Get Mystery Box with random crypto!

የሰንበት ት/ቤት መዝሙራት

የቴሌግራም ቻናል አርማ senbetmezmurat — የሰንበት ት/ቤት መዝሙራት
የቴሌግራም ቻናል አርማ senbetmezmurat — የሰንበት ት/ቤት መዝሙራት
የሰርጥ አድራሻ: @senbetmezmurat
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.62K
የሰርጥ መግለጫ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብ መሠረት በሰ/ት/ቤት የሚዘመሩ መዝሙሮች የሚቀርቡበት ቻናል ነው

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 10:41:12 መጋደላችን ከሥጋና ከደም አይደለም። እንዴት እናሸንፋለን?

በክፉው ቀን ለመቃወም እና ለመቆም፣
የእግዚአብሔርን ጦር እቃ ማንሳት

፩- የወገብ መታጠቂያ/ ትጥቅ/ ---- እውነት
፪- ጥሩር---------------------- ፅድቅ
፫- ጫማ--------- የሰላም ወንጌል
፬- የሚንበለበል እሳት ማጥፊያ ጋሻ-- እምነት
፭- የራስ ቁር እና ሰይፍ----------------የእግዚአብሔር ቃል

ዘወትር በመንፈስ በፀሎት፣ ልመና በፅናት መትጋት።
ኤፌ 6:11-20

አቤቱ ጦር እቃህን ለማንሳት የተዘጋጀን አድርገህ፣ አልብሰህ አሰልፈን።
139 viewsedited  07:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 10:22:19
97 views07:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 10:21:14 ሐዋርያው መነኩሴ

ሐዋርያው መነኩሴ የመረጡህ ሥላሴ/2/
ዋስ ጠበቃ ሁናት ተክልዬ(ጻድቁ) ለነፍሴ
አዝ
ዳሞት ትናገረው የአንተን ሐዋርያነት
የወንጌል ገበሬ የጣኦታት ጠላት
ጸሎተኛው ቅዱስ አባ ተክለሐይማኖት
ክንፍን የተሸለምክ እንደ ሰማይ መልአክ/2/
አዝ
ብራናው ሲገለጽ ገድለ ተክለሐይማኖት
ከሰወ ልጅ ልቦና ያወጣል አጋንት
የቅዳሴው ዕጣን ሲወጣ ከዋሻው
ምድርን ይባርካል ጸሎቱ ምህላው/2/
አዝ
የኢትዮጵያን ምድር አርስከው በወንጌል
ጭንጫው ፈራረሰ ተዘራበት ወንጌል
ትላንት የዘራኽው ዛሬ ለእኛ ሆኗል
አምላከ ተክልዬ ብለን ተምረናል /2/
አዝ
ከሱራፌል ተርታ ቆመህ ስታጥን
ቅዱስ ቅዱስ ብለህ ስታመሰግን
ጸሎት ትሩፋትህ ትህትና ስግደትህ
ፆምህ ከፍ አድርጎ ሰማይ አደረሰህ/2/
አዝ
ዛፉ ሲመነገል አምላክ የተባለው
መቶሎሚ ሲያፍር ትልቅ ሰው ነኝ ያለው
የተክልዬ ጸሎት ብዙ ነው ምስጢሩ
ስድስት ክንፍ አወጣ ቢቆረጥ
አንድ እግሩ/2/



107 views07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 13:36:56 #ማርያም አርጋለች

ማርያም አርጋለች ወደ ገነት(፪)
የሰማይ መላእክት እያረጋጓት
እርሷም እንደ ልጇ ተነስታለች

የአባቷን ዳዊት ትንቢት ልትፈፅም
ወርቁን ተጎናፅፋ በቀኙ ልትቆም
ወደ አምላክ ማደሪያ ወደ ሰማያት
አረገለች በእልልታ ድንግል የእኛ እናት
አርጋለች ማርያም ተነስታለች

#አዝ

ሰማያት ይከፈት ደመናም ይዘርጋ
ዝምታም አይኖርም እመ አምላክ አርጋ
አንደበት ይከፈት ማርያምን ያመስግን
ከዘላለም ጥፋት በምልጃዋ እንድንድን
አርጋለች ማርያም ተነስታለች

