ወር ድረስ እስኪ ትንሽ እንጠብቀው እየተባባልን ካሁን አሁን
ለውጡን ብንናፍቅም አቢ ግን ሲርበው እንኳን ሊጮህ አልቻለም። የሚያውቁን ሰዎች ኧረ እስኪ
ይሄን ልጅ ለሀኪም አሳዩት እያሉ ሲጨቀጭቁን በሰባተኛው ወር ይመስለኛል ጤና ጣቢያ
ወሰድነው። ዶክተሮቹም ህመሙ በደንብ ተለይቶ የሚታወቀው አንድ አመት ከሞላው በኋላ ነው ፣
ስላሉን አምስት የጭንቅ ወራትን አሳልፈን ዓመት ሲሞላው ይዘነው ሄድን።
.
ጤና ጣቢያው ከአቅሜ በላይ ነው ብሎ ለጳውሎስ ሪፈር ፃፈልን። ጳውሎስ ያሉ የአእምሮ
ስፔሻሊስት ሀኪሞች ከዚህ በፊት እንደነገርኩህ አቢ የአእምሮ ዝግመት ያለበትና የስሜት ህዋሳቶቹ
ምንም ነገር ሴንስ ማድረግ እንደማይችሉ አረዱን።
.
የሀኪሞቹን ንግግር ሲሰማ ሲምቢሮዬ የሚይዝ የሚጨብጠውን አጣ። በጣም ከመረበሹ የተነሳ
የመንግሥት ሀኪሞች ዝም ብለው ነፈዞች ናቸው ፣ ልጄን በገንዘቤ አድነዋለሁ ብሎ ያን ሰሞን
በቲቪ ይተዋወቅ የነበረ ትልቅ ጭራቅ ዶክተሮች የተሰባሰቡበት ሆስፒታል ይዞት ሄደ። እነዚህ የነፍስ
ደላላ የሆኑ ዶክተሮች ብዙም ሳያካብዱ 'የህክምናው ወጪ ውድ ነው እንጂ ይድናል' አሉን።
ሁለታችንም ሙሉ አፍሪካ የናንተ ግዛት ናት የተባልን ይመስል ፈነደቅን። የፈጠረኝ ጌታ ጥሎ
አይጥለኝም ብዬ የሞተ የተቀበረ ተስፋዬ ላይ እፍ እፍ ብዬ ነፍስ ዘራሁበት።
.
ሲምቢሮዬ በቅድሚያ ከዕለት ጉርሳችን ቀንሶ ያጠራቀማትን ሳንቲም አሟጦ ጨረሰ። ቀጥሎ
ከሚያውቁትና ከሚያውቃቸው ሰዎች ፊት እስኪነሱት ድረስ ተበደረ። በመጨረሻም አማራጭ
ሲያጣ ከልጄ አይበልጥብኝም ብሎ ለአቢ ማሳከሚያ የገቢ ምንጫችን የነበረውን ሀይሲ ታክሲውን
ሸጠው። ከመቶ ምናምን ሺህ ብር በላይ የሆነውን በህክምና ጨረሰው።
.
ያን ሰሞን በጭንቀት ብዛት ብቻውን ሳይቀር ማውራት ጀምሮ ስለነበር እንደገና ወደቀድሞ ህይወቱ
ቀስበቀስ ተመለሰ። በርግጥ ሱሱን አስትቼው እያለም የሀሽሹ ተፅዕኖ ከፍተኛ ስለነበር የባሰበት
የባሰበት ቀን እንዲጠቀም እፈቅድለት ነበር። አሁን ግን ከበፊቱ በባሰ ሁኔታ እንደ ሲጋራ ጋንጃውን
መጠብጠብ ጀመረ። ጨርቅ እስኪሆን ድረስ ደረቅ የሀበሻ አረቄ እየጠጣ ይመጣ ጀመር። እቤት
ሲገባ እንደሌላው ሞዛዛ ሰካራም አይለፈልፍ ፣ አይጮህ በቃ ዝም ብሎ ጃንኪናውን እየተወጋ ልክ
እንደ ሴት ማልቀስ ሆነ ስራው......ሳባብለው እኔን ላለማስጨነቅ ለጊዜው ዝም ይልና ሽንት ቤት
ገብቶ አሊያም እኛ ስንተኛ ለሊት ተነስቶ ማልቀስ የዘወትር ተግባሩ ዓይኖቹ ሟሙተው አብጠው
ሊጠፉ ደረሱ።
.
