Get Mystery Box with random crypto!

ባሌ በ50 ብር ሸጠኝ ! ክፍል 11 ========================== 'አዎ ምን መ | የፍቅር አለም LOVES WORLD

ባሌ በ50 ብር ሸጠኝ !

ክፍል 11



==========================
"አዎ ምን መሰለህ? የሱ ትልቁ ችግር.....እኔም እንዳላገባው ያስፈራኝ የነበረው ፣ ሲበዛ ለሱሱ
ሟች ነው። ምድር ላይ ሳይደነዝዝ መኖር አይችልም። ሱስ እየተጠቀመ ከሚደርስበት አካላዊና
አእምሮአዊ ጉዳት በላይ ሱሱን ቢያቆም የሚደርስበት ስቃይ ይበልጣል። የሌለበት የሱስ አይነት
አልነበረም። ጃንኪና ይወጋል(( የመርፌውን ሀሽሽ)).....በጋንጃ ይጦዛል.....በሲጋራ ጭስ ስሙን
መፃፍ እስኪችል ድረስ ቼን ስሞከር ነው....ኤልያስ ጥርሱ ይግላል እንጂ አይመረቅንም እስኪባል
ድረስ በርጫውን ያደቃል.....ጠርሙስ ውስጥ የተወለደ ይመስል ሀሞቱን እስኪተፋ ድረስ ሜንት
አረቄ ይጠጣል.......በርግጥ እኔም እሱ የሚጠቃመቸውን ማደንዘዣዎች በሙሉ እጠቀማለሁ። እኔ
ግን ሴት ነኝና ትዳር ውስጥ ከገባሁኝ የተከበረች ሚስት መሆን ስለምፈልግ ሱሶቼን በሙሉ
እተዋለሁ ብዬ ወስኜ ነበረ። እሱ ግን በተለይ ሳይጠጣና ሳይጦዝ መዋልና ማደር አይችልም። ይሄ
አመሉ አግብቼው አብሬው እንዳልኖር ያስፈራኝ ነበር።
.
ወንዴ ትዳር ማለት አፈቅርሀለሁ አፈቅርሻለሁ ፣ ያላንቺ አልኖርም ያላንተ መኖሬ ትርጉም የለውም
እየተባባልክ እንደፍቅረኝነት ዘመንህ ስለተፎጋገርክ ብቻ ጎጆ አይመሰረትም። ተጋባህ ማለት
የራስህን ግዛት ፣ የራስህን ትንሽዬ ሀገር መሰረትክ ማለት ነው። ባልየው የቤቱ ራስ ስለሆነ ጠቅላይ
ሚኒስተር ፣ የገቢ ምንጭ ስለሆነ ገንዘብ ሚኒስተር ፣ ሚስትና ልጆቹን ከአደጋ ስለሚከላከል
መከላከያ ሚኒስተር ይሆናል ፤ ሚስትየዋ ደግሞ ለልጆቿ ትምህርት ሚኒስተር ፣ ቤተሰቡ
ከህብረተሰቡ ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲኖረው ስለምታደርግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፣ ባሏና ልጆቿ
እንዳይራቡ ግብርና ሚኒስትር ትሆናለች። ይሄንን የሚያህል ትልቅ ተቋም ውስጥ ስለተፋቀርክ ብቻ
ዘው ብለህ አትገባም። የነገ ህይወትህ ላይ ዛሬ ቆም ብለህ የማያዳግም ውሳኔ መወሰን አለብህ።
.
እኔም ለብዙ ጊዜ የኤልያስን የእንጋባ ጥያቄ እየደጋገምኩ አሰብኩበት። ለራሴ እንዲህም
አልኩት......
'ትሰሚኛለሽ ሪች ተጋባችሁ ማለት አንቺ ሴተኛ አዳሪ እርግፍ አድርገሽ ታቆሚያለሽ ፣ ያ ማለት
