Get Mystery Box with random crypto!

ባሌ በ50 ብር ሸጠኝ ! ክፍል 12 ወንድማገኝ ለማ . . . ================== | የፍቅር አለም LOVES WORLD

ባሌ በ50 ብር ሸጠኝ !

ክፍል 12

ወንድማገኝ ለማ
.
.
.
=====================
"አየህ ወንዴ....ሴት መሆን እንግዲህ ጥቅሙ እዚህ ጋር ነው። ምን መሰለህ? የወንድ ልጅ
ጉልበቱ ጡንቻው ሲሆን የኛ የሴቶች ደግሞ ዕንባችንና ብልጠታችን ነው። አንተ ምን ጠንካራ
ብትሆን አንዲት ሴት ሀይል ሳትጠቀም በዕንባዋ ብቻ ታሸንፈሀለች።
እኔም የሚያውቀው ቢሆንም እያለቀስኩ እስከዛሬ ድረስ በስቃይ እንደኖርኩ ፣ የሴተኛ አዳሪ ህይወት
እንዳንገሸገሸኝ ፣ ከሱ ውጪ የሌላ ወንድ እቅፍ ውስጥ መግባት እንደማልፈልግ ፣ ከውልደቴ
ጀምሮ የተናኩትን ሚስት ተብዬ በማህበረሰቡ ዘንድ መከበር እንደምፈልግ ዕያነባሁ ነገርኩት። ክብር
አሰጠኝ ብዬ እግሩ ስር ተደፍቼ ለመንኩት። በፍቅሬ ስለታወረ ስሜታዊ ሆኖ እሺ አለኝ።
.
አቤ..........................................................
............................................................
..............................ት የተደሰትኩት ደስታ!!!!!!!!!!!!
!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!! ነፍስሽ ከሲኦል ውስጥ ምህረት አግኝታ መንግስተ ሰማያት ልትገባ ነው
እንኳን ብባል እንደዛች ቀን የምደሰት አይመስለኝም! እንደ አይኔ ብሌን የምሳሳለትን አቢን የወለድኩ
ጊዜ እንኳን እንደዛች ቀን አልፈነጠዝኩም! ዓለም በቁጥጥሬ ውስጥ የሆነች መሰለኝ። እንዴት
አልደሰት ወንዴ? ከልጅነቴ ጀምሮ በስቃይ ኖሬ ዛሬ ክብር ሳገኝ ያልፈነጠዝኩ መቼ ልፈነጥዝ ነው?
ከሲምቢሮዬ አፍ የእሺታን ቃል ስሰማ ማመን አልቻልኩም። ቅዠት መሰለኝ። ወራቱ ሀምሌ መጨረሻ
አካባቢ ስለነበር
'ነገውኑ መሄድ አለብን' አልኩት በደስታ እንደ ቁንጫ እየዘለልኩ
"ወዴት?" አለኝ። እኔ ደስተኛ በመሆኔ መላ አካላቱ ጥርስ በጥርስ ሆኖ
'ፃድቃኔ ማርያም ሄደን ሀጢያታችንን ሁሉ ተናዘን ፍልሰታን እዛው ሱባኤ ይዘን አዲስ ህይወት
መጀመር አለብን' ፃድቃኔ ማርያም ከዛ በፊት ሄጄ አላውቅም። ነገር ግን ብዙ የማውቃቸው ሴቶች
እዛ ሄደው ሲመጡ ጥቂቶች ሴተኛ አዳሪነታቸዉን እርግፍ አድርገው ስለተዉ ነው ወደዛ እንሂድ
ያልኩት። ምንም ሳያንገራግር በሀሳቤ ተስማማ።
.
