Get Mystery Box with random crypto!

ጸያሔ ፍኖት

የቴሌግራም ቻናል አርማ tseyahafinoti — ጸያሔ ፍኖት
የቴሌግራም ቻናል አርማ tseyahafinoti — ጸያሔ ፍኖት
የሰርጥ አድራሻ: @tseyahafinoti
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.73K

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-12-08 15:32:11 +"በምድር ያለች ሰማይ"+

ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤ/ክ የክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ናት የምንላት የእኛ ስለሆነች በደጋፊነት አይደለም። እርሱ ክርስቶስ የሰማዩን ስርዓት ያዥ እንዳላት የሰማዩን ሥርዓት የያዘች ፣ #ፈቃዱ_የሚመራት ፣ #ውዴታው_የሳባት ፣#ከዚሁ ፍቅር_ገመድ_ያልወጣች ፣ #የሰማዩን_በምድር የምትኖር ፣ በምድር_ያለች_ሰማይ ስለሆነች ነው እንጂ።

እርሱ የሰማዩን እወዳለሁ እንዳለ እንስሳዊ ጠባይዕን ለመልዐካዊ ጠባይዕ አስገዝቶ መኖርን ፣ ሥጋዊነትን ገዝቶ ፣ መንፈሳዊ ኑሮን ለልጆቿ የምታስተምር ስለሆነች ነው እንጂ ከዚህም ፈቃዱ እንዳትወጣ ማለዳ በኪዳኑ ጸሎቷ "ሀበነ ንሑር በትዕዛዝከ - #አቤቱ_በትዕዛዝህ_በፈቃድህ_እንኖር_ዘንድ_ምራን" እያለች ትማልደዋለች ። ሰርክም በቅዳሴው "እወ እግዚኦ አምላክነ በእንተ ዐቢይ ስምከ ንጉደይ እምኩሉ ሕሊና ዘኢያሰምረከ - አዎን አቤቱ አምላካችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ስለ ግሩም ልዑል ስምህ ብለህ አንተን #ከማያስደስት ፣ #ከፈቃድህ_ከወጣ_ክፉ_አሳብ_እንሸሽ_ዘንድ_መሸሹንስጠን" እያለች ትለምነዋለች ። እንዲሁም በንስሃ ጸሎቷ "ሀበነ እግዚኦ ንግበር ፈቃድከ ወሥምረትከ ኩሎ ጊዜ - #አቤቱ ሁልጊዜ #ፈቃድህን_ውድህን_እንሰራ_ዘንድ_ልብንና_ልቡናን_ጥበብን_ስጠን" እያለች ለፈቃዱም ፈቃዱን በትህትና ትጠይቃለች። በትህትና የመሠረታት የትሁት ክርስቶስ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤ/ክ ግለሰብ አቋቁሞ የማይመራት መንፈስቅዱስ የሚመራት እንከን የሌላት ምልዕተ ትህትና በምድር ያለች ሰማይ ናትና።
አባ ገ/ኪዳን ግርማ

@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
@Yahiwenesei
257 viewsMeba ZeGebriel, 12:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-03 01:19:57 የኢኦተቤክ አስተምህሮ ና ስርአትን የጠበቁ የትኞቹን መዝሙራት ማግኝት ይፈልጋሉ

የቸብቸቦ መዝሙራት
          ▓⇨→vido    ⇨ግጥም
የበገና መዝሙራት  
         ▓⇨→vido     ⇨ግጥም
የቅዱሳን መዝሙራት
          ▓⇨→vido    ⇨ግጥም
የንግስ መዝሙራት
          ▓⇨→vido    ⇨ግጥም
የምስጋና  መዝሙራት
          ▓⇨→vido    ⇨ግጥም
የንስሐ  መዝሙራት
         ▓⇨→vido   ⇨ግጥም
የሠርግ መዝሙራት
          ▓⇨→avido   ⇨ግጥም
ወቅታዊ መዝሙራት
          ▓⇨→vido    ⇨ግጥም
ለአገር የተዘመሩ
          ▓⇨→vido   ⇨ግጥም
         