#አዝ

የአምላክ ማደሪያ ቅዱስ ስጋሽ
አምላክን ያቀፉት እነዚያ እጆችሽ
ሙስና መቃብር ይዞ አላስቀራቸው
ተነስተዋል በክብር በእምነት አየናቸው
አርጋለች ማርያም ተነስታለች

#አዝ

ሐዋርያት አበው እንኳን ደስ አላችሁ
በክብር አረገች ማርያም ሞገሳችሁ
ወደ ዓለምም ውጡ ሰበኑዋን ይዛችሁ
የድንግል እርገቷን ንገሩ ተግታችሁ
አርጋለች ማርያም ተነስታለች


      
373 views10:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 15:47:34 #ቡሄ፣ #ጅራፍ_ማስጮህ፣ #ችቦ_ማብራትና #ሙልሙል_ዳቦ ሐይማኖታዊ ምስጢራቸው ምንድነው?

ደብረ ታቦር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያዕቆብን፣ ዮሐንስንና ጴጥሮስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ከወሰዳቸው በኋላ በዚያ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበትና ሙሴና ኤልያስን ጠርቶ የህያዋንና የሙታን አምላክነቱን ያሳየበት ከዘጠኙ የጌታ ዓበይት በዓለት ውስጥ አንዱ ነው። ቤተክርስቲያናችንም የተለያዩ ስርዓቶችን በመፈፀም አክብራው ታልፋለች፡፡
በደብረ ታቦር በዓል የሚፈጸሙ (#ቡሄ፣ #ጅራፍ ማስጮህ፣ #ችቦ ማብራትና #ሙልሙል_ዳቦ) ትውፊታዊ የሃይማኖት ስርዓቶች ምሳሌዎች ምን እንደሆነ እናያለን፡፡

#ቡሄ

ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ከስሙ ትርጉም እንደምንረዳው ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል ስለሆነ ብራ፣ ብርሃን ደማቅ የሚል ፍቺ ያለው ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
አንድም ቡሄ ማለት ወቅቱ የክረምት ጨለማ አልፎ የብርሃን ወቅት ስለሚመጣ ሰማይም ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቀት ስለሆነ ብራ ተብሏል፡፡
"ቡሄ ከዋለ የለም ክረም ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት እንዲሉ"
አንድም ቡሄ…..ቡኮ "/ሊጥ" ማለት ነው፡፡ በዚህ በዓል ቡኮ ተቦክቶ ዳቦ/ሙልሙል/ ተጋርሮ የሚታደልበት በዓል ስለሆነ
ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

#ሙልሙል_ዳቦ

ሙልሙል ዳቦ አመጣጡ ጌታችን ብርሃናዊ መለኮቱን በገለጠበት በዚህ ዕለት በደብረ-ታቦር አካባቢ የነበሩ ህፃናት እረኞች ቀኑ የመሸ ስላልመሰላቸው /ጌታችን በብርሃን አካባቢውን ሞልቶት ስለነበረ/ በዛው ሆነው ከብትና በጎቻቸውን እየጠበቁ ሲቆዩባቸው የሰዓቱን መግፋት የተመለከቱ ወላጆች በችቦ ብርሃን ተጠቅመው ለልጆቻቸው የሚቀመስ ሙልሙል ዳቦ ይዘው ወዳሉበት መምጣታቸውን ያሳያልና ታሪኩን እየዘከርን በዓሉን እናከብራለን፡፡
አንድም እንደ ሐዋርያት የምስራች ሲነግሩን ወንጌል ሊሰብኩልን በየደጃፋችን መጥተው "ቢሄ በሉ" የሚሉትን ታዳጊዎችን ይበሉት ዘንድ ይሰጣቸዋል ይህም መጽሐፋዊ ነው ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን በደረሳችቡት ሁሉ ተመገቡ /ማቴ 10፥12/ ብሏልና ህፃናቱም የጌታን በዓል ሊያበስሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ ሳይሆን ህፃናቱም የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ የምስራች ወንጌል ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋሪያት በገቡበት ሀገር ሁሉ አስተምረው አጥምቀው የፀጋ ልጅነትን አሰጥተው እንደሚቆዩ ሁሉ ልጆችም ዘምረው አመስግነው መርቀው ውለዱ ክበዱ የመንግስተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ብለው አመስገነው ይሄዳሉና በሐዋሪያት ህፃናቱ ይመሰላሉ፡፡

