Get Mystery Box with random crypto!

ወዳጄ የሚገርም ነገር ልንገርህ ድልድይም ግርግዳም ከድንጋይ ነው የሚሰሩት፡፡ ግን ተግባራቸው ይ | Shega info

ወዳጄ የሚገርም ነገር ልንገርህ ድልድይም ግርግዳም ከድንጋይ ነው የሚሰሩት፡፡

ግን ተግባራቸው ይለያያል ድልድይ አንዱን ከሌላው ሲያገናኝ ግርግዳ ግን አንዱን ከሌላው ይለያል፡፡

.....እና ምን ለማለት ፈልጌ መሰለህ ፍላጎትህ ሀሳብህ ተሰጥኦህ አልሳካ ቢልህ በፍላጎትህና ባንተ መካከል ያለውን ዶፍ የሚያሳልፍህን ድልድይ ገንባ እንጂ ፍላጎትህን ግርግዳ ሰርተህ አትከልለው፡፡
አስተውል ያሰብከው ካልተሳካ የተስፋ መቁረጥ ግርግዳ ሳይሆን የፅናት ድልድይ ስራ፡፡

አንተ አሁን ያሰብከው ስላልሆነ የተመኘህው ስላልደረሰ የልብህን በር አትዝጋ ዛሬውኑ ተነስ ያሰብከውን ትሆናለህ
ጋዜጠኛ መምህር ሙዚቀኛ ተዋናይ ሰአሊ ኢንጂነር የህግ ባለሞያ ሌላም ሌላም
ትሆናለህ፡፡

ሰው ሀሳቡን ያክላል ስለዚህ ሀሳብህን አክብረው ውደደው ያኔ እናከብርልሀለን፡፡
ፅናት ድልድይ ነው
ተስፋ መቁረጥ ግርግዳ ነው፡፡

ሁለቱም በቃላት ይገነባሉ፡ ፡ አልችልም: አይሆንም: አይሳካም: ከንቱ ነው: የትም አልደርስም፡ እድሜዬ ሔዷል ፡ የሚለውን ግንብ አፍርስና፡፡

ይቻላል፡ ይሳካል፡ የማይሆን ነገር የለም፡ እኔ አሸናፊ ነኝ ብለህ ለውስጥህ ንገረውና ወደስኬትህ በድል ተሻገር፡፡ አንተ አሸናፊ ነህ፡፡ ሀሳብህ የእውነት እመነኝ ይሳካል ሀሳቤ ተራ ነው አትበል፡፡

ዛሬ የምታያቸው ግኝቶች በሙሉ ከዚህ በፊት የአንድ ተራ ሰው ሀሳብ ነበሩ፡፡ ዛሬ አለም ተቀበላቸው፡፡

ስለዚህ ይህንን ፅሁፍ ስትጨርስ ለውስጥህ እንዲ በል፡፡
እኔ ድልድይ እንጂ ግርግዳ አልሰራም አሸናፊ ነኝ፡ ያሰብኩት ሁሉ ይሳካል፡ እኔ ሰው ነኝ፡ ሰው አለምን ይቀይራል፡፡ እኔም ከቀያሪዎቹ አንዱ ነኝ በል፡፡

መልካም የስኬት ጊዜ ተመኘሁ!!
ሼር ጆይን ያድርጉ
Join @shegainfom