          ከእስልምና ወደ ክርስትና በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ በYOUTUBE

         𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘
   





           𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 ‌‌
93 viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 22:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 21:32:41 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
           #ተዝካራ_ለጽዮን_ማርያም _(ኅዳር ፳፩)
    እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከምድረ ግብጽ በሙሴ መሪነት ጠላት ገድሎ ባሕር ከፍሎ ካሻገራቸው በኋላ በደብረ ሲና ተራራ ታቦተ ጽዮንን ሰጥቷቸዋል፤ (ዘጸ 12፥51 ፣ ዘጸ 31፥18 ፣ ዘጸ 34፥1)፡፡ ፵ ዘመን ሙሉ መና ከደመና አውርዶ ውኃ ከጭንጫ አፍልቆ እየመገበ በሙሴ ምትክ ኢያሱን በአሮን ምትክ አልዓዛርን ሰጥቶ ምድረ ርስት አገባቸው፡፡ ከዚያ መስፍን ሲሞት መስፍን ካህን ሲሞት ካህን እያስነሳ ከዔሊ ደረሰ፡፡ ዔሊ ክህነት ከምስፍና ይዞ ፵ ዘመን አስተዳድሮ ሲደክም አፍኒንና ፊንሐስ የተባሉ ልጆቹን የበላይና የበታች አድርጎ ሾማቸው፡፡ የዔሊ ልጆች ግን ክፉዎች ነበሩና በዔሊ ሥርዓት አልተጓዙም፤ በፊት የነበረውንም ሥርዓት አጠፉ፡፡ ካጠፉት ሥርዓት የተወሰኑት ቀጥሎ ተዘርዝረዋል፡፡
1. በቀዳማይ ሰዓተ ሌሊት በርቶ በቀዳማይ ሰዓተ መዓልት የሚጠፋ የደብተራ ኦሪት የሙሴና የአሮን ሥርዓት ነበር፤ ምን ያደርጋል ብለው አስቀርተዋል፡፡
2. መሥዋዕት የሚሠው ሰዎች ሲመጡ ከታረደው ስጡን ይላሉ፤ መሥዋዕት አቅራቢዎቹም ‹‹መጀመሪያ ስቡ ይጢስ፣ ደሙ ይፍሰስ ዐጥንቱ ይከስከስና ከዚህ በኋላ የወደዳችሁትን ታደርጋላችሁ›› ሲሏቸው ‹‹ብትሰጡን ስጡን ባትሰጡን በግድ እንወስዳለን›› እያሉ ብልት ብልት ስጋ እየነጠቁ ይወስዱ ነበር፡፡
3. ጽዮንን  መቃጠሪያ አደረጓት፤ ሴቶችም ይህንማ መቼ ከባሎቻችን አጣነው ብለው ቀርተዋል፡፡
   ዔሊም ይህን ሰምቶ ‹‹ልጆቼ የምሰማባችሁ ይህ ነገር መልካም አይደለም፤ እንዲህ አታድጉ ሰውስ ሰውን ቢበድል በእግዚአብሔር ያስታርቁታል ሰው ግን ከእግዚአብሔር ጋራ ቢጣላ በማን ያስታርቁታል? ተው›› አላቸው፤ ልጆቹ ግን አልሰሙትም፤ (1ሳሙ 2÷22-26)፡፡ በቤተ መቅደስ ውስጥ ጽዮንን ለሚያገለግል ለሳሙኤል እንደነገረው እስራኤል ከፍልስጥኤማውያን ጋራ ጦርነት ገጥመው ድል ኾኑ፡፡ እነሱም ‹‹ታቦተ ጽዮንን ባንይዝ ነው›› አሉ፡፡ እግዚአብሔር የአፍኒንና ፊንሐስ ሞት ፈቃዱ ነውና ታቦተ ጽዮንን ይዘው አብረው ዘመቱ፡፡ አሕዛብም እልልታውን ሰምተው ‹‹ወዮልን የእስራኤል አማልክት መጡብን›› ብለው ተጨነቁ፡፡ ነገር ግን አሕዛባውያኑ በድፍረት ጦርነቱን ገጠሙ፡፡ በጦርነቱም አፍኒንና ፊንሐስ ሞቱ፤ ታቦተ ጽዮንም ተማረከች፡፡ እስራኤል ከቀድሞው የበለጠ ፴ ሺህ እግረኞች አለቁ።