#ችቦ_ማብራት

ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥን የሚያመለክት ነው፡፡ ጌታችን በደብረ ታቦር መለኮቱን ሲገልጥ ብርሃን አካባቢውን ሞልቶት ነበርና ያንን በዘመናችን ለመግለጥ የበዓሉ ዋዜማ ማታ ችቦ አብርተን አምላካችንን እናመሰግናለን፡፡ አንድም ደግሞ የችቦ ታሪክ ከላይ እንደገለፅነው የእረኞቹ ወላጆች ይዘውት የመጡት ብርሃን ነው፡፡

#የጅራፍ_ምሳሌነት

በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ሚስጥር በእየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ሞቱ ምሳሌ ነው፡፡ በዚህ በዓል ጅራፍ መገመዱ እና ማጮሁ ሁለት አይነት ምሳሌ አለው፡፡

#የመጀመሪያው ጌታችን በዕለተ አርብ የደረሰበትን ግርፋትና ህማም እናስብበታለን፣

#ሁለተኛው ደግሞ ድምፁን ስንሰማ የባህሪ አባቱን የአብን የምስክርነት ቃልና በግርማው ሲገለጥ የተሰማውን ነጎድጓድ ያስታውሰናል፡፡ የጅራፍን ትውፊታዊ ውርስ መጽሐፋዊ ትምህርቱንና ምስጢሩን ከትውልድ ጠብቆ ማስተላለፉ ተገቢ ነው፡፡

በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከነዚህ ሚስጢር ካላቸው ትምህርቶችና ትርጓሜያቱ ከትውልድ ወደ ትውልድ በቅብብል እንደመጣልን እኛም ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ሳይለቅ ማስተላለፍ ይጠበቅብናል፡፡ የዚህ ነገር ባለ ድርሻ አካላት ደግሞ ወጣቶችና ወላጆች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በቡሄ ጨዋታ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ ፊዝና ሳቅ ይታይባቸዋል ተጫዋቾቹም ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን አይነት መልዕክት ያስተላልፋሉ። የሚብሰው አሳባቢ ነገሩ ደግሞ ኃይማኖታዊ ስርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛ መቀየሩ ነው፡፡ ስለሆነም ይህን ነገር በተለይ የነገ የሀገር ተረካቢና የቤተክርስቲያን ተተኪ የሆንን ወጣቶች ማስተካከል ይኖርብል፡፡ ወላጆችም ሕፃናት በየደጃፋችን ላይ በዓሉን ሊያበስሩ ሲመጡ አስደንግጦ ከማባረር በሚገባው መልኩ አስተምረን መርቀን ማስተናገድ ይጠበቅብናል ባህሉም እንዳይተው የበኩላችንን አደረግን ማለት ነው።

ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን
489 views12:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 13:27:33
ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ

በመጀመሪያ ሰላመ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን እያልን መዓዛ ሃይማኖት መንፈሳዊ ማኅበር በደማቅ ሁኔታ የሚከበረውን የታላቁን ገዳም ደብረ ሊባኖስ የአቡነ ተክለሃይማኖት ዓመታዊ በዓለ ንግሥ ምክንያት በማድረግ ነሐሴ 24/2014 ዓ.ም ወደ ደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም መንፈሳዊ ጉዞ አዘጋጅተናል።ስለዚህ እርስዎም የበረከቱ ተሣታፊ ይሆኑ ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር እና በጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ስም ተጠርተዋል።

መነሻ ቦታ : ፒያሳ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን
መነሻ : 12:00 ሰዓት
መመለሻ ከንግሥ በኋላ
የጉዞ ዋጋ : 350 ብር

