Get Mystery Box with random crypto!

1500 አመት እድሜ ያለው የሐዋሪያው ጴጥሮስን መኖሪያ ቤት የሚጠቁም ጽሁፍ ማግኘታቸውን አርኬዎሎጂ | Agape Love❤

1500 አመት እድሜ ያለው የሐዋሪያው ጴጥሮስን መኖሪያ ቤት የሚጠቁም ጽሁፍ ማግኘታቸውን አርኬዎሎጂስቶች ገለጹ።
የእስራኤል እና የኣሜሪካ ኣርኪዎሎጂስቶች ቡድን በገሊላ ባህር ኣቅራቢያ ባደረጉት ቁፋሮ 1,500 አመታት እድሜ ያለው ህንጻው የሐዋሪያው ጴጥሮስ መኖሪያ ቤት በነበረበት ቦታ ላይ መሰራቱን የሚጠቁም ጽሁፍ አግኝተናል ብለዋል።
በግሪክ በተጻፈው በዚህ ጽሁፍ ላይ ‘ቆስጠንጢኖስ የክርስቶስ ኣገልጋይ’ የሚል በ4ተኛው ክፍለ ዘመን ክርስትናን የተቀበለው የሮማ ንጉሰ ነገስት ስም የሚጠቅስ ቃላት የተጻፈ ሲሆን ‘የሰማያዊ ሐዋሪያት መሪና አለቃ” የሚል ስም አንደተካተተበት ተገልጿል።
ይህ ‘የሐዋሪያት መሪና ኣለቃ’ የሚለው መጠሪያ የቤዛንታይን ክርስቲያን ጸሃፊዎች ሐዋሪያው ጴጥሮስን ለመግለጽ የሚጠቀሙበት መጠሪያ እንደነበር ዜናው ጠቅሷል።
ቁፋሮውን ያደረጉት የእስራኤል ኪነሬት ኮሌጅ እና የኒውዮርክ ኒያክ ኮሌጅ አጥኚ ቡድን ኣባላት በጴጥሮስ እና በወንድሙ በእንድሪያን ቤቶች አቅራቢያ ተገንብቷል ተብሎ የሚታመን የቤዛንታይን ዘመን ቤተክርስቲያን ህንጻ ማግኘታቸውን ኣስታውቀው ነበር።ዜናውን የዘገበው ክርስቲያን ሄድ ላይንስ ነው።