Get Mystery Box with random crypto!

የተበተነ ሕሊና አንድ ወጣት መነኩሴ አረጋውያኑን ልቡናዬ ይታወክብኛል በበአቴ መቀመጥ አልቻልኩም | ጸያሔ ፍኖት

የተበተነ ሕሊና

አንድ ወጣት መነኩሴ አረጋውያኑን ልቡናዬ ይታወክብኛል በበአቴ መቀመጥ አልቻልኩም ስለዚህ ነገርም አዝናለሁ ብሎ ጠየቃቸው። ሽማግሌው መነኩሴም በበአትህ ተቀመጥ ሐሳብህም ወደ አንተ ይመለሳል አለው። አህያዋ የታሰረች ከሆነች ውርንጭላዋ ከቦታ ወደ ቦታ ይዘላል። በራቀ ጊዜም ወደ እናቱ ይመለሳል። እንደዚኹም ሐሳባችን በራሳችን ላይ ይነሣብናል ስለ እግዚአብሔር ብለን ከታገስን በጊዜው ቢበተን ወደ ባለቤቱ ይመለሳል ጸጥም ይላል። 

+++++
ከአባቶች መነኮሳት አንዱ እንዲህ ብሎ ጠየቀ ለምን ልቤን ያስጨንቀኛል ልቡናዬ ይጨነቃል። አንድ ቀን እንኳ አርፍ ዘንድ አይተወኝም። ስለዚኽ ነገር ነፍሴ ታዝናለች። ሽማግሌውም አለው:- ሰይጣን እንዲኽ ያለ ሐሳብ ሊያሳድርብህ ወደ አንተ ሲመጣ አትመልስለት የተለያዩ ቃላትን ያሳድርና ያበሳጭሃል። ነገር ግን መግዛት አይቻለውም። ትቀበለው ዘንድ አንዲቱን እንኳ ላንተ አያዝም (አንተን ማስገደድ አይችልም)። ….

መነኩሴውም ይኽ ነገር ይርቅልኝ ዘንድ እጸልያለው እሰግዳለሁ ነገር ግን ልቤ አያርፍም የምለውን (በቃሌ የምጸልየውን) አላውቅምና። ሽማግሌውም አለው ልጄ አንተ የምትችለውን ያህል አንብብ (ጸልይ) አባ ሙሴና ሌሎች አባቶችን ሁሉ ይኽንን ነገር ሲሉ ሰምቸዋለሁና። ሰነፍ ሰው የያዘውን የቃሉን ትርጓሜ አያውቀውምና ተበሳጭቶ ይተዋል። ነገር ግን እኛ የምንለውን (የምንጸልየውን) ካላወቅን ሰይጣን ቃላችንን ያውቃልና አፍሮ ከእኛ ይሸሻል አለው። 

መጽሐፈ ገነት

መ/ር ንዋይ ካሳሁን

https://t.me/akanim1wasen2