Get Mystery Box with random crypto!

Semeredin Shemsee

የቴሌግራም ቻናል አርማ semer1536 — Semeredin Shemsee S
የቴሌግራም ቻናል አርማ semer1536 — Semeredin Shemsee
የሰርጥ አድራሻ: @semer1536
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 213
የሰርጥ መግለጫ

✔ተገቢ ያልሆነ ትችት በተዘዋዋሪ ምስጋና መሆኑን አምናለሁ።

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-04 01:10:55 But be careful, too, that you are open to any legitimate possibilities for making a deal that come your way. If an opposition leader states publicly that some of your ideas have merit, that could be the olive branch you've been waiting for to achieve peace, and also reach some of your goals.
7 views22:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 01:10:55 In community work, there's almost always someone opposed to whatever it is you're doing. Even if your goal is something everyone can agree on, there will be those who disagree with your methods for achieving it. When your opposition starts fighting your efforts, it's best to be familiar with what tactics they might use to do so and how your group might most effectively respond.

WHAT ARE SOME GENERAL WAYS TO FIGHT THESE TACTICS?

There are a variety of tactic-specific ways to deal with each of these forms of attack. Some strategies that apply no matter what tactic is being used include:

➢ UNDERSTAND YOUR OPPONENT AND HIS/HER/THEIR STRATEGY

If knowledge is power, ignorance is weakness. An opponent you understand is much weaker than an opponent whose every move baffles you. Understand your foe's beliefs, background, and position. This will put you in a stronger position to respond to attacks. It can also increase your organization's image as an intelligent, rational group. What does your opponent believe and want?

➢TURN NEGATIVES INTO POSITIVES

As the saying goes, when the opposition gives you lemons, make lemonade. The ability to turn any negatives you are given into positive situations is a very powerful ability for your organization to have.

➢ SET THE AGENDA

If you are meeting with the opposition, your organization should establish or influence the agenda. This way, it will be your group that controls the meeting; you, and not the opposition, will have the chance to be on the offensive, which is always the stronger position to be coming from. Further, if you allow the opposition to set the agenda, chances are good that some of the important points you wanted to discuss won't even be brought up.The opposition will naturally use their "home court advantage" to talk about their strengths, rather than points they may be weaker on.

➢ PUBLICLY STATE THE OPPONENT'S STRATEGY

This makes the opposition's tactics seem clearer to all of the members in your group (and therefore easier to fight). It is also a great way to win sympathy and respect from the general public. This is particularly true if you are a relatively small group fighting a larger agency or corporation in a just cause. Everyone wants to root for the underdog; giving your battle a "David and Goliath" image can do a great deal to further your cause.
Some of the information you should consider making public:

What your opponent has said or done

Why it is untrue or unjust

What is true and/or equitable

How the truth affects you and your opponent



➢ KEEP YOUR OPPONENTS OFF BALANCE

Don't rely on the same approaches all of the time. Instead, constantly take the opposition by surprise. This can not only can help in your current battle, it will help your group avoid stagnation. If you tried to privately negotiate a solution last time you butted heads with the opposition, this time you might go public with the situation. Or, you might ask for a third party to act as a facilitator. Be creative, and don't be afraid to try something new. Leaving your opponent in a cloud of uncertainty of what your tactics will be this time is a powerful strategy on it's own, and gives you an advantage over the opposition before you even start.

➢ LEARN FROM THE PAST

If an organization has a history of responding in a certain manner, chances are that's how they will respond again. Know the history including the preferred tactics of the people you are battling - and know how your organization has traditionally responded. That way, you'll be thoroughly prepared for what is likely to happen, and you'll be more likely to avoid any pitfalls you've fallen into in the past.


