Get Mystery Box with random crypto!

ሐዋርያው መነኩሴ ሐዋርያው መነኩሴ የመረጡህ ሥላሴ/2/ ዋስ ጠበቃ ሁናት ተክልዬ(ጻድቁ) ለነፍሴ | የሰንበት ት/ቤት መዝሙራት

ሐዋርያው መነኩሴ

ሐዋርያው መነኩሴ የመረጡህ ሥላሴ/2/
ዋስ ጠበቃ ሁናት ተክልዬ(ጻድቁ) ለነፍሴ
አዝ
ዳሞት ትናገረው የአንተን ሐዋርያነት
የወንጌል ገበሬ የጣኦታት ጠላት
ጸሎተኛው ቅዱስ አባ ተክለሐይማኖት
ክንፍን የተሸለምክ እንደ ሰማይ መልአክ/2/
አዝ
ብራናው ሲገለጽ ገድለ ተክለሐይማኖት
ከሰወ ልጅ ልቦና ያወጣል አጋንት
የቅዳሴው ዕጣን ሲወጣ ከዋሻው
ምድርን ይባርካል ጸሎቱ ምህላው/2/
አዝ
የኢትዮጵያን ምድር አርስከው በወንጌል
ጭንጫው ፈራረሰ ተዘራበት ወንጌል
ትላንት የዘራኽው ዛሬ ለእኛ ሆኗል
አምላከ ተክልዬ ብለን ተምረናል /2/
አዝ
ከሱራፌል ተርታ ቆመህ ስታጥን
ቅዱስ ቅዱስ ብለህ ስታመሰግን
ጸሎት ትሩፋትህ ትህትና ስግደትህ
ፆምህ ከፍ አድርጎ ሰማይ አደረሰህ/2/
አዝ
ዛፉ ሲመነገል አምላክ የተባለው
መቶሎሚ ሲያፍር ትልቅ ሰው ነኝ ያለው
የተክልዬ ጸሎት ብዙ ነው ምስጢሩ
ስድስት ክንፍ አወጣ ቢቆረጥ
አንድ እግሩ/2/