Get Mystery Box with random crypto!

ያልታደለች ችግኝ....! ችግኝ ተተክሎ ዛፍ እንጀሚሆን እንጂ፣ ችግኝን እንዴት እንደሚንከባከቡት | Semeredin Shemsee

ያልታደለች ችግኝ....!

ችግኝ ተተክሎ ዛፍ እንጀሚሆን እንጂ፣ ችግኝን እንዴት እንደሚንከባከቡት በውል የማያውቀው ህፃን፣የተከላትን የዛፍ ችግኝ ለማየት ጥዋት ይወጣና ውኃ ካጠጣት በኃላ አጠገቧ ቁጭ ብሎ ሲያያት ውሎ ሲያያት ያመሻል።እንዲህ የመጨነቁና የመጠበቡ ምስጢር ደግሞ አባቱ ይኽቺን ችግኝ ተክለህና አጽድቀህ ጠብቀኝ ብሎት ለስራ ወደ ክፍለ አገር ስለሄደ ነበር።እናት የልጇን እንግዳ ነገር ስለለመደችው የት ዋልህ እያለች አታስጨንቀውም፤ ብቻ ጀምበሯ ማዘቅዘቅ ስትጀምር ልጇን ለእራትና መኝታ ትጠራዋለች። ይኽ እየሆነ ሳለ በአላህ ቸርነት ችግኟ ጸደቀች፤ አባትም ከሄደበት አገር በሰላም ተመለሰና ለልጁ አደራ ሰጥቶት የሄደው የችግኟ ነገር ከምን እንደደረሰ ለማወቅ ሽቶ ''ችግኝህ እንዴት ሆነች የእኔ ጎበዝ?'' ሲል ጥያቄ አቀረበ። ገና ከጅማሬው የችግኝን ጠባይ ያልተረዳው የዋሁ ህፃን ፊቱ በደስታ እየፈካ አባቱ የሰጠውን ሃላፊነት በሚገባ እንደተወጣ ለማሳየት ''ቆይ ላሳይህ'' አለና ወደ ውጪ በረረ። አባት ለነገሩ ትኩረት ሳይሰጠው ከባለቤቱ ጋር ወግ ይዞ እያለ ህፃኑ በፍጥነት ተመልሶ ''ይኽው አባቴ ችግኟ ጸድቃለች'' አለ ችግኟን ነቅሎ አምጥቶ ለአባቱ እያሳየ።ያልታደለች ችግኝ....።ሁሌም ቢሆን አንድን ስራ ለምን እንደምንሰራው ምክናያቱን ለማን እንደምንሰራው ማወቅ ይኖርብናል።ይኽ ደግሞ ስራችን በገዛ ራሳችን እንዳይበላሽና በስራችን ተስፋ እንዳንቆርጥ ይረዳናል።በተጨማሪም ስራችንን እናከብረውና እንጠብቀው ዘንድ ያግዘናል። ይኽ አጭር ታሪክም የሚጠቁመን ይህንኑ ነው።በተልይም ችግኙን እንደነቀለው እንደዚህ ዐላዋቂ ህፃን እምነታችንን የተውን ባህላችንን የጣልን በአጠቃላይ የምንሰራው የጠፋብን ካለን ልብ በሉ ይለናል።