Get Mystery Box with random crypto!

የሰንበት ት/ቤት መዝሙራት

የቴሌግራም ቻናል አርማ senbetmezmurat — የሰንበት ት/ቤት መዝሙራት
የቴሌግራም ቻናል አርማ senbetmezmurat — የሰንበት ት/ቤት መዝሙራት
የሰርጥ አድራሻ: @senbetmezmurat
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.62K
የሰርጥ መግለጫ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትና ደንብ መሠረት በሰ/ት/ቤት የሚዘመሩ መዝሙሮች የሚቀርቡበት ቻናል ነው

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-05-26 20:30:27
535 views17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 20:30:27 ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት በአማልጀነቱ እና በተራዳኢነቱ የሚታወቀው ቅዱስ ገብርኤል ነው ። ነገደ መላእክትንም ሆነ ደቂቀ አዳምን የሚያረጋጋ መልአክ በመሆኑ መልአከ ሰላም በመባል ይታወቃል። የመላው ሰው ልጆች ረዳት ስለሆነ ምንግዜም አግብርተ እግዚአብሔር ቅዱሳንን ሲረዳ የሚኖር የ እግዚአብሔር ባለሟል የሰው ልጆች ወዳጅ ነው ። የ ቅዱስ ገብርኤል አማላጆነት በረከት እና ረድኤት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን ።
502 views17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 15:40:44 የርኩሳን መናፍስት ስብስብ

በሰይጣን የሚመሩት ርኩሳን መናፍስት ንስሓ በገቡትና በአማኞች ላይ ስለሚከፍቱት ውጊያ ዕቅድ ለማውጣት ይወያዩ ዘንድ ጉባኤ ተቀመጡ ። በዚህ ጊዜ ሊቀ መንበሩ አማኞችን ሊያጠፋ የሚያስችል እጅግ አዲስ ዕቅድ እንዲያቀርቡ አባላቱን ጠየቀ ።

አንደኛው ርኩስ መንፈስ እንዲህ አለ : " #የእግዚአብሔርን ሕልውና እንዲጠራጠሩ እናድርጋቸው ። "

ሁለተኛው " መጽሐፍ ቅዱስን እንዲጠራጠሩ እናድርጋለው ። " አለ ።

ሌላኛው ደግሞ " ዘላለማዊነትን እንዲጠራጠሩ እናድርጋቸው ። " አለ ።

አራተኛው " በምኞትና በፈተናዎች እናታላቸው ። " ብሎ ተናገረ ።
እነዚህን የሚሙስሉ አሳቦች ከየአቅጣጫው መወርወራቸው ይቀጥል እንጅ ሊቀ መንበሩን አንዱንም አሳብ ሊያጸድቅ አልፈለገም ፤ ሁሉም የቆዩና ከዚህ በፊት #የተጠቀሙባቸው_ዕቅዶች_ነበሩና ። ሁሉም እርግጠኛ የሆኑ ውጤቶች ሊያቀርቡ ስላልቻሉ ብዙ ሰዎች ከእነርሱ እያመለጡ ወደ እምነት ጎራ መግባት ቻሉ ።

አንድ የሚሻል ልምድ ያለው ርኩስ መንፈስ የሰው ልጆችን ሊያጠፋ የሚችል አንድ አዲስ እና ስኬታማ ዕቅድ ለማዘጋጀት ኃላፊነቱን ከወሰደ በኋላ እንዲህ በማለት ተናገረ ፦ " ስለ #እግዚአብሔር ሕልውና ፤ ስለ መጨረሻው ፍርድ እውነትነት ፤ ስለ ዘላለማዊው ቅጣት ፤ ስለ ገነትና ስለ ሲዖል መኖር መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ነገር ሁሉ ትክክለኛ እና እውነት መሆኑን አጉልተን እናሳያቸው ። ከዚህ በተጨማሪ ንስሓ አስፈላጊና መቅረት የማይገባው ጉዳይ መሆኑንም እናሳያቸው ..." በዚህ ጊዜ እያንዳንዱ ርኩስ መንፈስ እጅግ በቁጣ ተሞልቶ ንግግሩን ከመጨረሱ በፊት አቋረጡትና ዕቅዱን በውግዘት ውድቅ አደረጉበት ። ተቃውሞአቸው እጅግ መራር ነበር ።
በዚህ ጊዜ ሊቀ መንበሩ ርኩስ መንፈሱ እቅዱን ገልጾ እስኪጨርስ ድረስ እንዲረጋጉ ምልክት ሰጣቸው ።

