Get Mystery Box with random crypto!

' ሲቪል ዜጎችን ለመመገብ የሚደረገውን ጥረት ማደናቀፍ እጅግ የጭካኔ ተግባር ነው። የተዘረፈውን ነ | ሸገር jobs

" ሲቪል ዜጎችን ለመመገብ የሚደረገውን ጥረት ማደናቀፍ እጅግ የጭካኔ ተግባር ነው። የተዘረፈውን ነዳጅ መልሱ " - ሳማንታ ፓወር

የአሜሪካ ህዝብ ተራድኦ ድርጅት (USAID) አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር ፤ ህወሓት (TPLF) የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለስራ የሚጠቀምበትን 150,000 ጋሎን ነዳጅ መዝረፉን በመግለፅ ድርጊቱን አጥበቀው አውግዘዋል።

በተጨማሪም በእርዳታ ሰራተኞች ላይ እንግልት መድረሱን በመጠቆም ፤ ህወሓት (TPLF) በእርዳታ ሰራተኞች ላይ ያደረሰውን እንግልት ድርጅታቸው አጥብቆ እንደሚያወግዝ ገልፀዋል።

" ኢትዮጵያውያን ሲቪል ዜጎችን ለመመገብ የሚደረገውን ጥረት ማደናቀፍ እጅግ የጭካኔ ተግባር ነው " ያሉት ፓወር ህወሓት (TPLF) የዘረፈውን ነዳጅ እንዲመልስ በድርጅታቸው ስም ጥሪ አቅርበዋል።

ከነዳጅ ዝርፊያ ጋር በተያያዘ አሁንም ዓለም አቀፍ ተቋማት ድርጊቱን እያወገዙ ሲሆን ህወሓት (TPLF) በሰጠው ምላሽ " ከወራት በፊት ለዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ያበደርኩትን ነዳጅ መልሼ ወስድኩ እንጂ ዘረፋ አልፈጸምኩም " ብሏል።

ነዳጁን ለድርጅቱ ያበደርኩት ከጥቂት ወራት በፊት በነዳጅ እጥረት ምክንያት የምግብ እርዳታ ማከፋፈል ባለመቻሉ ነው ያለው ህወሓት ድርጅቱ ነዳጅ መበደሩንና እንደሚመልስ ግንዛቤ ነበር ሲል ገልጿል፤ " ስምምነታችን በጽሁፍ ተሰንዶ ተቀምጧል " ሲል እየቀረበበት ላለው ክስ ምላሽ ሰጥቷል።

#ArifNeger

ዩትዩብ: https://youtube.com/c/Addisnegertop10

ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@arifneger24

ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/Arifneger

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/Arifnegermedia/
!