Get Mystery Box with random crypto!

‍ 'ሀፍሲ' ክፍል ሁለት ፀሀፊ፦ ኑዕማን ኢድሪስ '... ሀፍሲ ላገባሽ እፈልጋለሁ። ታገቢኛለሽ? | || Sᴇʟʟᴜ ᴀʟʟᴇ ɴᴇʙɪʏ ﷺ ||

‍ "ሀፍሲ"
ክፍል ሁለት
ፀሀፊ፦ ኑዕማን ኢድሪስ

"... ሀፍሲ ላገባሽ እፈልጋለሁ። ታገቢኛለሽ?" ብሎ ጠየቃት።
በጣም ፈራች። ኡስማን እስካሁን ከምታዉቃቸዉ ወንዶች ሁሉ የተሻለ ነዉ። አላማ ያለዉ፤ ዲኑን የሚኻድም፤ የዱንያ ሪዝቅም የማይጎለዉ ሊወደድ የሚችል ወንድ ነዉ። ነገር ግን ይሄንን ጥያቄ ከዚህ በፊት ይጠይቃት እንጂ ተመሳሳይ ጥያቄዎች በቤተሰቧችና በጓደኟቿ በኩል ስለሚመጡ የኡስማንን ጥያቄ አስታዉሳዉ አታቅም።
"... ኡስሚ" አለች እየፈራች። "እስካሁን ከማዉቃቸዉ ወንዶች አንተ የተሻልክ ነክ ቢሆንም በዚህ አመት ተመራቂ ተማሪ እንደሆንኩ ታዉቃለህ። በዚያ ላይ የጀመዓዉ ስራም ስላለ ጊዜ ከመጣበቡ የተነሳ ያንተ ጥያቄ ትዝ ብሎኝ አያዉቅም። በጣም ይቅርታ ኡስሚ አሁን ግን ልረዳክ እፈልጋለሁ ጊዜ ስጠኝ ልሰብበትና ቀጣይ ወር ስንገናኝ መልሱን እነግረሀለሁ።" ብላዉ ከተቀመጠችበት እየተነሳች "ኡስሚ ሳሪ እየጠበቀችኝ ነዉ ልሂድ"
"እሺ ሂጂ አታስቁሚያት ስንገናኝ ግን መልስሽን እጠብቃለሁ።" ብሏት ተሰነባብተዉ ከቢሮዉ ወጣች።

ኡስማን ሀፍሲን ሲበዛ ይወዳታል። እሷን የማያስብበትና የማይመኝበት አንዲትም ደቂቃ አታልፍም። ነገር ግን ግኑኝነታቸዉ በሀላል እንዲሆን ስለሚፈልግ ለትዳር ከመጠየቅ ዉጭ ለስራ ሲደዋወሉም ሆነ ሲገናኙ በጣም ጥንቃቄ ያደርጋል።

... ለረጅም ሰአት ቢሮ ዉስጥ ተቀምጦ "ቀጣይ ወር ስንገናኝ ምን ትመልስልኝ ይሆን?" እያለ ያስባል። ረጅሙን የሀሳብ ጉዞ ተጉዞ ሀፍሲ እሱን ለማግባት ፍቃደኛ ሁና፤ ሽማግሌ ልኮ፤ አግብቷት፤ በደስታ የፍቅር ህይወት እየኖሩ፤ ሚያማማሩ ልጆች ወልደዉ ከልጆቻቸዉ ጋር አብረዉ እየተጫወቱ፤  የሞቀ ቤት ዉስጥ የሞቀ ፍቅር እየተጎነጩ ....... በመሀል ብንን አለና በራሱ ተገረመ። "ሰዉ ተኝቶ ብቻ ሳይሆን ቆሞም ያልማል" ብሎ በመደነቅ ፈገገ። እንደገና መለስ ብሎ ያለመዉ ሁሉ እዉን እንዲሆንለት አንገቱን ወደ ላይ ቀና በማድረግ "ኢላሂ ምርጫዋ አድርገኝና ምኞቴን አሳካልኝ" ዱዐ አደረገ።

... ቀናቶች እየሄዱ ነዉ። ሀፍሷ ተመራቂ ተማሪ በመሆኗ ጥናቴዊ ፅሁፏ ላይ ሙሉ ቀኗን ታሳልፍለች። ማታ ደግሞ ለጀመዓዉ ገቢ እንዴት ማሰባሰብ እንዳለባት በማሰብ እናትና አባቷን በኸይር ስራዉ ላይ ታሳትፍቸዋለች። ታማክራቸዋለች። የሀፍሲ አባት ነጋዴ ስለሆነ ሀብታም ከሚባሉት ዉስጥ ነዉ። ብዙ አህለል ኸይራቶችንም በአባቷና በአባቷ ጓደኞች በኩል ስለምታገኝ ገቢ በማሰባሰቡ ረገድ ሀፍሲ የጀመዓዉ የጀርባ አጥንት ነች።
በዚህ ወር ብቻ በሷ በኩል እስከ ስድሳ ሺህ ብር መሰብሰብ ስለቻለች በሹራዉ ወቅት የምታቀርበዉን ሪፖርት በማዘጋጀት ላይ ነች።