➢ BE WILLING TO COMPROMISE

Your opponents may be willing to work with you in good faith, particularly if you have run a good advocacy campaign. Keep an eye open for situations that might turn into a chance to work together. Be careful that by saying cooperation, your opponents don't really mean capitulation to their interests.
8 views22:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 21:04:31 ጥላህን አንሣ

ሰውዬው አሳ በማጥመድ ሙያው ተጠቅሞ የሚያጠምዳቸውን አሳዎች በመሸጥ ይተዳደራል።ዘውትር ማልዶ ይኽንኑ ስራውን ስያከናውን ከእለታት አንድ ቀን ግን አሳዎች ወደ መቃጥኑ አልቀርብም በማለታቸው እጅጉን አዘነ።መቃጥኑን እያነሳ አንዴ ወደቀኝ አንዴም ወደ ግራ እያደረገ ደጋግሞ ቢጥለውም ትርፉ ድካም እንጂ አንድም የተያዘ ዓሳ አልነበረም።ከውኃው ዳር ሆነው የሰውዬውን ሁኔታ ሲከታተሉ የነበሩ አንድ የእድሜ ባለጸጋ ሰው ጠጋ ብለው ተገቢውን ሰላምታ ካቀረቡለት በኋላ ስለሰራው ጠየቁት እሱም ''ኧረ አባቴ የዛሬውስ አይወራ ይኸው እዚህ ከተገኘሁ ብዙ ሰዓት ቢያልፍም እስካሁን ግን አንድም ዓሳ ወደ መቃጥኑ ብቅ አላለም፤እኔ የምለው ዓሳዎቹ ዛሬ የት ገቡ?'' አለ ብስጭት ብሎና ተማሮ።ሽማግሌው ወደ ሰውዬው ጠጋ ብለው ''ዓሳዎቹማ የትም አልሄዱም ነገር ግን አንተ ጥላህን ጥለህባቸው በየት በኩል ይምጡ፤ትሰማኛለህ ወዳጄ ዓሳዎቹ ወደመቃጥኑ እንዲመጡ ከፈለክ ጥላህን አንሳላቸው'' አሉት ይባላል።
19 views18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 01:04:06 ድሮ ነው አሉ፤ ሰውዬው ለአሽከራቸው ክፉ ነበሩ። በተለይ ሲበሉ ሰው እንዲያያቸው አይፈልጉም።አሽከራቸው ሁል ጊዜ ቀን አደግድጎ ማታ መብራት ይዞ ይመግባቸዋል።

ታዲያ አልፎ አልፎ ያጎርሱኛል በሚል ተስፋ ዞር እያለ ቢያያቸው እሳቸው እንኳንስ ሊያጎርሱት ቀርቶ ለምን ዞር ብሎ ያየኛል ሲሉ በዐይነ መዓት እያዩት ጥርግ አድርገው ይበላሉ ።አሽከራቸው እንደ አህያ ቢሰራላቸውም፣ እሳቸውን አደግድጎ ቆሞ ሲመግብ መብራቱን ይዞ ፊቱን አዙሮ መቆም ሲገባው ''ምን አባቱ እየዞረ ያየኛል '' በሚል ብቻ ይጠሉት ነበር።

አንድ ቀን ይሄው አሽከራቸው በጠና ይታመምና ወደ ሀኪም ቤት ይዘውት ይሄዳሉ። ከምርመራው በኃላ መርፌ መወጋት ስለነበረበት ሀኪሙ መርፌውን ወደ ታፋው ሲያመቻች ሰውዬው ከኃላ ቆመው ዶክተሩን ''ዶክተር እባክህን ታፋውን ሳይሆን ማጅራቱን ውጋልኝ '' ይሉታል ።ሀኪሙም በሰውዬው ንግግር ቢገረምም እንደማይሆን ነገራቸው ።

ሰውዬው አሁንም ማጅራቱን እንዲወጋላቸው ይለምናሉ ፣ሁለቱ ሲከራከሩ አሽከርየው ጣልቃ ይገባና ''ዶክተርዬ ተወው አትከራከር፤ ያመመኝ ማጅራቴን ባይሆንም ለጌቶች ሲባል ማጅራቴን ውጋኝ'' አለ ይባላል ።

