Get Mystery Box with random crypto!

Amhara times

የቴሌግራም ቻናል አርማ shegermidias — Amhara times A
የቴሌግራም ቻናል አርማ shegermidias — Amhara times
የሰርጥ አድራሻ: @shegermidias
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.54K
የሰርጥ መግለጫ

ኑ ለኢትዮጵያ እንታገል
መረጃ በ @Amhratimesbot ልታደርሱኝ ትችላላችሁ

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-03-05 19:39:23 የአሜሪካ እና የቻይና እሸጥአገባ ቀጥሏል
አሜሪካ ዜጎቿ በቻይና ኢንቨስት እንዳያደርጉ ከለከለች
ዋሽንግተን በተለይም የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በቻይና ኢንቨስት እንዳያደርጉ እገዳ ጥላለች። አሜሪካ ቻይናን በዋና ጠላትነት የፈረጀች ሲሆን ቤጂንግ ዓለምን መቆጣጠር ትፈልጋለች ስትል ከሳለች።
RT
የካቲት 26/2015 ዓ.ም
====================
1.3K views16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 18:32:47 በመሆኑም መንግሥት ለዘመናት የኖረች እና ከግማሽ የሀገሪቱ ህዝብ በላይ የያዘችን ቤተ ክርስቲያን ክብርና ልዕልና በሚዳፈር መልኩ በተፈጸመው ሕገ ወጥ ተግባር ላይ የተሳተፉ እና ይህን ድርጊት የፈጸሙ የጸጥታ አካላትና እንዲፈፀም ያዘዙ የመንግሥት ኃላፊዎችን በ፲፭ ቀናት ጊዜ ውስጥ ለይቶ በሕግ እንዲጠየቁ እንዲያደርግ እና ይህንንም ለቤተ ክርስቲያኒቱም ሆነ ለሕዝበ ክርስቲያኑ በግልጽ እንዲያሳውቅ እንዲሁም በተለመደው የሀሰት ውንጀላ በዓላችንን በማክበር ላይ እያሉ የመንግሥት የፀጥታ አካላት በፈፀሙት ሕገ ወጥ ተግባር ምክንያት በተፈጠረው ግርግር መነሻት የታሰሩ ምእመናንን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ እየጠየቅን ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ቤተ ክርስቲያን መብቷን ለማስከበር ወደ ቀጣይ እርምጃዎች የምትገባ መሆኑን በአክብሮት እያሳወቅን ይህንንም ድርጊት ተከታትሎ የሚያሳውቅ እና የሚያስፈጽም የሕግ ባለሙያዎች ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደሥራ እንዲገባ የሚደረግም መሆኑን ጭምር እናሳስባለን፡፡

በዚህ ሕገ ወጥ ድርጊት የሊቀ ሰማዕቱን የቅዱስ ጊዮርጊስ ክብረ በዓል ለማክበር በመምጣት ህይወቱን ላጣው ልጃችን እግዚአብሔር ነፍሱን በአብርሃም፣ በያዕቆብና በይስሐቅ እቅፍ ያኑር፣ ለቤተሰቦቹም መጽናናትን ያድልልን እያልን ቀላልም ሆነ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባችሁ የቤተ ክርስቲን የጭንቅ ቀን ልጆች ደማችሁን እና መከራችሁን እንደ ሰማእታት ዋጋ ይቆጥርላችሁ ዘንድ ጸሎታችን ነው፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
የካቲት ፳፬ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ኢትዮጵያ
1.7K views15:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 18:32:31 "የቤተ ክርስቲያን በዓል እንዲረበሽ እና ምእመናን ህይወታቸውን እንዲያጡ እንዲሁም እንዲጎዱ ያደረገው ከመንግሥት የጸጥታ መዋቅር የተተኮሰው አስለቃሽ ጭስ እና ጥይት መሆኑ ለሁሉም የታወቀ ሆኖ እያለ ጉዳዩን ወደ ሌላ አካል ለማላከክ የተሄደበትን ርቀት ቤተ ክርስቲያን በፍፁም የምትቀበለው አይሆንም፡፡" ብፁዕ አቡነ ሄኖክ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

