#እነሆ_አዲስ_መጽሐፍ #መጽሐፈ_ሐዊ ጥንታዊው የብራና መጽሐፍ 'መጽሐፈ ሐዊ' እንሆ በግእዝ እና | ሺኖዳ መጻሕፍት አቅራቢ - 𝐒𝐡𝐞𝐧𝐨𝐝𝐚 𝐁𝐨𝐨𝐤𝐬 𝐃𝐞𝐥𝐢𝐯𝐞𝐫𝐲

Picture 1 from ሺኖዳ መጻሕፍት አቅራቢ - 𝐒𝐡𝐞𝐧𝐨𝐝𝐚 𝐁𝐨𝐨𝐤𝐬 𝐃𝐞𝐥𝐢𝐯𝐞𝐫𝐲 2022-05-12 14:06:30
#እነሆ_አዲስ_መጽሐፍ
#መጽሐፈ_ሐዊ

ጥንታዊው የብራና መጽሐፍ "መጽሐፈ ሐዊ" እንሆ በግእዝ እና አማርኛ ተተርጉሞ ለንባብ በቃ።

ይሄ መጽሐፍ በአብዛኛውን ጊዜ በማጣቀሻነት ሰዎች ሲጠቀሙበት እናያለን። ነገር ግን ገበያ ላይ ወጥቶ ለንባብ ቀርቦ አልታየም። ምክንያቱም መጽሐፉ እጅግ ትልቅ መጽሐፍ መሆኑና የተጻፈውም በብራና የተጻፈ ስለነበር ለገበያም አያመችም ነበር።

በብራና ሲጻፍ በወቅቱ 260 የፍየል ቆዳ እንደፈጀ በታሪኩ ላይ ተቀምጧል። ክብደቱም አሁን ላይ ሲለካ 17 ኪሎ ግራም ነው። አሁን ግን መጽሐፉ 22 ምዕራፎችን ብቻ የያዘ ቅጽ ፩ ለገበያ ቀርቧል። ቀሪው ደግሞ በቀጣይ እንደሚታተም ሰምተናል።

መጽሐፈ ሐዊ በአንድ አርዕስት ወይም በአንድ ሃሳብ ብቻ የተወሰነም አይደልም። በተለያዩ ሃሳቦች እና ጭብጦች ያታጨቀ መጽሐፍ ነው። ከነዚህም በጥቂቱ፦

በምሥጢር የሚያራቅቅ
☞በአእምሮ የሚያመጥቅ
☞በመንፈስ የሚያረቅ❖

☞ ሃይማኖትን ከምግባር የሚያሰናስል
☞ሥርዓትን ከትውፊት የሚፈትል

☞መርሐ ክርስቶስን ከሐዋርያት
☞ተለውተ ሐዋርያትን ከሊቃውንት
☞ፍና አበውን ከቅዱሳን አንደበት ያገናኘ
በሊቁ አባት በአንትያኮስ ተሰብስቦ የተዘጋጀው ጥንታዊው መጽሐፍ ነው።

ሰለ ግብረ ገብነት፣ ስርዓተ ምንኩስና፣ ስለ ንጽሕና (ድንግልና)፣ ነገረ ፍልስፍና፣ በሃይማኖት ስለ መጽናት እንዲሁም ስለ ቀደሙት ቅዱሳን እና ሌሎችን በደንብ አድርጎ የሚናገር በቅዱሳን አባቶች ተከትቦ የቆየ መጽሐፍ እንደሆነ ይነገራል። ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌም በብዙ መንገድ ሲገልጹት ነበር። ምክንያቱም መጽሐፈ ሐዊ ብዙ ምርምሮችን በውስጡ አብሮ ይዟል።

ለዚህ ዘመን ትውልድም የአባቶችን እግር ተክተው የተረጎሙትን ሊቀ ጠበብት መሠረትን ልናመሰግናቸው ይገባል።
ሺኖዳ መጻሕፍት አቅራቢ - 𝐒𝐡𝐞𝐧𝐨𝐝𝐚 𝐁𝐨𝐨𝐤𝐬 𝐃𝐞𝐥𝐢𝐯𝐞𝐫𝐲

ሺኖዳ መጻሕፍት አቅራቢ - 𝐒𝐡𝐞𝐧𝐨𝐝𝐚 𝐁𝐨𝐨𝐤𝐬 𝐃𝐞𝐥𝐢𝐯𝐞𝐫𝐲

@shenodabooksdelivery
1.55K ተመዝጋቢዎች
ሃይማኖት ምድብ
👉 ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ ማንኛውንም መፅሐፎች ይዘዙን። ያለ ተጨማሪ ክፍያ እንልክለዎታለን✈️ ባሉበት እናደርስል...