Get Mystery Box with random crypto!

The Blue Vet

የቴሌግራም ቻናል አርማ thebluevet2021 — The Blue Vet T
የቴሌግራም ቻናል አርማ thebluevet2021 — The Blue Vet
የሰርጥ አድራሻ: @thebluevet2021
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.13K
የሰርጥ መግለጫ

The Blue Vet is an Inspiration and Wisdom for Livestock sector run under @BeyondStudent4Change Initiative. You want to share something use @YimeT, @Salah_8, and @BetyydrS,@Eleazi @DrBam @AronAlexVet

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

3

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-09 15:24:33 በጎንደር የማክሰኝት ወረዳና የእንስሳት ሀኪሞቿ ፈተናዎች

የማክሰኝት የእንስሳት ህክምና ክሊኒክ በወርልድ ቪዥን የበጐ አድራጐት ድርጅት በ2002 ዓ.ም ከተገነባበት ጊዜ ጀምሮ ዘርፈ ብዙ የህክምና አገልግሎቶችን ለአካባቢው ማህበረሰብ በመስጠት ላይ ይገኛል። በአካባቢው Anthrax(አባሰንጋ), Blackleg(አባጎርባ), Lumpy skin disease(አጉረብርብ), Epizootic lymphangitis (ንድፍት) ኬዞች በተደጋጋሚ በአካባቢው የሚከሰቱ ሲሆን፤ Anthrax(አባሰንጋ) ከአንድ አመት በፊት ተከስቶ ለሰውና ለእንስሳት ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆኖል።

የክሊኒኩ ሀኪም የሆኑት ዶ/ር አለማየሁ እሸቴ እንደገለፁት አብዝሀኛው የሀገራችን ህዝቦች ኑሯቸው ከእንስሳት ጋር የተገናኘ እንደመሆኑ ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎች(zoonosis diseases) በሰው ህይወትና አካል ላይ ጉዳት እያደረሱ ይገኛሉ። በመሆኑም የህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ፣የጤና ተቋማት ፣የእንስሳት ህክምና የአካባቢ ደህንነት ጥበቃ ተቋማት (one health approach) ተናበው በጋራ ቢሰሩ የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ጠቁመዋል።

በክሊኒኩ እንዲሁም በባለሙያው ላይ ያሉ በርካታ ችግሮች ገልፀዋል። በገበያ ላይ በቂ የሆነ የመድሀኒት አቅርቦትና አቅራቢ ድርጅት ባለመኖሩ ፤መሠረታዊ የሆኑ የላብራቶሪ ሪኤጅንቶች ና የባለሙያውን ደህንነት የሚጠብቁ ግብአቶች አለመሟላታቸው፤ተማሪዎች ከትምህርት ተቆማት ተመርቀው ከወጡ በሁዋላ ወደ ስራ ዐለም ሲገቡ ተከታታይ የሆነ የክህሎት ስልጠና እና ተጨማሪ የትምህርት እድል አለመኖር፤ በየጊዜው የባለሙያው የደረጃ እድገት አለመኖር፤ መንግስት ለዘርፉ በቂ የሆነ ትኩረት ባለመስጠቱ ምንም እንኳን በዘርፉ ትልቅ የሆነ ሀብት ቢኖርም መጠቀም አልተቻለም።

በተጨማሪም ባለሙያው የሚጠይቃቸውን የአገልግሎት ጥቅማቅሞች፤አስተዳደራዊ ጥያቄዎች የሚመልስ አካል ባለመኖሩ የሀኪሞችን ብሩህ ተስፋ ና የሞራል ተነሳሽነትን ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አድርጓል። የህክምና ባለሙያዎች ወደ አስተዳደራዊ ሀላፊነት ቢመጡ በዘርፉ የሚታዩ ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮች ስለሚያቁ ወደ ሀላፊነት እንዲመጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።