ስልክ ቁጥር : +251926137262
+251911561321
+251960029538

የጉዞ ትኬት ሳያልቅ አሁኑኑ ይመዝገቡ
በረከቱ እንዳያልፈን በቶሎ እንመዝገብ

ትኬቱን ለማግኘት በ ከላይ ባሉት ስልኮች ወይም በቴሌግራም ግራም @wengelyohannes
554 views10:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 16:50:12
634 views13:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 16:50:10 ​ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም

የጸሎትና የተመስጦ ሕይወትዋ

ከአባት ከእናቷ ቤት ተለይታ በቤተ መቅደስ እንድትኖር ያደረገ እግዚአብሔር ነው ። የብሕትውና ኑሮን ተምራለች ። የአርምሞ ሕይወት ውሰጥ አልፋለች ። የእናት አባቷን ፍቅር ገና በሕፃንነት ዕድሜዋ ካጣች በኀላ የመራችው ሕይወት በእግዚአብሔር ፍቅር ተጠምዳ የመኖር ሕይወት ነው ። የብሕትውና የዝማሬ የጸሎትና የተመስጦ ሕይወትን ገነዘብ አደረገች ። ቅዱሳት መጻሕፍትን በማንበብ ከመዝሙራት በማጥናት ኖረች ። በቅድስት ኤልሳቤጥ ፊት የተናገረችው መዝሙር ለዚህ ነገር ማሣያ ነው ። ምክንያቱም ኸተናገረቻቸው ቃላት አብዛኛዎቹን የወሰደቻቸው በቅዱስ መጽሐፍ ከሚገኙ አንቀጾች ነው ።

አርምሞ ከመንፈሳዊነት መገለጫዎቿ መካከል አንዱ ነው ። እነደ ታናሽ ብላቴናነቷ በቤተልሔም የተመለከተችው ክብር እጅግ ታላቅ ቢሆንም ይህንን ሁኔታም ለመሸከም ከዕድሜዋ በላይ ቢሆንም ዙሪዋን በተአምራት ብትከበብም የመላእክትን የእረኞቹን ምስጋና ብታዳምጥም የጥበብ ሰዎች ወርቅ ዕጣን ከርቤን ሲገብሩለት ተቀብላ ብታከፋፍልም የኩራትን ነገር አላሰበችም ። ስለ አንዲቱም ነገር አልተናገረችም " ሁሉን ነገር በልቡናዋ ትጠብቀው ነበር " ተባለላት ። ቅዱሳት መጻሕፍት የሰጡላት ምስክር ይኼንን ነው ። / ሉቃ 2:19/ ይህ ሁሉ ነገር ለእኛ ትምህርት ይሆነን ዘንድ ተጻፈ ። እናታችንን በነገር ሁሉ እንመስላት ዘንድ ትንሽ በመናገር ብዙ በመጸለይና በማሰላሰል በተመስጦ ሕይወትም እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር ይርዳን ።ነገር ግን ለመናገር ጊዜ አለውና የምትናገርበት ጊዜ በደረሰ ጊዜ ለወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ የሚችለውን ያህል ነገረችው ። ስለ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካላት እውቀት እጅግ በጣም ጥቂቱን ክፍል ለምሳሌ የግብፅ ስደቷን ጌታ ከአይሁድ አለቆች ጋር በቤተ መቅደስ ያደረገውን ውይይትና የመሳሰሉትን ለዓብነት ይጠቀሳሉ ።

የእናታችን የቅድስት ድነግል ማርያም በረከቷ ይደርብን
588 views13:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 21:33:21 በመጨረሻም ሕፃኑ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ እንዲህ አለ፡፡ ይህን ያህል ገድል ተጋድዬ ምን ዋጋ ትሰጠኛለህ ቢለው፣ ጌታ በልብህ ያለውን ሁሉ እሰጥሃለሁ አለው፡፡ ዳግመኛም ሥጋህ በምድር ላይ እንዳይፈርስ እንዳይበሰብስ በኤልያስ ሠረገላ ላይ አኖርሃለሁ አለው፡፡ 
ስለሆነም በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያናችን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ለእናታችን ለቅድስት ኢየሉጣ እና ለሕፃኑ ለቅዱስ ቂርቆስ ያደረገውን ይህን ታላቅ ተአምር ድንቅ ሥራ በማሰብ ከዋዜማው ጀምራ እግዚአብሔርን ስታመሰግን ትውላለች ታድራለች፡፡
የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል በረከት ተራዳኢነት ከሁላችን ጋር ይኑር አሜን፡፡


እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል አመታዊ
ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!
927 views18:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 21:32:47 ቅዱስ_ገብርኤል


እንኳን ለታላቁ መልአክ ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን!!!

በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት ሐምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል አመታዊ በዓል ነው፡፡ ይህ ቀን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ቅድስት እየሉጣንና ልጇን ቅዱስ ቂርቆስን ከሞት አደጋ እንደታደገበት የሚታሰብበት ዕለት ነው። የሐምሌ 19 ስንክሳርና የሐምሌ ወር ድርሳነ ገብርኤል እንዲህ ተርከውታል፡፡

በዘመነ ሰማእታት ከሐድያን ነገሥታትና መኳንንት በክርስቲያኖች ላይ መከራ አጽንተውባቸው ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙዎች ሰማእትነትን ሲቀበሉ የተቀሩት አገር ጥለው ተሰደዱ። እየሉጣም የሦስት ዓመት ህፃን የነበረውን ቅዱስ ቂርቆስን ይዛ ሸሸች በዚያም የሸሸችውን መኮንን አገኘችው ሰዎችም ነገር አሰሩባት ወደእርሱ አስቀረባት እና ስለ አምልኮ ጠየቃት እርሷም መኮንን ሆይ ዕድሜው ሦስት አመት የሆነው ህፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እሱን ጠይቅ አለችው፡፡ 

ህፃኑም ወዳለበት ጭፍራውን ልኮ ወደእርሱ አስመጣው ህፃኑም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና አንተ ደስተኛ ህፃን ሆይ እንዴት ነህ አለው፡፡ ህፃኑም መልሶ አዎ ለኔ ተጠብቆልኛል ላንተ ግን ሐዘንና ለቅሶ ጥርስ ማፋጨትም ነው፡፡ መጻሐፍ ለዝንጉዎች ተድላ ደስታ የላቸውም ብሏል እና አለው፡፡ እግዚአብሔር ኃይልና ንግግርን ሰጥቶታልና ብዙ ተናገረ በዚያም ያሉትን እስካስደነገጣቸው ድረስ ንጉሱን መኳንንቱንና ጣኦታቱን ረገማቸው፡፡ከብርታቱም የተነሳ አደነቁ፡፡ 

መኮንኑም በአፈረ ጊዜ በያይነቱ በሆነ ስቃይ ታላላቆች የማይችሉትን ታላቅና አስጨናቂ የሆነ ስቃይን አሰቃየው እናቱንም ከእርሱ ጋር አሰቃያት፡፡ እግዚአብሔርም ያለ ምንም ጉዳት ያነሳቸው ነበር፡፡ ብዙዎች አህዛብም ይኸንን አይተው አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስም አምነው በሰማእትነት አረፉ፡፡ የሰማእትነትንም አክሊል ተቀበሉ፡፡ በህፃኑም ላይ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አደረበት፡፡ ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶችንም አደረገ ብዙዎች በሽተኞችንም አዳናቸው፡፡ 
በዚያም ፍላቱ ወደላይ በሚዘል ብረት ጋን ውስጥ ለመጨመር ሲወስዷቸው የነዚህን ቅዱሳን አሟሟት ያዩ ዘንድ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲሰበሰቡ አዘዛቸው፡፡ በዚህን ጊዜ ቅድስት እየሉጣ የፍላቱን ጩኸት በሰማችና ባየች ጊዜ ተሸበረች፡፡ ተዘጋጅቶላት ከነበረው ክብር ልታፈገፍግ ሞከረች፡፡ ልጇ ቅዱስ ቂርቆስ ግን እናት ሆይ ከዚህ የብረት ጋን ግርማ የተነሳ አትፍሪ ድንጋጼም አይደርብሽ አናንያንና አዛርያን ሚሳኤልንም እግዚአብሔር ከእቶነ እሳት እንዳወጣቸው ሁሉ እኛንም ከዚህ ከብረት ጋን ሊያወጣን ችሎታ ያለው መሆኑን አትጠራጠሪ፡፡ 