በየካቲት ፳፫ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ላይ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች አማካኝነት የተፈጸመውን ሕገ ወጥ ድርጊት አስመልክቶ ከአዲስ አበባ ሀገረ ሰብከት የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከሀገራችን ኢትዮጵያ ሀገረ መንግሥት ምሥረታ ጀምሮ ያለችና መንግሥትን ያጸናች፣ የራሳቸው የጽሑፍ ቋንቋ ካላቸው ጥቂት ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ እንድትሆን ፊደል ቀርፃ ያስተማረች፣ መንግሥት የአረንጓዴ አሻራን መርሐግብር ከማስጀመሩ ከሺህ ዓመታት በፊት የአካባቢ ጥበቃን ስትሠራ የኖረችና አሁንም በየአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት፣ ገዳማትና አድባራት የአካባቢ ጥበቃ ሥራን የምትሠራ፣ ዘመናዊ ትምህርት ከመጀመሩ ከሺህ ዓመታት በፊት ሥርዓተ ትምህርት ቀርፃ ያስተማረችና የሀገር መሪዎችን፣ የስነ ህንፃ ባለሙያዎችን፣ የመድኃኒት አዋቂዎችንና ተመራማሪዎችን ያፈራች ቤተ ክርስቲያን ከመሆኗም በላይ ተቋም መሥርታ ለዘመናት የተቋምን ምንነት ያስተማረች ራሷ ሀገር የሆነች ናት፡፡

በተለይም ደግሞ መላው የአፍሪካ ሀገራት በቅኝ ግዛት በተያዙበት፣ አውሮፓውያን ኢትዮጵያንም ለመቀራመት ተስማምተው በፋሺስቱ የኢጣልያ መንግሥት አማካኝነት ሀገራችንን በወረረበት ጊዜ የንጉሱን የክተት አዋጅ ተከትሎ ሕዝቡ ለነፃነቱ እንዲዋደቅ የሀገር ፍቅር ለምእመኗ ያስተማረች በመሆኑ እና የንጉሱም ጥሪ ሀገራዊ ብቻ ሳይሆን ሀይማኖትን የመጠበቅ ጥሪም የነበረ በመሆኑ ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ ንጉሱን እንዲከተል ከማድረጓም በላይ ታቦተ ቅዱስ ጊዮርጊስን በካህናቱ አጅባ የጦር ግንባር ድረስ በመዝመት፣ ምእመኑን እና ህዝቡን በማጽናናትና ፀሎተ ፍትሀት በማድረግ በዓድዋ ጦርነት ኢትዮጵያ ሀገራችን ድል እንድትቀዳጅና ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም የነፃነት አርማ እንድትሆን በማድረግ ትልቁን የታሪክ ድርሻ እንደምትወስድ የታወቀ ሀቅ ነው፡፡
ከዚህ የድል በዓል በኋላም ኢትዮጵያ በነፃነት በቆየችባቸው ዓመታት ሁሉ ይህን የአድዋ የድል በዓል ቤተ ክርስቲያን የሰማእቱን ቅዱስ ጊዮርጊስ ታቦተ ሕግ ከመንበረ ክብሩ ወጥቶ ህዝቡን በመባረክ፣ ካህናቱና ምእመናኑ በታላቅ ምሥጋና እና መዝሙር በመላ ሀገሪቱ ስታከብረው የኖረች፤ወደፊትም እየፈጸመች የምትጸናበት አኩሪ ታሪኳ ነው፡፡

ይሁን እንጂ ይህ በዓል ላለፉት ጥቂት ዓመታት የድል በዓል መሆኑ ቀርቶ የጠብ እና የጥላቻ በዓል እየሆነ መምጣቱ ቤተ ክርስቲያንን በእጅጉ ያሳዘነ ተግባር ሆኗል፡፡ በተለይም ትላንት የካቲት ፳፫ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም በተከበረው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክብረ በዓል በቤተ ክርስቲያን ላይ የአድዋ የድል በዓልን አስታኮ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች የተፈፀመው እጅግ አሳዛኝ ድርጊትን ግን ቤተ ክርስቲያን ሰምታና አይታ በዝምታና በሀዘን ብቻ የምታልፈው ጉዳይ አልሆነም፡፡