አዲሱ አያሌው (ሚቹ)
የጎንደር ዩኒቨርስቲ 5ተኛ አመት የእንስሳት ህክምና ተማሪ
19 views12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 15:24:33
18 views12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 13:24:51 ሰሞነኛው የዶሮ በሽታ እና በዘርፉ ላይ እያስከተለ ያለው ጉዳት https://am.addiszeybe.com/featured/adama/economy/current-affairs-am/current-chicken-pox-disease-and-its-impact-on-the-sector
172 views10:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 13:15:11 ሰሞነኛው የዶሮ በሽታ እና በዘርፉ ላይ እያስከተለ ያለው ጉዳት https://am.addiszeybe.com/featured/adama/economy/current-affairs-am/current-chicken-pox-disease-and-its-impact-on-the-sector
157 views10:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 12:24:48
ከተማሪነት በላይ ለለውጥ
የኡስማን እይታወች

ይህን ትልቅ ሀሳብ በደንብ ልብ ብሎ ላስተዋለው እና ትኩረት ለሰጠው ብዙ ነገሮችን ይገልፃል። እንደ አጠቃላይ አብዛኛው የ ሀገሪቱ አምራች ሀይል በየትምህርት ማዕከሎች እና ዩኒቨርቲዎች እንደመገኘቱ መጠን ሁሉም በሚማርበት መስክ ይህን ፅንሰ ሀሳብ ማለትም ከተማሪነት በላይ ለለውጥ አስተሳሰብን ቢተገብር እራሱን ብሎም ሀገርን መለወጥ የሚችልበት ሰፊ እድል አለው::

ይህ ሀሳብ ካዳረሳቸው ቦታዎች መካከል ጎንደር ዩኒቨርስቲ አንዱ ነው። ምስጋና ለክለቡ መስራቾች ይሁን እና ያለንን አቅም በአግባቡ ከተጠቀምን ከተማሪነት በላይ ከፍ የማንልበት ምክንያት እንደማይኖር አሳይተውናል። ይህንንም ግቢው ውስጥ ባካሄድናቸው በርካታ እንቅስቃሴዎች መገንዘብ ችለናል::

በተለይ የእንሰሳት ህክምና ሴክተሩን በማነቃቃት በባለ ሙያው የሚነሱ ጥያቄዎችን ለሚመለከተው አካል በማድረስ በተለያዩ ቦታዎች የሚወጡ ማስታወቂያዎችን ተደራሽ እንዲሆኑ በማድረግ እንዲሁም የተማሪዎችን እና የሙያተኛውን የእውቀት እድማስ ለማስፍት በጠቃሚ መረጃ በኩል በማስተላለፍ የበኩሉን ሚና እየተጫወተ ይገኛል::

ይህ ሀሳብ በሁሉም ተዳርሶ የራሱን ሚና ይጫወት ዘንድ የመስራቾች ብቻ ሳይሆን የሁላችንም ሚና ሊሆን ይገባል::

ከተማሪነት በላይ ለለውጥ
አለባቸው ሙሀመድ(ኡስማን)
የ 5ኛ አመት DVM ተማሪ
160 views09:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 19:07:53 የእንስሳት ጤና ባለሙያነት

የእንስሳት ጤና ሙያ በብዙ መልክ እጅግ የተለየ ድንቅ ሙያ ነው። ስለተከፈለን እና ስለሚበቃን ሳይሆን ነፍስን ወደን እና አክብረን ስለምንሰራ የሚያስደስተኝ ሙያዬ ነው። እንደ እንስሳት ሀኪምነቴ ልናውቀው የሚገባ ነገር ብዬ የማስበው የእንስሳት ሙያ እጅግ የተከበረ ሙያ መሆኑን ማወቅ ነው። ለዚህ የሚከተሉትን ነጥቦች አስቀምጫለሁ።

በስድስት አመታት ከ60 በላይ ኮርሶችን መማራችን እንደ መሪ ብዙ ጫና ያለውን ነገር እንድንጋፈጥ አድርጎናል። የተሰማውን መናገር የማይችል እንስሳትን ማከማችን እንደ ትክክለኛ መሪ ውስብሰብ ችግሮች በመረዳት መፍትሄ ሰጭነትን አላብሶናል። የእንስሳት ሀኪም ብዙ መጽሀፍቶችን ማንበብ የግድ ይለዋል መሪም ልክ እንደዛው! የanimal health ecnomics እና vet. Epidemology መሠረታዊ የሪሰርች እና የኢኮኖሚክስ እውቀት ሰጥተውናል። ከእንስሳቶች ባህርያት (animals behavior) የአመራር ክህሎትን እንማራለን። የproduction ትምህርቶች ለቢዝነስ የሚገባን አመለካከት ጭምር አላብሶናል።