በዚህም ካህኑ ዔሊ በደብተራ ኦሪት ፊት ለፊት በወንበር ላይ ተቀምጦ የታቦተ ጽዮንን ነገር ያወጣ ያወርድ ነበር፡፡ ከዚያም አንድ የብንያማዊ ሰው ልብሱን ቀዶ እየሮጠ ሲመጣ ዔሊ ‹‹ከወዴት መጣህ?›› ብሎ ቢጠይቀው ‹‹ትናንት ከሰልፍ አምልጨ የመጣሁ ነኝ›› አለው፡፡ ከጦርነቱ አምልጦ የመጣው ብንያማዊም ለዔሊ ልጆቹ እንደሞቱ፣ እስራኤላውያን እንዳለቁና ታቦተ ጽዮን እንደተማረከች ነገረው፡፡ ዔሊም ‹‹ልጆቼ ብመክራቸው እንቢ ብለዋል ታቦተ ጽዮን ግን እንዴት ትማረካለች?›› ብሎ አለቅሳለሁ ሲል ከወንበሩ ወድቆ ሞቷል፡፡ ‹‹ዔሊ የ፺፰ ዓመት ሽማግሌ ነበርና ከወንበሩ ወደቀ ዐንገቱ ተሰብሮ ሞተ›› እንዲል (1ሳሙ 4÷9-18)።
   
   ፍልስጥኤማውያንም ታቦተ ጽዮንን ማርከው ወደ አዛጦን ወስደው በዳጎን አጠገብ አድርገው ሄዱ፡፡ በነጋታው ሲገቡ ዳጎን በግንባሩ ወድቆ አገኙት፤ እንደነበረው አድርገውት ቢሄዱም አሁንም በነጋታው ሲመለሱ እጅ እግሩ ተቆራርጦ ደረቱ ቀርቶ አገኙት፡፡ ከዚያ ታቦተ ጽዮንን ወደ ጌት ሰደዷት፤ ከዚያም ወደ አስቀሎና ኢሎፍሊ እየተዘዋወረች ለሰባት ወር ከተቀመጠች በኋላ ባደረገችው የኃይልና የመቅሰፍት ተአምር ቀንበር ያልተጫነባቸው ላሞች ጠምደው በአዲስ ሠረገላ ጭነው ካሳ ወርቅ ሠርተው ላኳት፡፡ ላሞቹም ያለ ነጅ ወደ እስራኤል ሀገር አምጥተው በቤትሳሚስ ከኢያሱ እርሻ አጠገብ ደርሰው ቆሙ፡፡ የቤትሳሚስም ሰዎች ሠረገላውን ፈልጠው ላሞቹን አርደው መሥዋዕት አቀረቡ፤ ከዚያ ወደ አሚናዳብ ቤት መጥታ ልጁ አልዓዛር እያገለገላት ዳዊት እስኪያመጣት ድረስ በዚያው ሃያ ዓመት ተቀምጣለች፡፡ ከዚያም ታቦተ ጽዮን ከአሚናዳብ ቤት ወደ ዳዊት ከተማ (እስራኤል) በዳዊት የንግሥና ዘመን ተመልሳለች፤ (2ሳሙ 6፥1-19)፡፡

    በተጨማሪም ነቢዩ ዘካርያስ ጽዮንን በተቅዋመ ማኅቶት አምሳል ያየበት፣ ቀዳማዊ ምኒልክ ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የገባበት፣ በዮዲት ጉዲት ጊዜ በዝዋይ ደሴት ከ፵ ዓመት በላይ ቆይታ ሰላም ሲሆን ተመልሳ አክሱም የገባችበት ዕለት በመሆኑ እንዲሁም አብርሃና አጽብሐ በአክሱም ከተማ ከ፫፻፴፮-፫፻፴፱ ዓ.ም ቤተ መቅደሱን ሠርተው ቅዳሴ ቤቱን ያከበሩበት ስለሆነ የበዓሉ መታሰቢያ ኅዳር ፳፩ ቀን በድምቀት ይከበራል፡፡ ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን አሜን!
(ውድ አንባቢያን ስለ ዔሊ ልጆች ጥፋት እና ስለ ታቦተ ጽዮን መማረክ ሙሉውን ታሪክ መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ ከምዕራፍ ሁለት እስከ ምዕራፍ ሰባት ያለውን ያንብቡት)፡፡

               ወስብሐት   ለእግዚአብሔር!
ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ ፣ መድበለ ታሪክ