ስንቶቻችን ይሉኝታ በሚሉት ገመድ ተተብትበን የበላንን ሳይሆን ያልበላንን ለማከክ ተገደን እንኖር ይሆን ? ግን ለም ? እኛ ስለራሳችን መኖር ሲገባን ከራሳችን በላይ ስለራሳቸው ብቻ ሊያኖሩን የሚሞክሩትን ሁሉ ዝም ማለት ተገቢ አይመስለኝም ።
22 views22:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 12:49:09
ያልታደለች ችግኝ....!

ችግኝ ተተክሎ ዛፍ እንጀሚሆን እንጂ፣ ችግኝን እንዴት እንደሚንከባከቡት በውል የማያውቀው ህፃን፣የተከላትን የዛፍ ችግኝ ለማየት ጥዋት ይወጣና ውኃ ካጠጣት በኃላ አጠገቧ ቁጭ ብሎ ሲያያት ውሎ ሲያያት ያመሻል።እንዲህ የመጨነቁና የመጠበቡ ምስጢር ደግሞ አባቱ ይኽቺን ችግኝ ተክለህና አጽድቀህ ጠብቀኝ ብሎት ለስራ ወደ ክፍለ አገር ስለሄደ ነበር።እናት የልጇን እንግዳ ነገር ስለለመደችው የት ዋልህ እያለች አታስጨንቀውም፤ ብቻ ጀምበሯ ማዘቅዘቅ ስትጀምር ልጇን ለእራትና መኝታ ትጠራዋለች። ይኽ እየሆነ ሳለ በአላህ ቸርነት ችግኟ ጸደቀች፤ አባትም ከሄደበት አገር በሰላም ተመለሰና ለልጁ አደራ ሰጥቶት የሄደው የችግኟ ነገር ከምን እንደደረሰ ለማወቅ ሽቶ ''ችግኝህ እንዴት ሆነች የእኔ ጎበዝ?'' ሲል ጥያቄ አቀረበ። ገና ከጅማሬው የችግኝን ጠባይ ያልተረዳው የዋሁ ህፃን ፊቱ በደስታ እየፈካ አባቱ የሰጠውን ሃላፊነት በሚገባ እንደተወጣ ለማሳየት ''ቆይ ላሳይህ'' አለና ወደ ውጪ በረረ። አባት ለነገሩ ትኩረት ሳይሰጠው ከባለቤቱ ጋር ወግ ይዞ እያለ ህፃኑ በፍጥነት ተመልሶ ''ይኽው አባቴ ችግኟ ጸድቃለች'' አለ ችግኟን ነቅሎ አምጥቶ ለአባቱ እያሳየ።ያልታደለች ችግኝ....።ሁሌም ቢሆን አንድን ስራ ለምን እንደምንሰራው ምክናያቱን ለማን እንደምንሰራው ማወቅ ይኖርብናል።ይኽ ደግሞ ስራችን በገዛ ራሳችን እንዳይበላሽና በስራችን ተስፋ እንዳንቆርጥ ይረዳናል።በተጨማሪም ስራችንን እናከብረውና እንጠብቀው ዘንድ ያግዘናል። ይኽ አጭር ታሪክም የሚጠቁመን ይህንኑ ነው።በተልይም ችግኙን እንደነቀለው እንደዚህ ዐላዋቂ ህፃን እምነታችንን የተውን ባህላችንን የጣልን በአጠቃላይ የምንሰራው የጠፋብን ካለን ልብ በሉ ይለናል።
26 viewsedited  09:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 18:15:19 ዛሬ ላይ የገጠሙን ችግሮች ' የዛሬ ዐመት ላይ ታሪክ ናቸው ፡፡ ታሪክ ብቻ ! እስከ ዛሬ በጣም ብዙ ከባባድ ጊዜያቶች ገጥመውህ አያውቁም ? ታውቃለህ ፡፡ እሺ ችግሮቹ ዛሬም ድረስ አሉ ?