ሪፖርቱን በፅሁፍም ጭምር ስለሆነ የሚያቀርቡት ከምሽቱ ሁለት ሰአት አከባቢ አልጋዋ ላይ ተቀምጣ ላፕቶፗን ከፈተች። ነገር ግን ቀኑን ሙሉ ለጥናታዊ ፅሁፏ መረጃ ለማግኘት ቃለ-መጠይቅ ስታደርግ ስለዋለች ድክም ብሏታል። መጻፍ ግዴታ ስለሆነ ብቻ ትንሽ ለመጻፍ እየሞከረች ተንቀሳቃሽ ስልኳ አቃጨለ " ላ ላ  ላ ነህታጁል ማላ ከይነዝዳዱ ጀማላ..." የሚለዉ የሀሙድ ነሽዳ ነበር። ስልኳን ስትመለከተዉ የኡስማን ቁጥር ነበር።
"ሄሎ ኡስሚ"
"አሰላሙዓለይኩም ሀፍሲ"
"ወአለይከሰላም" ... ሰላምታ ከተለዋወጡ በኃላ
"ሀፍሲ እሁድ ጧት 2:30 ሹራ አለ። መቅረት አይቻለም።" ብሎ ቆፍጠን ያለ ትእዛዝ አስተላለፈ።
"እ ዛሬ ቀኑ ማን ነዉ?" ሁኔታዎች ከመደራረባቸዉ የተነሳ ቀኑ ሁሉ ጠፍቶባታል።
"አሁን ጁመዓ ሚረሳ ቀን ነዉ?"
"እ.. እሺ ትንሽ ቢዚ ስለሆንኩ ነዉ ኡስሚ አልቀርም ኢንሻ አላህ!" ብላዉ ተሰነባበቱ። ደክሟትም ስለነበር ብዙም ሳታናግረዉ፤ የጀመረችዉን ፅሁፍ ሳትጨርስ እንቅልፍ ተኛች።
.
.
.
... ዛሬ እሁድ ነዉ። ሀፍሲ ማቅረብ ያሉባት ሁለት ሪፖርቶች አሉ። አንደኛዉን በደንብ አድርጋ ፅፋለች። ሁለተኛዉን ግን ወሩን ሙሉ ረስታዉ ወደ ሹራ ለመሄድ ከቤት ስትነሳ ነዉ ያስታወሰችዉ። በራሷ አፈረች። "በቁም ነገር ጠይቆኝ እንዴት ስለሱ ማሰብ አቃተኝ?" ብላ ራሷን ወቀሰች።  ትንሽ ከተረጋጋች በኃላ እንደገና ስላቀረበላት ጥያቄ ማሰብ ጀመረች። አስር ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ዉስጥ ግን መልሷ "አይሆንም" እንደሆነ ወሰነች!። መግደርደርም ሆነ እሱን ማስጠበቅ አልፈለገችም። "ለሱ  ከወንድምነትና ከጀመዓ አሚርነት የዘለለ አመለካከት የለኝም። ስለዚህ አልሆነዉም!።"

ሸኽ አጃዒቡ፣ ኡስማን፣ ሀፍሲ፣ ሙቤና ነኢማ በሹራ ሰአት ቀጠሯቸዉን አክብረዉ የተገኙ ሲሆን ሳሪና አዲሱ እንግዳ ዴቭ እየተጠበቁ ነዉ። ሁለቱ እስከሚመጡ ብለዉ ሸኽ አጃኢቡ ቀልድና ቁም ነገሩን እያዋዙ ያስቋቸዋል።
"ልጆቼ በስህተት መንገድ ላይ ያለን ሰዉ ስትመልሱ ሂክማን ተጠቀሙ..." ሸኽ አጃኢቡ አብዛኛዉ ሰዉ የሚያዉቃቸዉ ወጣቶችን ለስለስ ባለአንደበት ሲገስፁ፤ አንዳንዴም በቀልድ መልክ ጎንተል እያደረጉ ሲመክሩ ነዉ። ታድያ ሂክማን አብዘተዉ ይወዷታል።
"... አንድዎ ሸኽ ዘንዳ የኔ ቢጤ ደረሳ መፅሀፍ ተወሶ ሲመልስላቸዉ ኪታቡ ወጥ በወጥ አድርጎት ነበር። ታዲያ እኚህ ሸኽ ወጣቱን ክፉ ንግግር አልተናገሩቱም። እሱ እንዳስቀየማቸዉ እሳቸዉ አላስቀየሙትም። ዳግመኛ መፅሀፍ  ለመዋስ ሲመጣ የጠየቃቸዉን መፅሀፍ ሲሰጡት ከመጽሀፉ ጋር አክለዉ የወጥ ማድረጊያ ሰሀን ሰጡት... ማስተማር ማለት እንዲህም አይደል።" ብለዉ ለራሳቸዉ ፈገግ አሉ።

በመሃል ሳሪ "አሰላሙዓለይኩም" ብላ ወደ ቢሮ ገባች። ሁሉም አንድ ላይ "ወአለይኩም ሰላም" ብለዉ መለሱ። ሳሪ ከኃላዋ አስከትላዉ የገባችዉ ዴቭ ገና ሲገባ ነበር ትንሿን ቢሮ በተቀባዉ ሽቶ ያወዳት። ሁሉም አይናቸዉ እሱ ላይ አረፈ። በተለይ ሀፍሲ ፈዛ ቀረች። ክፍት ወደሆነዉ ወንበር ሂዶ እስከሚቀመጥ ድረስ አይኖቿን መንቀል አልቻለችም።

ክፍል ሶስት ይቀጥላል.....

 @SELLU_RESUL
@SELLU_RESUL
SHARE