እናት ሆ ከዚህ ከሚያልፈው ዓለም ጭንቅና መከራ ለመዳን ስትይ በማያልፈው ዘላለማዊ እሳት ለመቀጣት ትመርጫለሽን ይኽስ አይሆንም ይቅርብሽ፡፡ በአሁኑ ጊዜ እግዚአብሔር በመካከላችን አለና ይረዳናል፡፡ እናት ሆይ ሶስናን ከእደ ረበናት /መምህራነ አይሁድ/ ዳንኤልን ከአፈ አናብስት ያዳነ እርሱ እኛንም ከጋን ፍላት ያወጣናል፡፡ ይልቁንም እግዚአብሔር በዚህ የብረት ጋን ውስጥ ግዳጃችንን ልንፈጽም ፈቅዶ ከሆነ ኢዮብ ንብረቱንና ገንዘቡን ልጆቹንና ሚስቱን በመጨረሻም የተፈጥሮ አካሉን ባሳጣው ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ እግዚአብሐር ሰጠ እግዚአብሔር ነሳ እግዚአብሔርም እንደወደደ አደረገ ከማለት በስተቀር ምንም የተናገረው ነገር እንደሌለ ሁሉ እኛም የሱን ዓላማ በመከተል ይኽንን መከራ ልንታገስ ይገባናል፡፡ 

ነገር ግን እናቱ በዚህ ምክር ልትጽናና ባለመቻሏ ቅዱስ ቂርቆስ ዐይኑን ወደ ሰማይ አቅንቶ አቤቱ አምላክ ሆይ ይችን ባሪያህን ከርስትህ የምትለያት ከሆነ ከባለሟልነትህ መጽሐፍ ፋቀኝ፤ አቤቱ አዝመራውን አቃጥለ ፍሬውን ልትባርክ ትወዳለህን ይኽን እንዳታደር ግን ቸርነትህ ትከለክልኸለች አቤቱ እንጨቱን ቆርጣችሁ አንድዱት ቅጠሉን ግን ጠብቁት ብለኽ ልታዝ መለኮታዊ ባሕሪህ አይደለም፡፡ ነገር ግን እንጨቱንም ቅጠሉንም በአንድ ጠብቁት ብለኽ ታዝዛለኽ እንጂ፡፡ እንግዲህ በዚህ ምክንያት ይኽንን ያየ ሁሉ ማዳን የሚችል አምላክ ቢኖራቸውስ ኖሮ ከእሳት ባልሸሹም ነበር ብሎ አይጠራጠር፡፡ 

አቤቱ ዲያብሎስም ከባለስልጣኑ ይልቅ እኔ በረታሁ ቅዱሳኖቹንም ድል ነሳኋቸው ብሎ እንዳይመካ ከመንጋውም አንድ በግ ቀማው በማለት እንዳይደነፋ ለእናቴ ጽኑ የሆነ ኃይለ መንፈስ ቅዱስን ስጣት ብሎ በጸለየ ጊዜ ዲያብሎስ ከእየሉጣ አጠገብ ብን ብሎ ጠፋ፡፡ ከዚህ በኋላ ቅድስት እናቱ በሰማያዊ መንግሥት አባት የሆንከኝ ልጄ ሆይ ጌታኽ ኃይልን ሰጥቶኛልና የሚጠብቀንን ገድላችንን ፈጽመን ድል እናድርግ እነሆ በብረት ጋን ውስጥ የሚነደውን እሳት በማይበት ጊዜ በለምለም /በምንጭ/ ላይ እንደሚወርድ ጠል ሆኖ አይቸዋለሁና አለችው፡፡

