የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ቱርክ እና ሌሎችም አገራት ከአፍሪካ ጋር ሊያቀያይሙን አፍራሽ ፕሮፓጋንዳ እየነዙብን ነው ማለታቸውን ቱርክ አጥብቃ ነቀፈችው፡፡
የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማክሮን እኛን ከመክሰስ አገራቸው በቅኝ አገዛዝ ዘመን የፈፀመቻቸውን ጥፋቶች ቢያርሙ ይሻላቸዋል የሚል መግለጫ ማውጣቱን ዴይሊ ሳባሕ ፅፏል፡፡
ማክሮን ከቱርክ በተጓዳኝ እንደ ሩሲያ እና ቻይና ያሉ አገሮች የፈረንሳይን ስም እያጠፉ ነው ያሏቸው አገሮች ናቸው፡፡
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት በዚህ ጉዳይ ላይ የተናገሩት በአልጀሪያ የሰሞኑ ጉብኝታቸው ወቅት ነው ተብሏል፡፡
የማክሮንን አስተያየት በተመለከተ ከሩሲያ እና ከቻይና በኩል የተሰጠ ምላሽ በዘገባው አልተጠቀሰም፡፡
#ArifNeger
#Ethiopia #Ethiopiannews #ዜና #News
ለፈጣን መረጃዎች
ዩትዩብ: https://youtube.com/c/Addisnegertop10
ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/@arifneger24
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/Arifneger
ቴሌግራም: https://t.me/arifnegermedia
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/Arifnegermedia/
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!