በበነጋታው አውቶቢስ ተራ ሄደን ሰላ ድንጋይ በሚሄድ ካቻማሌ ተሳፍረን ሸገር ለቀን ወጣን።
ዕቃችንን ተሸክመን የገዳሙ ማደሪያ ቦታ ጋር ስንደርስ ፍስለታን ሱባዔ ለመያዝ ከተለያዩ ቦታዎች
የመጡ ሰዎች የሸራ ቤት ሰርተውና የሸራ ቤት እየሰሩ አገኘን። እኛም እሱ የወንዶች ማደሪያ ጋር
እኔም የሴቶች ማደሪያ ጋር አጠናና ሸራ ገዝተን ጊዜያዊ ቤት አሰራን።
.
ፃድቃኔ ማርያም ሄደህ ካላወክ በስተቀር የቦታውን መንፈሳዊነትና ለነፍስህ የሚሰጣትን እርካታ
በቃላት ለመግለፅ መሞከር ከንቱ ልፋት ነው። ያኔ በቃ ጥሩ መንፈሳዊ ሆንን።
ጠዋት ተነስተን ፀበል እንጠመቃለን....ከሰዓት እናስቀድሳለን....ከቅዳሴ መልስ ቆሎ ና በሶአችንን
በቀን አንዴ ብቻ ቀምሰን ማታ ዋሻ ሄደን ፀሎት እናደርጋለን። ደግሞ በጣም የሚገርምህ ነገር
ወንዴ እዚህ በቀን ሶስቴ ና አራቴ እየበላህ ሲርብህ እዛ ግን እፍኝ ቆሎና አንድ ኩባያ በሶ በቀን
አንዴ ብቻ ቀምሰህ የረሀብ ስሜት በጭራሽ አይሰማህም። ከዛ ጥቂት ቆይተን ወደ ፀበሉ መሄጃ
ያለ ዋሻ ጋር የሚኖሩ አንድ ባህታዊ አግኝተን ሀጢያታችንን ተናዘን ንሰሀ ገብተን ፍፁም መንፈሳዊ
ሆንን። ሐምሌ መጨረሻ ላይ ሄደን ሐምሌ መጨረሻ ላይ ሄደን ፍልሰታ ሲያልቅ እንመጣለን ብለን
አስበን የነበርነው ሰዎች እስከ መስከረም 21 ቀን ድረስ እዚያው ነበርን።
.
ሁለታችንም ማርያምን ምስክር አድርገን ቃል ኪዳን ተገባባን ፣ አጫፋሪ ሳያስፈልገን ቀለበት
አሰርን። ሲምቢሮዬ አርግዞኝ አምጦኝ እንደገና የወለደኝ መሰለኝ። ዕድሜ ዘመኔን ያለጥፋቴ
የበደለኝን አምላኬን አልሜውም አስቤውም የማላውቀውን ትቢያ ከሆነው ከሴተኛ አዳሪ ህይወት
አውጥቶ ለትዳር ዙፋን ስላጨኝ የሚስትነትን ዘውድ እንድጭን ስላደረገኝ በመዝሙር
እያመሰገንኩት ወደ አዲስ አበባ መጣን።
.
አዲስ አበባ እንደደረስን ቤቴ ዝም ብለሽ አትገቢም ብሎ መጠነኛ ድግስ ደግሶ የኔና የሱ ጓደኞች
በተገኙበት የእወቁልን ግብዣ አደረግን። ሴተኛ አዳሪ የሆኑ ጓደኞቼ በማግባቴ በደስታ እያነቡ
መቋቋሚያ ብለው ሴትነታቸውን አርክሰው ከሸቀሉት ገንዘብ ላይ የአቅማቸውን አዋጥተው ሰጡኝ።
የሱም ሹፌርና ወያላ ጓደኞቹ እንዲሁም ትርፍ ሲጭን ቤልት ሳያስር ሲቀር የማይቀጡት ጉቦ
የሚሰጣቸው ሁለት ሀይገር ባስ ሀይገር ባስ የሚያካክሉ ትራፊኮችም የቻሉትን አንድ አንድ የቤት
ዕቃ ገዙልን። እኔ እየተፈጠረ ያለውን ነገር ማመን ስላልቻልኩ መጠጥ ሳልቀምስ እንደ ሰከረ ሰው
ጎረቤት እስኪገረም ድረስ እጮህ ነበር። ዕንባዬን መቅጣጠር አቅቶኝ አይኔን እስኪለበልበኝ ድረስ
አለቅሳለሁ.......ወንዴ ያኔ ያደረኩትን አብዛኛውን ነገር አላስታውሰውም።
