Get Mystery Box with random crypto!

#የአለም_እውነታወች ------------------------------------// የሰው ዋጋው እየ | Shega info

#የአለም_እውነታወች
------------------------------------//
የሰው ዋጋው እየቀነሰ የዶሮ እና የእህል ዋጋ እየጨመረ ሲመጣ በርትተህ ፀልይ ፡፡
የውሻ ቡችላ እየተሸጠ ሰውን ግን በነጻ የሚፈልገው ሲታጣ ዘመኑ መክፋቱን አንተም አብረህ መክፍትህን እወቀው ፡፡

ስለ ብርቅየ እንስሳት ብዙዎች እያለቀሱ ይናገራሉ በምግብ እጥረት ስለሚሞቱት ህጻናት ግን ቃል አይናገሩም ፡፡

ስለ ጠፈር ሳይንስ ብዙ ይወራል (ይሰራል) የምድር ኑሮ ግን ሲተራመስ ያስተዋለ የለም ፡፡

ስለ ወደቁ ሐውልቶች ብዙ ይባላል በየ ጎዳናው ዳር ስለወደቁት ምስኪን ህጻናት ግን ምንም አይባልም ፡፡

ስለ አየር መበከል ዓለም በሙሉ ይጮሃል ስለሰው ልጆች መርከስ ግን ዝም ይባላል ፡፡

ውሾች እና ድመቶች አልጋህ ላይ እንዲዘሉ እየፈቀድክ ድሆች ግን የግቢህ ድንጋይ ላይ እንዲቀመጡ ባለመፍቀድህ የፈጣሪህን ምህረት ጠይቅ ፡:

☞☞ ሰዎች ሆይ የሚቀድመውን ብናስቀድም የማይተወን ፈጣሪ ይከተለን ነበር ፡፡
@shegainfom