አላልፋቸውም ያልካቸው ተራራ ተራራ የሚያህሉ የሀዘንና የመከራ ጊዜያቶች አልፈው እየሳቅክ ነበረ ፡፡ አዕምሮህም ነፃ ሆኖ ዘና ብለህ ነበረ ፡፡

አሁንም አዲስ ነገር የለም ሀቢቢ , እመነኝ ይህኛውም ያልፋል ፡፡
ሁሉም ያልፋል !
34 views15:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 18:09:16 ከሰዎች ጋር ያለህ ግንኙነት ጥሩ እንዲሆን የምትፈልግ ከሆነ ሰዎችን ዕወቃቸው ባህሪያቸውንና አመለካከታቸውንም አጥና ፡፡

ድመት ድመት መሆኗን ዘንግተህ እንደ በግ treat ልታደርጋት ብትሞክር ፊትህ ላይ ዳማ ትሰራልሃለች ፡፡ በጉንም እንደ ድመት ልታጫውተው ከሞከርክ በቴስታ ብሎ ሰማይ ምድሩን ያዞርብሃል ፡፡

ህይወት ሰፊ ነች አጋጣሚዎቿም ብዙ ናቸውና የተለያየ ዐይነት ባህሪ ካላቸው ሰዎች ጋር ልታገናኝህ ፣ ልታዛምድህና ልታቆራኝህ ትችላለ ፡፡ አንዳንዱ በባህሪው ግትር ፣ ቁጡ ፣ ነጭናጫ ፣ ጭምት ፣ አዝግ ፣ ተንኮለኛ ፣ አልማጭ ፣ ራስ ወዳድ ፣ ጉረኛ ፣ ትዕቢተኛ ፣ ገለልተኛ ፣ ስግብግብ ፣ ሴሰኛ ፣ ፣ ጨካኝ ፣ ሴረኛ ፣ እኔ ብቻ ልደመጥ ባይ ፣ እኔ ብቻ ቆንጆ ነኝ ባይ ሊሆን ይችላል ፡፡ ሌላው ደግሞ በተቃራኒው አዛኝ ፣ ተጫዋች ፣ ትሁት ፣ ለሰው ሟች ፣ ቁጥብ ፣ ተናናሽ ፣ ፣ ለስላሳ ፣ ተግባቢ ሊሆን ይችላል ፡፡ ለሁሉም በሽተኛ ተመሳሳይ መድሃኒት እንደማይሰጠው ሁሉ የተለያየ ባህሪ ላላቸው ሰዎችም ተመሳሳይ approachን ማንፀባረቅ ተገቢ አይሆንም ፡፡

ምን አልባት ሁሌም ትሁት እና ለስላሳ መሆን ላያዋጣ ይችላል ፡፡ አንዴ ምን ሆነ መሰላችሁ , የሆነ ጓደኛዬ ወደ መስጂድ ለመሄድ ከቤቱ ወጥቶ መንገድ ጀመረ ፡፡ ውስጥ ለውስጥ እየተጓዘ ሳለም የሆነ ዕብድ ቋጥኝ የሚያህል ድንጋይ ይዞ በሚያስፈራ አካኋን ወደሱ አቅጣጫ እየተግተለተለ ሲመጣ ተመለከተ ፡፡ ፈርቶ ወደኋላ ቢሮጥ ዕብዱ የያዘውን ድንጋይ ሊወረውርበት ይችላል ፡፡ ብልጡ ጓጀኛዬ ፈጠን ብሎ እሱም ዕብዱ የያዘውን የሚያስንቅ ኪሊማንጃሮ የሚያህል ዐለት ተሸከመና ወደ ዕብዱ አቅጣጫ በፍጥነት መራመድ ጀመረ ፡፡ ወዲያውም ዕብዱ ፊቱን አዙሮ በመጣበት ነካው ፡፡
አንዳንዴ እንዲህም ይሰራል ( ሞክራችሁት ብትፈነከቱ እኔ የለሁበትም )