እኔ ከልጄ ህመም በላይ የሲምቢሮዬ እንዲህ መሆን ሠላሜን ነሳኝ። ሁለታችንም ስራ ስለማንሰራ
ታክሲው የተሸጠበት ብር ቀስበቀስ እየተመናመነ መጣ። ያ የሳቅና የጫጫታ ቤተ መንግሥት
የነበረው ቤታችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ፀጥታው የሚያስፈራ ኦና ሆነ! ልጄ ቢያመው እላዩ ላይ ሸንቶ
ዳይፐር ሳልቀይርለት ጭኑን ቢያቃጥለው አይለማ አይሰማ ፀጥ!!
.
እንደነገርኩህ እነዚህ አሳማ የሆኑ የሀገሬ ዶክተሮች ለገንዘባቸው ሲሉ ትንሽ ታገሱ እንትና የሚባል
ዶክተር ከውጭ አስመጥተናል እያሉ አራቆቱን። ሲምቢሮዬ ሙሉ በሙሉ ተበላሸብኝ። ያለመታከት
ይቅማል.......አረቄውን ይልፋል.....ደግሞ ይጦዝና ያገኘበት ያድራል። ቤቱ እሱ ሳይኖር የባሰ ባዶ
ስለሚሆን ከአራት ሰዓት በላይ ሲቆይብኝ ልፈልገው እወጣለሁ። የሆነ መንገድ ላይ ራሱን እስኪስት
ድረስ ሰክሮ ተዘርሮ እያለቀሰ አገኘዋለሁ። ሚዛኔን እስክስት ድረስ ደግፌው ወደቤት እገባለሁ። ብቻ
ከዚህ በኋላ ያለው ላይፋችን በህይወቴ ካሳለፍኳቸው ቀፋፊ ዘመናት ሁሉ በጣም አስከፊዎቹ
ናቸው። ለነገሩ ፃድቃኔ ደርሰን ተመልሰን አቢን እስክንወልድ ድረስ ባለችው ሁለት አመት የማትሞላ
ጊዜ ውስጥ ነው በዘመኔ ሁሉ በደስታ የኖርኩት ፣ ሌላው ሰላሳ ሶስት አመት ና ካሁን በኋላ ያለኝ
ህይወት ዝም ብሎ ዕድሜ እየቆጠሩ መባከን ነው።"
.
"እሺ ከዛ በኋላ ምንድነው የተፈጠረው?"
"ምን ያልተፈጠረ ነገር አለ ብለህ ነው ወንዴ.......ዓለም ክብ አይደለች? ይዘገያል እንጂ
ሁላችንም ወደ መጀመሪያችን መመለሳችን አይቀርም። ያ መጀመሪያችን ደግሞ መጨረሻችን
ነው።"
"ምን ለማለት ፈልገሽ ነው አልገባኝም"
"ቀላል ነገር'ኮ ነው የነገርኩህ እንዴት አይገባህም?.....እኛ ከአፈር ነው አይደል የተፈጠርነው? ያው
ከጊዜያት በኋላ ወደ መጀመሪያችን ተመልሰን አፈር እንሆናለን ፣ ስንወለድ ህፃን ሆነን ነው አይደል?
ከጊዜያት በኋላም ወደ መጀመሪያችን ተመልሰን ስናረጅ እንደገና ህፃን እንሆናለን። ይቺ ምድር
ከአለመኖር ወደ መኖር ስለመጣች ቀኗ ሲደርስ ወደ አለመኖርነቷ ትቀየራለች። እኔም ዕድለ ቢስ
ለደስታ ያልፈጠረኝ ሰው አይደለሁ? እግዜርም ሰይጣንም የተመቻቸ ህይወት ስኖር ይከፋቸዋል
መሰለኝ ተባብረው ወደ መጀመሪያዬ ወደ ጨለማው ህይወቴ መለሱኝ። እኔ'ኮ ግርም የሚለኝ
የሰይጣንስ እሺ ይሁን ፈጣሪ ግን የቁጣ በትሩን ይሄን ያህል እኔ ላይ ያሳረፈው ምን አድርጌው
ነው? በድዬውም ከሆነ ሌሎቹን እንደሚታገሰው እኔንም ለምን አይታገሰኝም! ገራሚ አምላክ እኮ
ነው!! በፈጠረን ፍጡሮቹ ላይ የሚያዳላ!!!"