.
ያው አዲስ ሙሽራ አይደለሁ? ለሊት ባሌ ከእንቅልፉ ሳይነሳ ቁርስ ሰርቼ ቀስቅሼ አበላዋለሁ። ያን
ሰሞን ደግሞ በነፃ ሲያገኘው ብርቅ ሆኖበት አብረን መተኛት አብዝተን ነበርና እንዲወፍርልኝ ብዬ
የቡላ ገንፎ.....አጥሚት...
..ቅቅል....ብቻ የተገኘውን ምግብ ባፍባፉ እጎሰጉስበት ነበር። እኔን ደስታ ሆዴን ሞልቶኝ ስለነበር
እሱን በማብላት እጠግብ ነበር። ከሰአትም ፒያሳ ታክሲ ተራ ድረስ ጎላ ብረት ድስት የሚያክል ምሳ
ዕቃ ተሸክሜ እሄድና አበላዋለሁ። ጓደኝቹ እስኪቀኑበት ድረስ ሙሉ በሙሉ ለወጥኩት። ስራ ለሊት
ስለሚወጣ 12:00 እንዲጨርስ አደርገውና ሲኒማ አምፒር ገብተን በግድ ሊያስቁን
የሚለማመጡን ተዋንዋያን የሚሰሩትን ፊልም አለማሳቁ እያሳቀን እናያለን....ሲኒማ ቤት መግባት
ሲሰለቸን ወይናችንን ገዝተን ግማሽ ኪሎ ስጋችንን ጠብሰን ቤታችን ውስጥ እየበላንና እየጠጣን
ጋቢያችንን ደረብ አድርገን ሶፋችን ላይ ተጋድመን ሮማንስ ፊልም እናያለን። ለመኖሪያችን
የሚቀርቡንን ቤተ ክርስቲያኖች የወር በአላቸው ሲሆን ጧፍ እያበራን ጉባኤ ላይ እንታደማለን።
ሳንቲም የሸቀለ ሰሞን እሁድን ከከተማ ወጥተን አየር ለውጠን እንመለሳለን። ከዚህ በላይ ምን
እፈልጋለሁ? አበድኩልህ!
.
የኔ ሲምቢሮም ሰውነቱ መለስ እያለ መጣ። ቤታችንን በሚያስፈልገን ዕቃ አሟላን። ከዛ ጭቃ
ህይወት አላቆ ይሄንን ክብር የሰጠንን አምላካችንን ጠዋት ማታ ያለመታከት ማመስገን ጀመርን።
ከዚህ በኋላ ልጅ መውለድ አለብን ተባባልን። አረገዝኩለት። አቤት እንክብካቤ! እንዴት አባቱ
አሞላቀቀኝ መሰለህ!?
ዘጠኝ ወር ሙሉ ቅብጥ ብዬ የእርግዝና ጊዜዬን ጨርሼ አቢን ወለድኩ። አቢ ሲወለድ ስራ መስራት
እስከማይችል ድረስ ቤቴ ቤቴ ማለት አበዛ። በብቸኝነት ገንዳ ላይ የተጣልኩት፣ የዝንብ ትራፊ እበላ
የነበርኩት ፣ የአባቴ መለመኛ ብቻ የነበርኩት ፣ ባመንኳት በመአዛ ለዛች ለደዘደዝ የተሸጥኩት እኔ
መከረኛዋ ራሔል ዓይኔን ባይኔ አየሁ።
"አድረግህልኛልና በቸርነትህ
አመሰግንሀለሁ እልል እልል
ለዓለም ለዓለም አማኑኤል
እገዛልሀለሁ መድሀኒዓለም" እያልኩ እኔና ሲምቢሮዬን ከሁለት ወደ ሶስት ያሸጋገረኝን ጌታዬን
አመሰገንኩት።
.
ይሄ የኔም የባሌም ደስታችን ግን ከስድስት ወር በላይ ሊቀጥል አልቻለም" አለችና ትንሽ አሰብ
አደረገች
'ለምን?' አልኳት
" ያው አበሳዬን ሊያሳየኝ አይደል የፈጠረኝ....
:
:
:
ይቀጥላል

╔═══❖• •❖═══╗
@silefikrr
╚═══❖• •❖═══╝
4 any comment @manditua