@orthodoxy_eywet
@orthodoxy_eywet
@orthodoxy_eywet
106 viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-26 21:51:09 ሴት በወር አበባዋ ጊዜ መጸለይ ትችላለች
ግለ አውናን / ሴጋ /ማስተርቤሽን/ የፈጸመ ሰው ተክሊል ማግባት ይችላልን
በሱባኤ ወቅት ህልመ ሌሊት (ዝንየት) ቢመታን ምን እናደርጋለን
ሕልመ ሌሊት በራሱ ኃጢአት ነውን
ሕልመ ሌሊት በምን ይከሰታል
ከዝሙት አጋንንት እና ከዝንየት በተጨማሪ በሕልመ ሌሊት የሚፈትነን አጋንንት የትኛው ነው
የሕልመ ሌሊት መፍትሔ ምንድን ነው
ቁርባን ቆርበን ሕልመ ሌሊት እንዳይጸናወተን ምን ማድረግ አለብን

በእነዚህ ትምህርቶች ዙርያ እየተማማርን እንገኛለን እርሶም እውቀቱ እንዲኖርዎ ከፈለጉ ይህን መስፈንጠርያ ይንኩ


█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░  𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█
█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵  ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█
█▓▒░ ► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█
█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵  ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█

     ተወዳጅ ዘማሪያን
          አዲስ ዝማሬ በይቱብ
       









           𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 ‌‌
109 viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 22:34:26 ትክክለኛ ወቅታዊ ኦርቶዶክሳዊ መረጃ ማግኘት ይፈልጋሉ?
የተለያዩ የአውደምህረት ዝማሬ፣ ስብከት
ወቅታዊ የቤተክርስቲያን መረጃ
የቅዱሳን እና የገዳማት ታሪኮች
እነዚህን ለማግኘት ከስር ያለውን ሊንክ በመጫን እና ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ እንሁን

subscribers subscribers
subscribers subscribers




211 viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 19:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-29 20:33:16
369 viewsወሰንየለው ባህሩ, 17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-15 20:25:10
በአዶላዋ ፈርጥ፥ በአዶላ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ዘወትር እሑድ ልዩ ሳምንታዊ  ጉባኤ ተዘጋጅቷል። ከነገ ጀምሮ ዘወትር እሑድ ከ10 ፡ 30 ጀምሮ በደመቀ ሁኔታ ይካሄዳል። ስለሆነም እርሶም በጉባኤው በመገኘት ከተዘጋጀው የወንጌል ማዕድ ለሕይወትዎ ስንቅ ይገበዩ ዘንድ መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!!
ዕለተ እሑድን በደብረ ገነት!
         
    የደብሩ ስብከተ ወንጌል
811 viewsወሰንየለው ባህሩ, 17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-07 22:52:44 ወዴት ነው?›› ተብሎ ሊሠዋው ባሰበው ልጅ ሲጠየቅ እጅግ

ል፡

ነገር ግን የልቡ ሐዘን ገንፍሎ ወጥቶ ከፈጣሪው ጋር እንዲያጣላው አልፈቀደለትም፡፡ ሐዋርያው እንደሚለው አብርሃም ልጁ ይስሐቅን ‹‹እግዚአብሔር ከሙታን እንኳ ሊያስነሣው እንዲቻለው አስቦአልና›› ከፈጣሪው ለቀረበለት ጥያቄ እሺ ብሎ በዝምታ ታዘዘ።(ዕብ 11፡17-19) ይህም የመታዘዙ ፋና አሁንም ድረስ በልጆቻቸው ለሚፈተኑ ወላጆች ምሳሌ ሆኖ ይታያል፡፡   

ሀብታችሁን የሚወርስ ብቸኛ ልጃችሁ ስለ ሞተ አዝናችኋል፡፡ ግን እስኪ ሀብቴን ይወርሳል ብሎ የሚያስበው አንድ ልጁ ሞቶበት ላዘነ አባት ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ የሰጠውን የማጽናኛ ቃል እንስማ፡፡ ቅዱሱ እንዲህ ይላል :- ‹‹ልጅህ በመሞቱ ምክንያት ሀብትህን የሚወርስ ስለሌለ ነው ያዘንከው? ለልጅህ አብልጠህ የምትመኝለት የቱን ነው? የአንተን ሀብት ወይስ ገነትን እንዲወርስ? ለጊዜው የሚጠቅመውን ምድራዊ ገንዘብ እንዲያገኝ ወይስ የማይጠፋና ዘላለማዊ የሆነው ርስቱን እንዲወርስ? አዎን፣ አሁን ልጅህ ወራሽህ ሆኖ ከአጠገብህ የለም። ነገር ግን በአንተ ምትክ ሆኖ እግዚአብሔር እርሱን ወራሹ አድርጎታል››፡፡