በፓኪስታንኛ የቤቱ ኢኮኖሚካል ጥያቄ በሙሉ የሚሸፈነው እሱ በሚያገኘው ገቢ ይሆናል ማለት
ነው። በገንዘብ በኩል የራሱ ታክሲ ስላለው ፣ የሚኖርበት ኮንዶሚኒየም የግሉ ስለሆነ ስጋት
አይግባሽ። ያ ማለት ግን ምንም ችግር የለም ማለት አይደለም። እሱ ቢያንስ ቢያንስ በቀን ለሱሱ
ብቻ ከ300-400 ብር ድረስ ያጠፋል። ስለዚህ አብረሽው ለመኖር የምትፈልጊ ከሆነ ኤልያስን
ከሱሱ እንዲላቀቅ ማድረግ አለብሽ። አንድ ባል ሱሰኛ መሆን የሚገባው የሚስቱና የልጆቹ ብቻ
ነው።
.
ሴት ስትሆን ትልቁ ፀጋህ ፈጣሪ ሲፈጥርህ ብልጥ የሆነና ከብዙ አንግሎች አንፃር ማሰብ የሚችል
አእምሮ ይኖርሀል። እናም ኤልያስን አሁን ከሚያፈቅረኝ በላይ ከነፍሱ እንዲያመልከኝ አደረኩት።
እስኪገረም ድረስ እየተንከባከብኩት ካለኔ መተንፈስ እስከማይችል ድረስ ሁሉ ነገሩ ሆንኩለት።
ነፍሱ ከአምላኩ በላይ በኔ ቁጥጥር ስር ሆነች። አምላክ ለሙሴ ከሰጠው አስርቱ ትዕዛዛት በላይ ፣
ኢየሱስ በምድር ላይ ሳለ ከተናገራቸው ስድስቱ ቃላተ ወንጌላት ይበልጥ የኔን ቀጭን ትዕዛዝ
ያከብርና ይፈፅም ነበር። አምላካችሁን በቀን ውስጥ አንዴ ወይ ሁለቴ ልታስቡት አሊያም ከነጭራሹ
ትዝ ላይላችሁ ይችላል ፣ ስለኛ ግን ሳታስቡ መዋልና ማደር አትችሉም። በየሰአቱ በየደቂቃው
በየሰኮንዱ ሽርፍራፊ ሁሉ ስለሴት ልጅ ስለምታስቡ እናንተን በቁጥጥራችን ውስጥ ለማዋል ልክ
ክሬም ኬክ እንደመቁረስ ያህል ለኛ ቀላል ነው።
.
እዛች አንሶላ የምታህል ፍራሽ ላይ ጋደም ብለን እንዲህ አልኩት....
'የኔ ሲምብሮ'
"ወይዬ የኔ ጣኦት" አለኝ። በቃ የዛን ሰሞን በፍቅሬ ደንዝዞ ስለነበር ወሬው ሁሉ ልቦለዳዊ ነበር
የሚመስለው።
'ከኔ ጋር አብረህ መኖር ትፈልጋለህ አይደል?'
አብረን እንኑር ያልኩት ይመስል ከተጋደመበት ፍንጥር ብል ተነሳና እላዬ ላይ ወጥቶ ዓይን ዓይኔን
እያየኝ.......
"የኔ ጣኦት! እዚች ምድር ላይ ብቻ መሰለሽ እንዴ አብሬሽ መኖር የምፈልገው? ሞቼ ስጋዬ ምስጥ
ሆኖ እንኳን(( እዚች ጋር እኔ ጣልቃ ልግባማ....እኛ ከአፈር ከተሰራን ስንሞት ለምንድነው ምስጥ
የምንሆነው? ሰው ማለት በትናንሽ ምስጦች የተገነባ ፍጡር ነው እንዴ? ፈረንጆቹም ሲሞቱ እንደኛ
ምስጥ ይሆናሉ? ወይንስ ሀበሻ ብቻ ነው በህይወት እያለ ትልቅ ምስጥ ሲሞት ትናንሽ ምስጥ
የሚሆነው?))(ፍልስምና)
....በአጥንቴ ብቻ ቀርቼ የምፅአት ቀን ሲደርስ መለከት ሲነፋ......ምድር ከመኖር ወደ አለመኖርነት
ስትቀየር.....ሀጥያን በግራ ፃድቃን በቀኝ ሲቆሙ......ልክ ምግባራችን የተመዘገበበት መዝገብ