ያ ማለት ግን አፀያፊ ስድቦችን የሰደባችሁን ስደቡ
ያዋረዳችሁንም አዋርዱ ማለት አይደለም ፡፡ ለአንዳንዶች ከመልስ ይልቅ ዝምታ ከመብረቅ የበለጠ የሚጮህ አስደንጋጭ መልስ ይሆናል ፡፡
35 views15:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 02:58:29
የስልጤ እና ጉራጌ ዞኖች የህዝበ ውሳኔያቸውን ''የዞን ምክርቤታቸውን ውሳኔ'' ''የሁለቱ ዞኖች የምክርቤታቸው ውሳኔ ምንም ይሁን ምን'' ባላሳወቁበት ሁኔታ፣ይቺ የምወዳት Nebiha Mohammed Abedulhakim ትልቅ የመንግስት ባለስልጣን በዪፋዊ የፌስቡክ ገፅዋ ምን እያለችን ነው?! ምንስ ያመላክታል?!

1፦የስልጤን እና ጉራጌን ህዝብ፣የህዝቡን ውክልና የያዘውን የዞን ምክርቤትና ይሄንንም መብት የጎናፀፈቸውንም ህገመንግስት የናቀችና ያዋረደች መሆኑን። (ለዚህም ሁለቱን ህዝቦች በይፋ ይቅርታ ልትጠይቅ ይገባል)

2፦ከሁለቱ ህዝቦችና የህዝቡን ውክልና ከያዘው ከዞን ምክርቤታቸው ውጭ በሆነ አካል፣ ፖለቲካል በሆነ መንገድ የተወሰ ውሳኔ መሆኑን። (ይሄ የታወቀ ነው)

3፦አዲስ በሚመሰረተው የሸዋ ክልል ስልጣን ለመያዝ ከፌደራል እስከ ክልል ያሉ ባለስልጣናት አሰፍስፈው እየጠበቁ መሆኑን። ( ሀዲያ፣ስለጤና ጉራጌ ክልል እንዳይሆኑ ካደረጉት ምክኒያቶች ውስጥ አንዱ ይሄ ነው)

N.B፦ ቀድመው በሚወጡት መረጃዎች መሰረት ከሆነ ውሳኔው የታወቀ ነው።ሸዋ ክልል ይመሰረታል።ታዲያ ምን ይሻላል?! ምን ይብቃን ያላችሁ እንደሆነ?! መማር።አዎ ማህበረሰባችን ማስተማር።ሁለንተናዊ በሆነ መንገድ ማብቃት፣ማደራጀት።ዞኑም ላይ ሆነ አዲስ በሚመሰረተው ሸዋ ክልል ላይ ወሳኝ ቦታዎች ላይ መኖር፣ቅርብ ሆኖ መታገል ነው እልሃለሁ ወገኔ!!
58 views23:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 10:18:49 ጥሩ ነገር ከፈለግክ መሞከር ፣መጠበቅና መታገስ ይኖርብሃል።አሁን ካልሆነ አትበል!

اللهم أدخله علينا بالأمن والإيمان والسلامة والإسلام وجوارٍ من الشيطان ورضوانٍ من الرحمن
امين

መልካም የሒጅራ አዲስ አመት ይሁንልን
1/1/1444 ዓ/ሒ
53 views07:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 01:18:31 Albert Einstein once said “ Every one is a Genius , But if you judge a fish by its ability to climb a tree it will live its whole life believing that it is stupid .”

እናንተ በእናንተነታችሁ ልዩ ናችሁ እራሳችሁንም ከማንም ጋር አታወዳድሩ የሚባለው በምክንያት ነው !
75 views22:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