'ኧረ ሪች እባክሽ እንደዚህ አትበይ'
"ለምንድነው የማልለው?! ከዚህ በላይ እንዳይቀጣኝ ፈርቼ ነው ዝም የምለው? አሁንም
እደግምልሀለሁ አምላክማ ያደላል። እስቲ ላንድ ምሽት ቺቺኒያ ብቻ ናና ተመልከት። የ15 የ16
ዓመት የሚሆኑ የሀብታም ልጆች አንድ ፐብ ለብቻቸው አዘግተው ሲጠጡ ያድራሉ ፣ እዛው በር ላይ
ደግሞ የነሱ እኩያ ቀኑ ጨልሞበት ቡትቶ ለብሶ ስቲኪኒና ሶፍት የበዛበት ትርፍራፊ ምግብ በልቶ
ራሱን ለመርሳት በማስቲሽ ሲጦዝ ታየዋለህ ፣ እና ይሄንን ዝም ብሎ የሚያየው ባያዳላ ነው ብለህ
ነው? ቀላል ያዳላል እንዴ! አንዱን ያለጥፋቱ ዕድሜውን ሙሉ ይቀጣዋል ሌላውን ግን በየሰከንዱ
ሀጢያት ሲሰራ እያየው በደስታ ያንበሸብሸዋል! ጓደኞቼን እንዲህ ስላቸው ሰማይ ቤት ይክሰናል
ይሉኛል። እዚህ ምድር ላይ ሲከፋኝ ላሽ ያለኝን ጌታ ጊዮርጊስን ነው የምልህ ነይ ገነት ግቢ ቢለኝ
አልፈልግም ነው የምለው! እዛም እየተሰቃየሁለት ደስ እንዲለው እፈልጋለሁ። ኤኒሀው እሱን
ተወውና ወደ ጨዋታችን እንመለስ...
.
ቀስበቀስ ቤታችን ውስጥ ወይዘሪት ድህነት ከንፈሯ ላይ ጉበት የመሰለ ሊፒስቲኳን
ለድፋ......ዓይኖቿን ስር ኩል ተቀብታ.....ፀጉሯን አቮካዶ ቅባት ተለቅልቃ.......የሆነ ሸፋፋ ሹል
ጫማ አድርጋ ነገሰችበት። የሲምቢሮዬ ኪስ ትናንት ማንም ሲቸግረው ብር እንደቆሎ
እንዳልዘገነበት ዛሬ ነፋስ የሚያወዛውዘው ሸረሪት ያደራበት ሆነ።
.
ወንድ ልጅ ከሚቸገር የፈለገ ሌላ ነገር ቢደርስበት ይሻለዋል። በተለይ ባል ሆኖ ሚስትና ልጆቹ የሱን
እጅ እንደሚጠብቁ ሲያውቅ ምን ያህል ግርማ ሞገሱ እንደሚገፈፍ በሲምቢሮዬ ስላየሁ ዛሬም
ወንዶችን እየጠላኋቸውም ቢሆን ተቸግረው እንዳያቸው ግን አልፈልግም። ወንዴ የርግማኖች ሁሉ
ርግማን አግኝቶ ማጣት ብቻ እንዳይመስልህ? የትዳር ራስ የሆነው ፣ የጎጆ መከበሪያ የሆነው ፣
የልጁና የሚስቱ ኩራት የሆነው ባል ቤሳቤስቲን ሲያጣ ያ ነው ታላቅ ርግማን! እኛ ሴቶችስ ያንንም
ያንንም አምታተን ገንዘብ እናመጣለን። እናንተ ወንዶች ግን ምንም ማድረግ ስለማትችሉ ቶሎ ነው
ተስፋ የምትቆርጡት። ወንድ ልጅ ተስፋ ቆረጠ ማለት ደግሞ የቤተሰቡ ማፈሪያ