እኛ በኃጢአት ምክንያት እግዚአብሔር የሰጠንን የተፈጥሮ ንጽሕና ስላጣን የሞት ጽዋ ታስፈራናለች፡፡ ንጽሐ ጠባይ (የተፈጥሮ ንጽሕና) ላላደፈባቸው ሕፃናት ግን ይህች ጽዋ ተስማሚ ናት፡፡  ለእኛ የሞታችንም ቀን የዘላለማዊ ቅጣታችን መጀመሪያ ጊዜ እንደ ሆነ እናስባለን፡፡ ለሕጻናት ግን የሞታቸው እለት ለዘላለማዊው የደስታ የመጀመሪያ እለት ነው፡፡

ሕፃናት የሞቱባችሁ ወላጆች ሆይ! ልጆቻችሁን በዚህ ዓለም ላይ ወይም በመቃብር ውስጥ አትፈልጓቸው፡፡ የሰማዩ ንጉሥ ካለበት፣ የሰማይ ሠራዊት ዙፋኑን ከብበው ከሚያመሰግኑበት መንፈሳዊ አገር ፈልጓቸው፡፡

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

https://t.me/akanim1wasen2
110 viewsወሰንየለው ባህሩ, 19:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-07 22:52:44 +++ "ያልተሞቁ ትንንሽ ፀሐዮች" +++

ሕፃናት በአካል መጠን አንሰው ቢታዩም በልባችን ውስጥ የሚይዙት ስፍራ ግን እጅግ በጣም ሰፊ ነው፡፡ ቃል ከአፋቸው ሳያወጡ በፊታቸው ብቻ በሚያሳዩን ፈገግታ ሕይወታችን ላይ ደስታን መዝራት ይችላሉ፡፡ ከዓይናቸው የምትወርደው አንዲት የእንባ ዘለላ ደግሞ ስሜታችንን በኃዘን ምስቅልቅሉን የማውጣት ኃይል አላት፡፡ ሕፃናት ለዚህች ቀዝቃዛ ዓለም የተሰጡ ፀሐዮች ናቸው፡፡ ታዲያ እነዚህ ትንንሽ ፀሐዮች ገና ከመውጣታቸው ብዙም ሳንሞቃቸው መልሰው ሊጠልቁ፣ የልጅነት ቡረቃዎቻቸውን ሳንጠግብ ፈጥነው ሊያንቀላፉ ይችላሉ፡፡ ይህ ሲሆን ኃዘኑ ከባድ ነው፡፡ 

ከአዋቂ ይልቅ የሕፃን ልጅ ሞት ኃዘን ይጠብቃል። በቤተሰብ ውስጥ ከሁሉም መጨረሻ ይሞታል ተብሎ የሚጠበቀው የቤቱ ሕፃን በመሆኑ ልጁ ከወላጆቹ ቀድሞ ሲሞት እጅግ አስደንጋጭ ይሆናል። ወላጆቹ ከልጃቸው ጋር በነበራቸው ያለፈ ግንኙነት ብቻ ሳይሆን፣ እርሱ ላይ የጣሉት የወደ ፊት ተስፋና ሕልማቸው ሁሉ ከንቱ እንደ ቀረ አስበው አንጀታቸው በኃዘን እሳት ይነዳል፡፡ በተለይ ሟቹ ሕፃን ለወላጆቹ አንድ ወይም ብቸኛ ከሆነ በቤተሰቡ ላይ የሚደርስባቸው የኃዘን ስብራት በቃል የማይገለጽ ጥልቅ ነው። ከአገኛቸውም የውስጥ ሕመም እና የልብ መታወክ የተነሣ ቶሎ ለመጽናናት ይቸገራሉ። ከአብራካቸው ወጥቶ ወደዚህ ዓለም የመጣው ሕፃን እንደ ሌሎቹ ሰዎች ሟች እንደ ሆነ ቢያውቁም እንኳን ሞቱ ግን ጨርሶ የማይታመን ይሆንባቸዋል፡፡

