Get Mystery Box with random crypto!

┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓                  '. #ሀፍሲ '.    ✎ፀሐፊ፦ መግፊራ ቢን | || Sᴇʟʟᴜ ᴀʟʟᴇ ɴᴇʙɪʏ ﷺ ||

┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓
                 ". #ሀፍሲ ".
   ✎ፀሐፊ፦ መግፊራ ቢንት ፉላን
┗─━─━─━∞◆∞━─━─━─┛
              #እውነተኛ_ታሪክ
┎━─━─━─━─━─━─━─━─━┒

        . ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.
┖━─━─━─━─━─━─━─━─━┚
@SELLU_RESUL
┯━━━━━▧▣▧━━━━━┯
        #ክፍል_አንድ ʕ❶ʔ
┷━━━━━▧▣▧━━━━━┷

ፒፕፕፕፕፕፕፕፕፕፕፕ......................የታክሲው ጩሀት ከገባችበት ሀሳብ አባነናት ፤ወዴት መሄድ እንዳለባት እንኳን በቅጡ ሳትወስን ነበር ከቤቷ ብድግ ብላ የወጣችው። ለካንስ በሀሳብ ባህር ውስጥ ሰምጣ፤ አስፋልት መሀል ገብታለች፤ ምን ልትሰራ እዚህ መጣች? እሷም አታውቀውም እግሯን ተከትላ ለጊዜው አስፋልት መሀል ተገኝታለች፤ ልቧ እና አእምሮዋ ተጣልተውባት በእግሯ መመራት ከጀመረች ይሀው እንደቀልድ 5 ወር ሆናት። ከመኪና አደጋ ስታመልጥ ይህ የመጀመርያዋ አደለም፤ ጀሊሉ በቁድራዉ ይሸፍናታል እንጂ እንደሷማ ቢሆን ይሄኔ ቤተሰቦቿ እሷን በማስታመም እየማቀቁ ወይ ሰደቃ ሊያወጡላት ደረታቸው እየደቁ ነበር።
አይ ሀፍሲ ምን ይሆን እንደዚ ከጥንካሬሽ ማማ አውርዶ ዘጭ ያደረገሽ??
...............................................................................
ሀፍሳ ትባላለች በሰፈር ስሟ (ፈንዲሻዬ)  በጣም ሳቂታ ስለነበረች የሰፈር ሰው ሁላ ተስማምተው ያፀደቁት ሁለተኛ ስሟ ነው ከልጅነቷ ጀምሮ ጠንካራ ጥሩ ፀባይ ያላት ሰው አክባሪ ታዛዥ......... በቃ ጥሩ የተባሉ ነገሮች ሁላ እሷ ላይ አሉ ለቤተሰቦቿ የመጨረሻ ልጅ ለዚያውም ብቸኛ ሴት ናት እናቷ እድሌ ብለው ይጠሯታል አባቷ ደግሞ መድመቂያዬ ይሏታል ወንድሞቿ ለሰከንድ ተከፍታ አይደለም ደብሯት ማየት አይፈልጉም አለም ትገልበጥልኝ ካለች አለምን ለመገልበጥ ማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም ልጅቷ ሀፍሲ ናታ የቤቱ እንቁ የቤቱ ድመቀት......................................
እሷ ግን እንደዚ አልነበረችም ቤተሰቦቿ እንዳቀበጧት ቀበጥ አይደለችም ጠንካራ ሴት መሆን የልጅነት ህልሟ ስለነበር አሁን እስካለችበት የአምስተኛ አመት የህክምና ትምህርቷ ድረስ ውጤቷን ለማንም ያላስደፈረች በት/ት ቤትም በኮሌጅ ቆይታዋም የተመሰገነች ጎበዝ ተማሪ ነበረች እናት እና አባቷ ዩኒቨርስቲ ገብታ እንድትመረቅ ቢፈልጉም የወንድ ልጆቻቸው ሀሳብ አሸንፎ ከፍተኛ ውጤት ብታመጣም እዚው አ.አ ቀርታለች የእድሜ እኩዮቿ በቤተሰቦቻቸው ሲመከሩ የሀጂ መሀመድን ልጅ አታይም እስቲ እንደሷ ሁኚ እየተባሉ ነበር።
..........................................................................

ሀፍሲ ለመጀመርያ ጊዜ ትጎዳለች፤ ከትምህርቷ ያዘናጋታል፤ አረ እንደውም ፀባይ ሁላ ልትቀይር ትችላለች፤ ተብሎ በቤተሰብም፤ በዘመድ አዝማድ፤ በሰፈርሰ ው፤ አጠቃላይ በሚያውቃት ሁሉ ተፈርቶ የነበረው የ1ኛ አመት ተማሪ ሆና አባቷ ጋሽ መሀመድ ሲሞቱ ነበር። ሀፍሲ ግን ሰው እንደጠበቃት አልነበረችም እንደውም ወንድሞቿን ተቆጪ እናቷን "ሰብር አድርጊ" ብላ ስታፅናና ነበር። "ለአባቴ ዱዐ እንጂ ለቅሶ አያስፈልገውም፤የሚወደው ይቅራለት፤ ዱዐ ያድርግለት" ብላ ሚያለቅሱትን ሁላ እያስቆመች በምትኩ ቁርዐን ትሰጣቸው ነበር።  "ሀዘኗን በውስጧ ይዛ ቤተሰቡን ለማፅናናት ነው እንጂ ሀፍሳማ ያባቷ ነገር እንዲ በቀላሉ አይወጣላትም" እያሉ ብዙዎቹ በግርምትም በማዘንም አምተዋታል። አንዳንዶቹ እናቷ ጋ እየመጡ "ዋ ይቺ ልጅሽን ተይ በያት ሀዘን በውስጧ አምቃ ቡሀላ የሆነ ነገር እንዳትሆንብሽ፤ አልቅሳ ቢወጣላት ነው ሚሻለው!" ብለው ስሞታ አቅርበዋል ሀፍሲ ግን ወይ ፍንክች ሀዘን ማመቅ የለ፤ መጎዳት የለ፤ ጠንክራ ቤተሰቡን ያጠነከረች ጀግና ሆነች፤ ቆይታ ሀዘኗን ይዛ እንዳትባል ይሀው አባቷ ከሞቱ 3 አመት አለፋቸው። ሀፍሲ ግን የድሮዋ ሀፍሲ ነበረች።
እና ዛሬስ ሀፍሲን ሚሰብር በሀሳብ የሚያዋዥቅ ከራሷ ሚያጣላ ምን ገጥሞት ይሆን .............
╬╬═════════════╬╬
   #ክፍል_ሁለት ʕ❷ʔ ይቀጥላል
╬╬═════════════╬╬

ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ።
               . ↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴

@SELLU_RESUL
SHARE