በየካቲት ፳፫ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም የቅዱስ ጊዮርጊስ ክብረ በዓል ለማክበር ህዝቡ ከየቤቱ ተሰባስቦ ከጠዋቱ ፫፡፲፭ ላይ ታቦተ ሕጉ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ የጆርጅያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት ከመንበረ ክብሩ ወጥቶ ዑደት ካደረገና ሕዝቡን ባርኮ በዐውደ ምህረቱ ላይ ከቆመ በኋላ ሊቃውንቱ ያሬዳዊ ወረብ በማቅረብ ላይ እንዳሉ ከመንግሥት የጸጥታ መዋቅር የቤተ ክርስቲያኒቱን ተቋማዊ ልዕልናን ተላልፈው በሰሜን በኩል ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ፪ ጊዜ በተኮሱት አስለቃሽ ጭስ ምክንያት የንግሥ በዓሉ በመረበሹ በዓሉ ተቋርጦ ከጠዋቱ ፬ ሰዓት ላይ ታቦተ ሕጉ ወደ መንበሩ ተመልሷል፡፡ በዚህም ምክንያት እስከአሁን በደረሰን መረጃ መሠረት በቤተ ክርስቲያን ቅጥር ከፍተኛ ረብሻ በመፈጠሩ ምክንያት ፩ ምእመን በተተኮሰው አስለቃሽ ጭስ ታፍነው ህይወታቸውን ማጣታቸውን፣ አገልጋይ ካህናት አባቶች፣ ምእመናን እና ምእመናት ከፍተኛ የሆነ አካላዊ እና ሥነ ልቡናዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ከ፲፭ ያላነሱ የሰንበት ትምህርት ቤት አገልጋይ ተማሪዎች በደረሰባቸው ጉዳት ምክንያት ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡

ይህ ድርጊት ከተፈፀመ በኋላም መንግሥት የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብርና ልዕልና በመዳፈር በቤተ ክርስቲያን ላይ ይህን በደል የፈፀሙ የጸጥታ መዋቅር አካላትን ለሕግ ያቀርባል፣ እንደ መንግሥት ኃላፊነቱን ይወጣል ብለን ብንጠብቅም የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ቢሮ በዓሉን አስመልክቶ በዕለቱ ባወጣው መግለጫ ችግሩን የፈጠሩት አካላት ‹‹የአደባባይ በዓሉን ለመረበሽ ሲያቅታቸው በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የሚደረገውን ኃይማኖታዊ በዓል ለመረበሽ ሞክረዋል፡፡ የጸጥታ መዋቅሩ ችግሩን ለመቆጣጠር በወሰደው እርምጃ ጉዳቱን ለመቀነስ ችሏል›› ሲል የችግሩን ሁኔታ ገልጧል፡፡

በዚህ መግለጫውም ላይ አሁንም ችግሩ የሌሎች ቡድኖች እንደሆነና የቤተ ክርስቲያኒቱን በዓል የረበሸው የእነዚህ አካላት እንቅስቃሴ ነው በማለት የሰጠው መግለጫ በቦታው ላይ ከነበረው እውነታ በእጅጉ የራቀ እና ድርጊቱ የተወሰኑ ግለሰቦች ሳይሆን የመንግሥት እውቅና ያለው መሆኑን እንዲሁም መንግሥት ችግሩን ለማረም እና መፍታት ፍላጎት የሌለው መሆኑን እንድንረዳ አድርጎናል፡፡ የቤተ ክርስቲያን በዓል እንዲረበሽ እና ምእመናን ህይወታቸውን እንዲያጡ እንዲሁም እንዲጎዱ ያደረገው ከመንግሥት የጸጥታ መዋቅር የተተኮሰው አስለቃሽ ጭስ እና ጥይት መሆኑ ለሁሉም የታወቀ ሆኖ እያለ ጉዳዩን ወደ ሌላ አካል ለማላከክ የተሄደበትን ርቀት ቤተ ክርስቲያን በፍፁም የምትቀበለው አይሆንም፡፡