በወዳጁ በአልዓዛር ሞት መንፈሱ ታውኮ ያለቀሰ የክርስቶስ አካሉ የሆነችው ቤተ ክርስቲያን ይህ ዓይነቱ ኃዘን ለገጠማቸው ቤተሰብ "አታልቅሱ" ብላ አታስተምርም። ለሰውነት የማይስማማውን ሕግ ጠብቁ ብላ በልጆቿ ላይ ጨካኝ አትሆንባቸውም። የቤተ ክርስቲያን መምህር የሆነው ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ በአንድ ወቅት :- "በልጆቻችሁ ሞት አታልቅሱ ብዬ አላስተማርኩም። እንደዚህ ተናግሬ እንደሆን የማይቻለውን ነገር እላለሁ። እኔ ልክ እንደ እናንተ ከአንዲት እናት የተወለድኩ መዋቲ ፍጥረት ነኝ። ባሕሪያችሁንም ስለምጋራ በሰው ያለውን ስቃይ እረዳለሁ። የአባቶችን ኃዘን የእናቶችን ማቃሰት አያለሁ። ... በሕሊናቸውም የልጃቸውን ልማዶች፣ የሰውነት እንቅስቃሴዎቹን እና ንግግሮቹን እያስታወሱ እንዴት እንደሚሆኑ አውቃለሁ" ሲል ተናግሮ ነበር።

ምንም ሕፃናትን በሥጋ የማጣት ሕመሙ ከባድ ቢሆንም ወላጆቻቸው ግን ‹‹ተስፋ እንደ ሌላቸው እንደ ሌሎች ደግሞ›› ኃዘን እንዲያበዙ አይፈቀድላቸውም።(1ኛ ተሰ 4፥13) ልጆቻቸው ከዚህ ዓለም ወደ ተሻለው ዘላለማዊ ቤት እንደ ሄዱ በማመን መጽናናት አለባቸው። የሞቱት ልጆቻቸውን መቃብር ሰውራ አታስቀራቸውም። በሰማይም አቀባበል ይደረግላቸዋል። ብዙ ጊዜ ልጆቻቸው በትምህርትም ሆነ በሌሎች ጉዳዮች ከአጠገባቸው ሲርቁ ትልቁ የወላጆች ጭንቀት ባይመቻቸውስ፣ ቢጎሰቁሉስ፣ ፊት ቢነሷቸውስ፣ ክፉ ነገር ቢያገኛቸውስ ... የሚሉት ናቸው። ይሁን እንጂ ከዚህ ዓለም አንቀላፍተው ወደ አምላካቸው ስለ ሄዱት ሕፃናት ግን እንዲህ ብለው ሊያስቡ አይችሉም፡፡ ምክንያቱም ልጆቻቸው ርቀው የሄዱት አመሉን በየሰከንዱ እየቀያየረ ከሚያስቸግር እንግዳ ሰው ዘንድ ሳይሆን፣ በጎነቱ ተሰፍሮ የማያልቅ ቸርነቱ የማይለወጥ ፈጣሪያቸው ጋር ነው። ከእርሱ ጋር ሆነው ማን ያስፈራቸዋል? ማንስ ያስደነግጣቸዋል?!

ሕፃናት የሞቱባቸው ወላጆች ከሚጸጸቱባቸው ምክንያቶች ውስጥ ‹ያለ ጊዜው› መሞታቸውና ልጆቻቸውን አድገው አለማየታቸው ነው፡፡ ይሁን እንጂ የሰውን ሁሉ የዕድሜ ዝርዝር ሰንጠረዥ በእጅ የጨበጡ ይመስል ‹ያለ ጊዜው ነው› እያሉ በድፍረት መናገር አግባብ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ያለ ጊዜው የሚያደርገው ሕይወትም ሞትም የለም፡፡ ነገሩ እኛ በምናስበው ጊዜ ስላልሆነ ‹ያለ ጊዜው›/‹ያልጠበቅነው ነው› ብለን እየተናገርን ካልሆነ በቀር፣ ለእርሱ ሁሉን የሚያከናውንበት ‹‹የሥራ ጊዜ አለው››፡፡(መዝ 119፡126)

