Get Mystery Box with random crypto!

ታዋቂው ኢራቃዊ ፓለቲከኛ አል ሳድር፤ ራሱን ከፖለቲካው እንዳገለለ ማስታወቁን ተከትሎ በሃገሪቱ ከፍ | ሸገር jobs

ታዋቂው ኢራቃዊ ፓለቲከኛ አል ሳድር፤ ራሱን ከፖለቲካው እንዳገለለ ማስታወቁን ተከትሎ በሃገሪቱ ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል

የአል ሳድር ደጋፊዎች ቤተ መንግስት ሠብረው መግባታቸውን ተከትሎ በባግዳድ ሰዓት እላፊ ታውጇል

ኢራቃዊው የሺዓ እስልምና መሪ እና ፖለቲከኛ ሙቅታዳ አል ሳድር
አል ሳድር ጥቅምት ላይ የተካሄደውን ምርጫ ቢያሸንፍም መንግስት ለመመስረት አልቻለም

ኢራቃዊው የሺዓ እስልምና መሪ እና ፖለቲከኛ ሙቅታዳ አል ሳድር ራሱን ከፖለቲካው እንዳገለለ ማስታወቁን ተከትሎ በኢራቅ ከፍተኛ ህዝባዊ ቁጣ ተቀሰቀሰ።

በሺዎች የሚቆጠሩ የፖለቲከኛው ተከታዮች ውሳኔውን በመቃወም ወደ ብሔራዊ ቤተመንግሥት ሰብረው ገብተዋል። አዲስ ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሰየም ተሰብስቦ የነበረውን የሃገሪቱን ፓርላማም ተቆጣጥረዋል።

ይህን ተከትሎ በአስቸኳይ የካቢኔ ስብሰባ ላይ የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አል ካዲሚ ስብሰባውን በትነው ወጥተዋል። በቤተ መንግስቱ እና በአካባቢው ከባድ ጥበቃ እየተደረገም ሲሆን በባግዳድ ሰዓት እላፊ ታውጇል።

ስልጣን ባይዝም በፖለቲካ ተሳትፎው ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረው አል ሳድር "በፖለቲካ ጉዳዮች ውስጥ ላለመግባባት ወስኛለሁ” በሚል ነበር ራሱን ከፖለቲካው ማግለሉን በይፋዊ የትዊተር የማህበረሰብ ትስስር ገጹ ያስታወቀው።

#ArifNeger

ለፈጣን መረጃዎች
ዩትዩብ: https://youtube.com/c/Addisnegertop10

ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@arifneger24

ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/Arifneger

ቴሌግራም: https://t.me/arifnegermedia

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/Arifnegermedia/