ከመገለጡ በፊት......ጌታን እኔ እንዲህ እለዋለሁ
'ይቅርታ.....ይቅርታ.....አንድ ጊዜ ለማውራት ቢፈቀድልኝ?' ጌታም ቀና ብሎ አጥንታም ነፍሴን
ያይና በዝምታው ተናገር ይለኛል።
'እኔ ከጣኦቴ ተለይቼ መንግስተ ሰማያት ከምገባ የእሳት ባህር ወዳለበት ገሀነም ብጣል ይሻለኛል!
ጌታ ሆይ እባክህ ስለ ጭንቅ አማላጇ ስለ እናትህ ብለህ ከራሔል አትለየኝ?' ብዬ አጥንታሙ ፊቴ
ላይ የአጥንት ዕንባ እያነባሁ ፊቱ ተደፍቼ ስለምነው የነገሩትን የማይረሳ የለመኑትን የማይነሳ የኔ
ጌታ.....እስከዛሬ ድረስ በሰው ልቦና ያልታሰበ አዲስ ዓለም ይፈጥርና እኔና አንቺን ብቻ
ወደተዘጋጀልን የክብር ስፍራ ይልከናል። እኔና አንቺም አዲሱ ሰማይ ቤታችን ላይ ሚጢጢ ሚጢጢ
ልጆች ወልደን በደስታ በተድላ እንኖራለን......እሜቴ ይሄን ያህልማ አይመሰጡ.....በሉ ተረቴን
መልሱ አፌን በከንፈርዎ ያብሱ!' ብሎ ያው እንደለመደው ብዙ ማውራት እየፈለኩኝ ከንፈሬን ትንፋሽ
እስኪያጥረኝ ድረስ መጠመጠኝና አይሆኑ አይሆኑ ቦታ ነካክቶኝ ቅንዝርዝ
.
ጥቂት ቆይቼ ዓይን ዓይኑን እያየሁት
'...የኔ ሲምቢሮ ዘላለም አብረኸኝ መኖር ከፈለክ ሱስህን በሙሉ እርግፍ አድርገህ መተው አለብህ'
ስለው ፊቱ ላይ የቅሬታ ስሜት አነበብኩ።
.
አውቃለሁ ያለሱሱ መኖር እንደማልችል! ይገባኛል ለዘመናት በብቸኝነቱ ዋሻው ውስጥ ተመሽጎ
ሲኖር ከሰዎች ይልቅ ሱሶቹ ቀድመው ደርሰውለት አጫዋች ጓደኛ ፣ ሀዘኑን መርሻ እንደሆኑት!!
አሁን ግን እኔ በህይወቱ ስለመጣሁ መደንዘዝ አያስፈልገውም። ሊያገባኝ ከፈለገ ለጎጆው ሲል
በተቃራኒው መንቃት አለበት። እሱ ካለሱሶቹ ከሚኖር እየተጎዳም ቢሆን እኔን ቢያጣ እንደሚመርጥ
ሳይመረኝ የምውጠው ሀቅ ነው።" አለችኝና ከተቀመጠችበት ተነስታ ከቁምሳጥኗ ውስጥ የሺሻ
ዕቃዋን አወጣች ፣ ስቶቭ ላይ ደቃቃ ከሰሎችን አቀጣጠለች ፣ ውሀውን ቀየረች ፣ ቡሬው ውስጥ
አዲስ መዋሰል ከትታ በአልሙኒየም ሸፈነችው ፣ የከሰል ፍሙን በመርፌ በሳሳችው አልሙኒየም
ላይ አድርጋ ሺሻዋን ማንደቅደቅ ጀመረች። ለኔም ቀዝቀዝ ያለ ቢራ ሰጠችኝ። የጉሮሮዬን ድርቀት
ጎንጨት ብዬ አለሰለስኩት። ጥቂት ፋታ ከወሰድን በኋላ.......
.
"እና ሱሱን እንዲያቆም አደረግሽው ወይስ አልሰማሽ አለ?" አልኳት በድጋሚ እንደ'ሷ ህይወት
የሚጎመዝዘውን ቢራ እየተጎነጨሁ..
"አየህ ወንዴ....ሴት መሆን እንግዲህ ጥቅሙ እዚህ ጋር ነው.......ምን መሰለህ...........
:
:
:
ይቀጥላል

╔═══❖• •❖═══╗
@silefikrr
╚═══❖• •❖═══╝
4 any comment
@manditua
❥❥____