"አድጎ ሳላየው" ስለሚለው ጸጸትም፣ እውነት ነው የሕፃናትን እድገት ማየት ደስ ያሰኛል፡፡ ነገር ግን ዋናው ቁም ነገር የልጁ ማደግ ሳይሆን አድጎ የሚኖረው ሰብእና ነው፡፡ የዛሬው ንጹሕ ሕፃን ነገ ሲጎለምስ ቀማኛ እና ደም አፍሳሽ ከሆነ ማደጉ የሚያስቆጭ ይሆናል፡፡ ዛሬ በሕይወት ያሉ ሕፃናት ነገ አድገው ምን ዓይነት ሰዎች እንደሚሆኑ ገና አልታወቀም። "ልጄ በዚሁ በጎነቱ ይቀጥል ይሆን? ወይስ ነገ ከአጉል ሰዎች ጋር ገጥሞ ክፋት ያስተምሩብኝ ይሆን?" የሚለው የብዙ ወላጆች የየቀን ሐሳብ ነው። ሕፃን ልጁ የሞተበት ወላጅ ግን ስለዚህ ነገር አይጨነቅም። የተፈጥሮ ንጽሕናውን ሳያጣ ክፋትን የሚጸየፉ የቅዱሳን ማኅበር ካሉበት፣ የጨለማ ወሬ ከማይወራበት ሰማያዊ እልፍኝ አንድ ጊዜ ገብቶለታልና።

በሕፃናት ልጆች ሞት ከመጠን በላይ ማዘንና በፈጣሪ ላይ መቆጣትን ቅዱሳን አበው በጽኑዕ ያወግዛሉ። በተለይ ቅዱስ ዮሐንስ አፈርቅ በፈጣሪ ላይ የሚደረገው ማጉረምረም "ትልቅ ኃጢአት" እንደ ሆነ ይገልጻል። ድርጊቱም የአምላክን ሥራ ፍጹምነት አለመቀበል በመሆኑ ፈጣሪን ከመስደብ አይተናነስም ይለናል።

ሰባት ወንዶች እንዲሁም ሦስት ሴቶች ልጆቹን በቅጽበት ሲያጣ ፈጣሪውን ያላማረረ ጻድቁ ኢዮብን እስኪ ለአፍታ እናስበው፡፡ ልጆቻቸውን ያጡ ወይም የሚያጡ ብዙ ወላጆች ልጆቹ ከመሞታቸው በፊት የመጨረሻ ቃላቸውን የመስማት፣ እጆቻቸውን የማሻሸትና ጥልቅ በሆነ ቤተሰባዊ ፍቅር የመሳም፣ ከሞቱም በኋላ እንደ ሥርዓቱ ዓይኖቻቸውን የመክደን እና አስከሬናቸውን አጥቦ የመገነዝ እድል አላቸው። ጻድቁ ኢዮብ ግን ከእነዚህ ውስጥ አንዱን እንኳን አላገኘም። ልጆቹ በታላቅ ወንድማቸው ቤት ሲበሉና ሲጠጡ ድንገት ዐውሎ ነፋስ ተነሥቶ ቤቱን ደርምሶ ስለ ገደላቸው እነርሱን ተንከባክቦ የማስታመም እድል አላገኘም። ነፍሳቸውም በወጣችበት ደቂቃ ዓይኖቻቸውን አልከደነም፡፡ የሞቱት ድንጋይ ተጭኗቸው ስለሆነና አስከሬናቸውን ለማውጣት በሚደረገው ቁፋሮ ወቅት አንዳንዶቹ ሕዋሳቶቻቸው በጣም ስለሚጎዱ ሙሉ አካላቸውን የመቅበሩ ነገር ያጠራጥራል፡፡ ታዲያ እነዚህ ሁሉ መከራዎች በአንድ ጊዜ ቢደራረቡበትም ጻድቁ ኢዮብ ግን ‹‹እግዚአብሔርን አልሰደበም፣ መላእክትን አልረገመም››። ይልቅ ወደ ምድር ሰግዶ ‹‹እግዚአብሔር ሰጠ፣ እግዚአብሔርም ነሣ፤ የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን›› ብሎ አምላኩን አመሰገነ። ትንሣኤ ባልተሰበከበት፣ የሰው ተስፋ በቀጨጨበት፣ ሞት ጥላውን ባጠላበት በኦሪት ዘመን የነበረ ኢዮብ እነዚያን ሁሉ ልጆች በአንድ ጊዜ አጥቶ እንዲህ ካመሰገነ፣ ስለ ትንሣኤው የተማርንና "የሙታንን መነሣት ተስፉ እናደርጋለን" ብለን የምንጸልይ፣ የኢዮብን ሩብ ያህል እንኳን መከራ ያልደረሰብን እኛ የሐዲስ ኪዳን ምእመናን ምን ያህል አመስጋኞች ልንሆን በተገባን?