ስለሆነም በማንኛውም አጋጣሚ ሙያህ ምንድን ነው ስትባል በኩራት የእንስሳት ሀኪም ማለት አለብህ! ለምን ካልከኝ መልሴ የሚያኮራ ሙያ ስለሆነ። ብዙዎች በእንሰሳት ህክምና አንቱ ተብለዋል ለሳይንስ በከፈሉት መስዋዕትነት መክንያት በሌሎች ዘንድ ትልቅ ክብር አግኝተዋል። አሁን ያለህበት ሁኔታ በሙያህ ያሉት ችግሮች ከተራራ ሊበልጥ ይችላል። ግን የምትወደው የምትኮራበት የእንስሳት ህክምና ሳይንስ ጥሎ አይጥልህም።

በነገራችን ላይ ለዚህ ሙያ ላቅ ያለ ስነልቦና ባለቤት መሆን ያስፈልጋል። በየትኛውም ሙያ ተስፋ የቆረጠ ሰው በራሱም ቢሆን ውጤታማ መሆን አይችልም። የሁኔታዎችን አለመጣጣም እና የሰዎች ጠማማነት ምክንያት በማድረግ እንስሳት ህክምና የወረደ ሙያ አድርጎ ማቅረብ በዛ ላይ የእንስሳት ህክምና ባለሙያ ሆኖ ጭምር በዚህ አውድ ውስጥ መውደቅ ነው እንደ አስተሳሰብ ከሌሎች ሙያዎች እኩል የሚገባንን ክብር እና ጥቅማጥቅም እንዳናገኝ አግዶ የያዘን ነገር ነው።

እኔ የእንስሳት ሀኪም ነኝ። በቅርብ አመታት ውስጥ የእንስሳት ህክምና በኢትዮጵያ ትልቁ ተከፋይ ሙያ እንዲሆን የምለፋ ይሆናል። አያይዘን በሙያ ውስጥ ያለን ችግሮች በመሰረታዊነት ለመፍታት የምታገል ይሆናል። የግል ጥረት ብቻ የትም አያደርስ ከተባበርን ግን ሙያችን ካሰብነው እና ከሚገባን ቦታ እናደርሰዋለን።

#Repost

ሳላሀዲን አሊ
ከተማሪነት በላይ ለለውጥ መስራች
194 views16:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 19:07:53
የእንስሳት ጤና ባለሙያነት
176 views16:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 13:32:24 The Blue Vet TikTok page

https://vm.tiktok.com/ZMNDU5Bwb/?k=1
191 views10:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 10:40:48 አለማቀፉ ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎች ቀን

በአለማቀፍ ደረጃ ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎች ቀን ላይ የማስተማርና የግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን እንዲሆን በማሰብ የተጀመረው በዛሬው ቀን እ.አ.አ 1885 ዓ.ም ሲሆን ሊውስ ፓስቸር ለመጀመሪያ ጊዜ ለውሻ እብደት በሽታ ክትባት በማበጀት የከተበበት ቀን እንደሆነ ታሪክ ይነግረናል፡፡ ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎች በባክቴሪያ፣ በቫይረስ፣ በፓራሳይት (ጥገኛ) እና በፈንገስ አማካኝነት የሚከሰቱ ሲሆን ለተለያዩ የሕመም አይነት የሚዳርጉ ሲሆን፤ በሰው እና በእንስሳት ላይ እስከ ሞት ድረስ ሊያደርሱ የሚችሉ ናቸው፡፡ ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎች የሰውን ልጅ ለህመም እና ለሞት ከማድረሳቸው ሳያስ በወረሽኝ መልክ ሲከሰቱ ጉዳታቸው ከሀገር ያልፍና የአለምን ኢኮኖሚ የማሽመድመድ አቅም ያላቸው እንደሆነ አለማችን ላይ እንካሁን የተከሰቱትን ተላላፊ በሽታዎችን መመልከት በቂ ነው፡፡

ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎች አደገኝነት በዚህ ላይ ብቻ አያበቃም ሀገራት ሀያልነታቸውን ለማሳየት ለጦርነት የሚጠቀሙባቸው እንደሆም ያለፉትን የአለም ጦርነት መመልከት ለዚህ ማሳያ ነው፡፡ ሀገራት ጥይት ብቻ በመጠቀም ሀገራቸውን ከጠላት ለመጠበቅ በማለት እጅግ አደገኛ የሚባሉትን የሰውን ፍጥረት በጥቂት ደቂዎች ሊያጠፉ የሚችሉትን በመያዝ ጉልበተኛነታቸው ለማሳየት የሚጠቀሙበት እንደሆነ ታሪክ ይነግረናል፡፡

በርካታ ጥናቶች እንደሚነግሩን የሰውን ልጅ ለጤና እክል፤ አልፎ ለሞት ከሚዳርጉት አበይት በሽታዎች ከ 60-75% የሚጠጋው ከእንስሳት የሚነሳ እንደሆነ በተለይም ከዱር እንስሳት እንደሆነ ይነግረናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በአለማችን ላይ እንደ አዲስ ከሚከሰቱ 5 የበሽታ አይነቶች 3 ያህል የሚሆኑት እንስሳት መነሻቸው እንደሆነ ያስቀምጣሉ፡፡

በእነዚህ አለማቀፍ እውነታዎች የምንገነዘባቸው ነገሮች መካከል፤

1. የእንስሳት ጤና ማለት የሰው ልጆች ጤና እንደሆነ
2. የእንስሳት ጤና አለመጠበቅ ለሰው ልጅ መዘዙ ብዙ እንደሆነ
3. ዋናው ደግሞ ለእንስሳት ጤና መጠበቅ በደንብ መሰራት እንዳለበት ነው፡፡

ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመከላከልና እና የአካባቢን ጤና መጠበቅ ለማረጋገጥ በሀገራችን የተላያዩ ተግባራት ይከወናል፡፡ ለአብነት የምንመለከተው ብሔራዊ የአንድ ጤና መማክርት ነው፡፡ በዚህ መማክርት ውስጥ የሰው ልጅ ጤና፣ የእንስሳት ጤና እና የአካባቢ ጤና የሚመለከታቸው የሚኒስቴር ተቋማት የሚገኙበት ሲሆን በስራቸው ያሉ ተጠሪ ተቋማትን ጨምሮ በርካታ ድጋፍ ሰጪ ሀገር አቀፍና አለማቀፍ ተቋማትን ይዞ የሚንቀሳቀስ ነው፡፡ በዚህም ተቋማት ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎች እና በርከት ካሉ የጋራ ጥረትን፣ አብሮ መስራት በሚጠይቁ ስራዎች ላይ በመቀራጀት ይሰራሉ፡፡

አሁን ላይ ኢትዮጵያ ትኩረት አድርጋ ከብዙዎች በመለየት ከላይ የጠቀስኳቸውን ተቋማት በማስተባበር ከምትሰራባቸው ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎች መካከል፤

1. Anthrax
2. Rabies
3. Brucellosis
4. Rift Valley Fever
5. Zoonotic Avian Influenza፣ ናቸው፡፡

በመጨረሻም ሁላችንም እንስሳት የሚፈልኩት በጤና የመጠበቅ መብት በመተግበር ለጤናቸው መጠበቅ የመኩላችንን በመወጣት ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎችን እንግታ እንቆጣጠር እላለው፡፡ እንስሳት ሁሉ በሽታ አምጪ ሳይሆን ለጤናችን መመለስ፣ ለመፍትሔ ምንገዶቻችን እና ጠባቂዎቻችን እንደሆኑም ግንዛቤ ሊወሰድ ይገባል፡፡ አመሰግናለው፡፡

ቦታ፡ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት
ፎቶ፡ (ዶ/ር ፈይሳ ረጋሳ እና ዶ/ር ይመስገን ታረቀኝ)

ይመስገን ታረቀኝ (ዶ/ር)
ከተማሪነት በላይ ለለውጥ
199 views07:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 10:40:32
አለማቀፉ ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎች ቀን
183 views07:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