ዳግመኛም መስፍኑ ሐሳቡ ሳይሳካለት ስለቀረ 14 የሾሉና የጋሉ የብረት ችንካሮች አምጥተው ሰባቱን በእናቱ በኢየሉጣ አካል ሰባቱን በራሱ በቂርቆስ አካል ማለት ሁለቱን በጆሮዎቹ ሁለቱን በዐይኖቹ ሁለቱን በአፍንጫዎቹ አንዱን በልቡ ይቸነክራቸው ዘንድ ጭፍሮቹን አዘዘ፡፡ ዳግመኛም የህፃኑን የእራስ ቆዳ ገፈው እሳት ውስጥ ይጨምሩ ዘንድ አዘዘ፡፡ 

አሁንም መልአኩ መጥቶ ይህንን መከራ ከእርሱ አራቀለት፡፡ ቀጥሎም በመቃን ውስጥ ጨምረው በገመድ እንዲጎትቱት አዘዘ፡፡ በዚህም ጊዜ መልአኩ አዳነው፡፡ ሕዝቡም ይህንን ሁሉ ተአምር ባዩ ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገኑት ቅዱስ ገብርኤልንም አከበሩት፡፡ ቅዱስ ቂርቆስና ቅድስት እየሉጣ ብዙ መከራ ከተቀበሉ በኋላ ጥር 15 በሰይፍ ተመትተው ስማትነትን ተቀብለዋል። 

የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤል ፣ ቅዱስ ቂርቆስና የእናቱ የቅድስት እየሉጣ ተራዳኢነት ጸሎት አይለየን። ከዚህ በኋላ ሕፃኑን አስፈልገው ቢጠይቁት ነቢዩ ዳዊት የተናገረው ኃይለ ቃል መንፈስ ቅዱስ ተገልጾለት፤ ‹‹የአሕዛብ ጣዖታት የወርቅና የብር የሰው እጅ ሥራዎች ናቸው፡፡ የሚታመኑባቸውም ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁኑ›› መዝ. ፻፴ በማለት ሲዘልፏቸው አገር ገዥው ሰምቶ ተቆጣና የብረት ጋን አስመጥቶ ውኃ ሞልቶ ከዕቶን እሳት ላይ ጥዶ ልዩ ልዩ ማገዶዎች በመጨመር ነበልባሉ ከመጠን በላይ ሆነ፡፡ የብረት ጋኑም ድምፅ እንደ ክረምት መብረቅና ነጎድጓድ እስኪያስፈራ ድረስ አስነድዶ ሕፃኑን ከነእናቱ ወስዳችሁ ጨምሩአቸው ብሎ አዘዘ፡፡ 

‹‹ጌታ ሆይ! የወይኑን ፍሬ ስትሻ ግንዱን ታጠፋለህን? እንደዚህስ ሁሉ እኔን አድነህ እናቴን ታጠፋታለህን?›› ብሎ በጸለየጊዜ መንፈስ ቅዱስ አደረባትና መንግሥተ ሰማያትን በዓይነ ሥጋ እንድታይ አደረጋት፡፡ ከዚህ በኋላ ፍርሃቱ ለቀቃትና ‹‹ልጄ ሆይ! ከዛሬ ጀምሮ መምህሬ፣ አባቴ፣ መካሪዬ እልሃለሁ እንጂ ልጄ አልልህም›› ብላ በጭካኔ ከልጅዋ ጋር ወደ ፈላው የብረት ጋን ገባችበት፡፡ 

በዚህ ጊዜ ሕፃኑ ቂርቆስ አናንያን፣ አዛርያንና ሚሳኤልን ያዳነ አምላክ ያድነናል ያለውን ቃል ለመፈጻም እግዚአብሔር አምላክ መልአኩ
ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው፡፡ መልአኩም በትእምርተ መስቀል እሳቱን ቢባርከው እንደ በረዶ ቀዝቅዞላቸዋል፡፡ በመልካቸውም እንደ ፀሐይ አበራ፡፡ ከእግር ጥፍራቸው እስከ ራስ ጠሩራቸው አንድም ሳይጎዳቸው በደህና ወጡ፡፡
996 views18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