የመንግሥት የፀጥታ አካል በቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ አስለቃሽ ጭስ በመተኮስ ምእመናን ላይ ጉዳት ሲያደርስ እና የቤተ ክርስቲያንን ክብር ሲያጎድፍ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ በጥር ፩ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን በተሰበሰቡ ምእመናን ላይ በቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ግቢ ውስጥ አስለቃሽ ጭስ በመተኮስ ብዙ ምእመናን እንዲጎዱ የተደረገ ሲሆን በጊዜው መንግሥት ይህን ድርጊት በፈጸሙ አካላት ላይ እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ልክ እንደአሁኑ ችግሩ የሕገ ወጦች ነው በማለት ለድርጊቱ እውቅና ሰጥቶት አልፏል፡፡ በዚህ ድርጊት መንግሥት በጸጥታ መዋቅሩ ውስጥ ያሉ እና መንግሥትንና ሕዝብን እንዲሁም ተገቢ ያልሆነ ያለመግባባት የሚያባብሱትን ግለሰቦች እና አመራሮች ለይቶ እርምት ከመውሰድ ይልቅ ሕዝብና መንግሥትን ሆድና ጀርባ የሚያደርግ ተግባሩን አስፋፍቶ ቀጥሏል፡፡
1.5K views15:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-03 10:54:20
አሜሪካ ከቻይና ጋር ወደ ጦርነት መግባቷ እርግጥ ወደ መሆኑ መቃረቡን አስታውቃለች
ዋሽንግተን ከቻይና ጋር ሊኖራት ስለሚችለው ጦርነትም እቅድ በማውጣት ላይ እንደምትገኝ ነው የተነገረው።
የአሜሪካ መከላከያ ሚንስትር ዋና ጸሀፊ ክሪስቲን ዋርሙዝ ጦርነቱ አይቀሬ መሆኑን የሚያሳይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ከቢጂንግ ጋር የሚደረገውን ጦርነት በድል ለመደምደምም አሜሪካ ተጨማሪ ወታደሮቿን በእስያ ለማስፈርና የበይነ መረብ ጥቃቶችን በስፋት ለማካሄድ ስለማሰቧ ዋና ጸሃፊው ተናግረዋል።
1.4K viewsedited  07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 20:38:43
ታሪክ ራሱን ደግሟል። በዘመነ ብልፅግና በአራዳ ጊዮርጊስ በዛሬው ቀን የተፈፀመው ድርጊት እና በ2008 በዘመነ ሕወሓት በእሬቻ በዓል ላይ የተፈጸመው ተመሳሳይ ነው። ምንም ልዩነት የለውም። ሕወሓት በኢሕአዴግ የአገዛዝ ሜካፕ ስም ይንቀሳቀስ የነበረ ፋሽስት ነበር። የአሁኑ ብልፅግና ደግሞ በኢትዮጵያዊነት ሜካፕ የመጣ ነገርግን ትክክለኛው ገፅታ ኦነግ ተከሽኖ ነው። ሀገሪቱ እየገዛ ያለው በኢትዮጵያዊነት አታሎ ቤተ መንግሥት የገባ ኦነግ የሚባል ሂትለራዊ ነው። ይህን እባጭ ከሀገሪቱ ጫንቃ ላይ መንቀል ግዜ የሚሰጠው አይደለም። አለበለዚያ ኢትዮጵያ ከእጃችን ታመልጣለች።
1.6K viewsedited  17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 19:33:25
የመንግስት ኮሙኒኬሽን "ችግር ፈጣሪ" ምናምን ብሎ ቀልዷል። ንፁሃንን በአፈሙዝ መትተው ከፈረስ እንዴት እንደሚጥሏቸው ተመልከቱ። ምንም ያላደረጉ ንፁሃንን። ችግር ፈጣሪው "መንግስት" እንደሆነ ህዝብ ያውቃል።
1.5K viewsedited  16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 17:51:24
አብን የዛሬውን መንግስታዊ ሽፍትነት ያወገዘ ሲሆን ለተሰዋው የድርጅቱ አባል ሀዘኑን ገልፇል
1.5K viewsedited  14:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 17:33:57
ዛሬ ፒያሳ ጊዮርጊስ ለንግስ የመጡ ምዕመናን ላይ የተለቀቀ ጭስ ቦንብ
1.5K views14:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 08:57:00
የቴዲ አፍሮ መልዕክት!

የአክብሮት ሰላምታዬን በማስቀደም በሀገር ውስጥ እና በመላው ዓለም ለምትገኙ ውድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለ 127ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ የሚል መልዕክቴን ሳስተላልፍ በታላቅ ብሔራዊ ኩራት ነው::

      የዘንድሮውን የ127ኛው የአድዋ ድል በአልን ስናከብር ሀገራችን ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ እንደ ሀገር የመቀጠል እጣዋ ከፍተኛ አደጋ ላይ የወደቀበት ወቅት መሆኑን አፅንኦት በመስጠት እና ቀደምት አባቶቻችን በታላቅ ተጋድሎ እና መስዋዕትነት ያቆዩልንን የጋራ ሀገራችንን ከመቼውም ጊዜ በላቀ የመጠበቅ እንዲሁም ከገጠማት እጅግ ፈታኝ የህልውና አደጋ የመታደግ ታላቅ ታሪካዊ ሃላፊነት እና አደራ በኛ ትውልድ ትከሻ ላይ መውደቁን ከግምት ውስጥ በማስገባት ሊሆን ይገባል::

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ቴዎድሮስ ካሳሁን
(ቴዲ አፍሮ)
1.5K viewsedited  05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 08:44:26
አሳዛኝ ነው…

አዲስ አበባ ሚኒሊክ አደባባይ የአድዋን የድል በዓለ ለማክበር የተሰባሰቡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በአድማ በታኝ ተበትነዋል።
1.5K views05:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