ይህን ተንኮል አዘል አሳብ ያቀደው ርኩስ መንፍስ ንግግሩን እንዲህ በማለት ቀጠለ ፦ " እነዚህን ነገሮች በሙሉ ለሰው ልጆች እጅግ አጉልተን ስናሳያቸው ከእኛ ጋር ተደላድለው መኖር ይጀምራሉ ፤ በምክራችንም ይታመናሉ ። በዚህ ጊዜ ወዲያውኑ ወደ ንስሓ የሚያደርሷቸውን ቀና እርምጃዎች መራመድ ሲጀምሩ ንስሐቸውን ለጥቂት ጊዜ ምናልባትም እስከ ነገ ድረስ እንዲያቆዩት እናድርጋቸው ። ይህን የምናደርገውም ኃጢአትን እስከሚሰናበቱትና ፍላጎታቸውን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲያረኩ ነው ። በዚህ መንገድ ንስሓ ለመግባት ከተዘጋጁ በኋላ እስከ ነገ ድረስ እናቆየው እያሉ ይቆያሉ ። በመጨረሻም ቀናቶቻቸው ስለሚጠናቀቁ ንስሓ የመግባት ዕድሉን ከነጭራሹ ያጡታል ። "

እያንዳንዳቸው ብድግ ብለው ርኩሱ ጥበቡን በማድነቅ አጨበጨቡለት ። ታውቃላችሁ? ! ከዚያን ጊዜ በኋላ ሰዎች በቡድንም ሆነ በነጠላ በኃጢአት መውደቅ ስለ ጀመሩ መጨረሻ ወደሌለው ጥልቅ ጉድጓድ ይወድቁ ጀመር ። ይህ ሊደርስባቸው የቻለውም #በእግዚአብሔርና በመጽሐፍ ቅዱስ ወይም በዘላለማዊነት ስላላመኑ አይደለም #ንስሓ_የመግባት_ዕድሉን_ካገኙት_በኋላ_ለነገ_በማለት_ስላዘገዩት_እንጂ ።

ወንድሜ ሆይ ፦ እንዲህ ያለውን አጭበርባሪ ወጥመድና አረመኔያዊ ብልጠት ተጠንቀቀው!! " ዛሬ ድምፁን ብትሰሙት ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ. .." [ዕብ 4:7 ] የሚለውን የመጽመፍ ቅዱስ ቃል በውስጥህ ሸሽግ ።
አንተ ዛሬ ልትሞት ስለምትችል ንስሓህን እስከ ነገ ድረስ አታዘግየው ።
ወይም ደግሞ ነገ ሊመጣ ቢችልም ባተሌ ልትሆንና ብዛት ባላቸው ነገሮች ልትወጠር ትችላለህ ። ወይም ደግሞ ነገ ልብህ ሊደነድንና የመንፈስን አነሳሽነት ልታጣው ትችላለህ ።
ለንስሓ እጅግ ተመራጩ ጊዜ አሁን ነው ፦ " በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳን ቀን ረዳሁህ ይላልና ፤ እነሆ ፦ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው እነሆ ፦ የመዳን ቀን አሁን ነው ። " [ 2ኛ ቆሮ 6:2]

ንስሓ ትገባ ዘንድ #እግዚአብሔር አምላክ ጸጋውን ያድልህ ።
575 views12:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 17:52:17
589 views14:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 22:14:21
እንኳን ለ ግንቦት ልደታ ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የልደት ቀን አደረሳችሁ ።
796 views19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 22:10:47 #ዮም_ፍስሐ_ኮነ

ዮም ፍስሐ ኮነ (፪)
በእንተ ልደታ ለማርያም

በባርነት ሳለን
ኃጢአት በአለም ነግሳ
በድንግል መወለድ
ቀረልን አበሳ
እግዚአብሔር መረጠሸ
ልትሆኚው እናቱ
ይኸው ተፈፀመ
የዳዊት ትንቢቱ
#አዝ
የሔዋን ተስፋዋ
የአዳም ዘር ህይወት
የኢያቄም የሐና
ፍሬ በረከት
ምክንያተ ድኂን
ኪዳነምህረት
ድንግል ተወለደች
የጌታዬ እናት
#አዝ
በሔዋን ምክንያት
ያጣነውን ሰላም
ዛሬ አገኘነው
በድንግል ማርያም
የምስራች እንበል
ሀዘናችን ይጥፋ
ተወልዳለችና
የአለም ሁሉ ተስፋ

791 views19:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 00:33:08
1.3K views21:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 14:54:52
870 views11:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