ልጆቻቸው በለጋነት እድሜያቸው የሞቱባቸው ወላጆች ‹‹ልጅህን ሠዋልኝ›› ተብሎ ሲጠየቅ ፈጣሪው ላይ ያላጉረመረመ አብርሃምን ሊያስቡ ይገባቸዋል። የገዛ ልጁን በገዛ እጁ መሥዋዕት አድርጎ እንዲያቀርብለት የተጠየቀው አብርሃም በፈጣሪው ላይ አልተቆጣም። "አባት ያደረከኝ የልጄ ገዳይ እንድሆን ነውን? ከዚህ ሁሉ ባትሰጠኝ በተሻለ ነበር" አላለም። "ከይስሐቅ በሚወለዱት ልጆች ዘርህን አበዛለሁ ብለኸኝ አልነበር። ታዲያ ዛፉን ነቅለህ እንዴት ፍሬውን ልትሰጥ ትችላለህ?" እያለም ፈጣሪውን አልተፈታተነም። አብርሃም ልጁ ይስሐቅን የመሥዋዕት እንጨት አሸክሞት ሲሄድ፣ ‹‹የመሥዋዕቱ በግ ግን
99 viewsወሰንየለው ባህሩ, 19:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 16:41:35 የተበተነ ሕሊና

አንድ ወጣት መነኩሴ አረጋውያኑን ልቡናዬ ይታወክብኛል በበአቴ መቀመጥ አልቻልኩም ስለዚህ ነገርም አዝናለሁ ብሎ ጠየቃቸው። ሽማግሌው መነኩሴም በበአትህ ተቀመጥ ሐሳብህም ወደ አንተ ይመለሳል አለው። አህያዋ የታሰረች ከሆነች ውርንጭላዋ ከቦታ ወደ ቦታ ይዘላል። በራቀ ጊዜም ወደ እናቱ ይመለሳል። እንደዚኹም ሐሳባችን በራሳችን ላይ ይነሣብናል ስለ እግዚአብሔር ብለን ከታገስን በጊዜው ቢበተን ወደ ባለቤቱ ይመለሳል ጸጥም ይላል። 

+++++
ከአባቶች መነኮሳት አንዱ እንዲህ ብሎ ጠየቀ ለምን ልቤን ያስጨንቀኛል ልቡናዬ ይጨነቃል። አንድ ቀን እንኳ አርፍ ዘንድ አይተወኝም። ስለዚኽ ነገር ነፍሴ ታዝናለች። ሽማግሌውም አለው:- ሰይጣን እንዲኽ ያለ ሐሳብ ሊያሳድርብህ ወደ አንተ ሲመጣ አትመልስለት የተለያዩ ቃላትን ያሳድርና ያበሳጭሃል። ነገር ግን መግዛት አይቻለውም። ትቀበለው ዘንድ አንዲቱን እንኳ ላንተ አያዝም (አንተን ማስገደድ አይችልም)። ….

መነኩሴውም ይኽ ነገር ይርቅልኝ ዘንድ እጸልያለው እሰግዳለሁ ነገር ግን ልቤ አያርፍም የምለውን (በቃሌ የምጸልየውን) አላውቅምና። ሽማግሌውም አለው ልጄ አንተ የምትችለውን ያህል አንብብ (ጸልይ) አባ ሙሴና ሌሎች አባቶችን ሁሉ ይኽንን ነገር ሲሉ ሰምቸዋለሁና። ሰነፍ ሰው የያዘውን የቃሉን ትርጓሜ አያውቀውምና ተበሳጭቶ ይተዋል። ነገር ግን እኛ የምንለውን (የምንጸልየውን) ካላወቅን ሰይጣን ቃላችንን ያውቃልና አፍሮ ከእኛ ይሸሻል አለው። 

መጽሐፈ ገነት

መ/ር ንዋይ ካሳሁን

https://t.me/akanim1wasen2
276 viewsወሰንየለው ባህሩ, 13:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