Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም አለይክ TUBE

የቴሌግራም ቻናል አርማ selewatulah_aleyk — ሰላም አለይክ TUBE
የቴሌግራም ቻናል አርማ selewatulah_aleyk — ሰላም አለይክ TUBE
የሰርጥ አድራሻ: @selewatulah_aleyk
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 619
የሰርጥ መግለጫ

بسم الله الرحمن الرحيم
السلام عليكم ورحمت الله
በዚህ የቴሌግራም ቻናላችን ላይ ኢንሻ አላህ የተለያዩ ተከታታይ ደርሶችን እንማማርበታለን ።
✍ተውሂድ የሌለው ሰው ምንም አይነት ምቹ ሂወት ቢኖረውም ነፍሱ እየዞለመ ነው የሚኖረው ነፍስ የምትረካው የምትደሰተው ተውሂድን ስታገኝ ነው
وَلَهُ كُلُّ شَيْءٍ
አላህ ተጠቃሚ ያድርገን ።
ኢብኑ ሱለይማን

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-19 17:22:00 አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ  እባኮቹ  እዚህ ቻናል ላይ እየገባቹ Subscrib like coment በማረግ አበረታቱኝ እዚህ ቻናል ላይ
ማራኪ ቁርአን
የንፅፅር ትምህርት
የቴክኖሎጂ መረጃዎች
ስለ ኮምፒውተር
ስለ ስልክ
እና የተለያዩ ዳእዋዎች ሙሀደራዎቾ ይለቀቃሉ ይቀላቀላሉን



39 views𝚊𝚙𝚙 𝚍𝚎𝚟𝚎𝚕𝚘𝚙𝚎𝚛 в𝚒𝚗𝚒𝚢𝚊𝚖𝚒𝚗 𝚜𝚞𝚕𝚎𝚢𝚖𝚊𝚗, 14:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 12:41:04

49 views𝚊𝚙𝚙 𝚍𝚎𝚟𝚎𝚕𝚘𝚙𝚎𝚛 в𝚒𝚗𝚒𝚢𝚊𝚖𝚒𝚗 𝚜𝚞𝚕𝚎𝚢𝚖𝚊𝚗, 09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 07:20:37 ﴿ إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا ﴾

@selewatulah_Aleyk
51 viewssubheneke rebena subhanek, 04:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 13:06:34 ሀያቱ ረሱል ﷺ ክፍል 2
አወላለዳቸው
የተወለዱት የዝሆን አመት (ዓመል ፊል) በመባል ሚታወው ዘመን ነው፡፡ ይህም ዓመት አብረሃ ካዕባን ለማፍረስ የሞከረበት ኣመት ነበር፡፡ አላህም እጅግ በሚያስደንቅ ጥበብና ተአምር ሀሳቡን አምክኖታል፡፡ ይህ በቁርአን ታሪክ ተወስቷል። ነቢዩ ሙሐመድ (ፈይወ) በዚሁ አመት በወርሃ ረቢአል አወል 11ኛው ቀን በእለተ ሰኞ እንደተወለዱ ዘገባዎች ያመለክታሉ።

@Selewatulah_Aleyk
INBOX on telegram @ibn_suleyman01
116 viewsSelewatulah Aleyk, 10:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 21:46:27 ጥቂት አስተምህሮት
ያለ አሳዳሪዋ(ወኪሏ) ፈቃድ ያገባች ማንኛዋም ሴት ጋብቻዋ ውድቅ ነው፡፡

ያለ አንዳች ምክንያት ከባሏ ፍች የጠየቀች ሴት የጀነት ሽታ በሷ ላይ እርም ነው፡፡
ሴት ልጅ ሽቶ ተቀብታ ሰዎች ያሸቱላት ዘንድ በሰዎች አጠገብ ካለፈች እሷ ዝሙተኛ ነች፡፡
110 viewsSelewatulah Aleyk, edited  18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 21:31:30 ወጣቶችን አጋቡ
=============
ወላጆች በልጆቻችሁ ጉዳይ አላህ ፊት ትጠየቃላችሁ። እነርሱ የናንተ ሐቅ እንዳለባቸው ሁሉ፤ እናንተም የነርሱ ሐቅ እንዳለባችሁ አትዘንጉ። ከሐቆቃቸው መካከል አንዱ በጊዜ መሰተር ነው። በተለይ ሴት ልጆች ያሏችሁ፣ በተለይ ኒቃብ ለባሽ ከሆኑ፤ ወላጆች ለነዚህ ልጆቻችሁ ሷሊሕ የትዳር አጋር በጊዜ አፈላልጋችሁ መዳር አለባችሁ።

ከወላጆች በተጨማሪ ትልቅ ወንድም፣ ትንሽ ወንድም፣ ያገባችሁ እህትና ወንድሞች ለታናናሾቻችሁ ጥንዳቸውን መፈለግ አለባችሁ። አባት ባይኖር ኖሮ ወልይ ሆነህ የምትድራት'ኮ አንተ ነህ። እንዳትነግርህ ሐያእ አድርጋ ፈራችህ። እና ራሷ ፈልጋ ታምጣ? ምን እያሰብክ ነው ብሮ? በቃ የራስህን ካገባህ ለሌላው አታስብም? ከወላጆቿና ካንተ ውጭ ይህቺን ልጅ የመዳር ቅድሚያ ኃላፊነት ያለበት ማነው? በዙሪያህ ብዙ ጓደኞች አሉህ። በነርሱ ዙሪያ ብዙ ጓደኛ አላቸው። ይሄን ሰንሰለት ተጠቅመህ ለእህትህ አንድ ሷሊሕ ወንድ አጥተህ ነው?


እናትና አባት ሆይ! ሌላው ቢቀር በእናንተ የእድሜ ክልል ያሉ ሰዎችን ታውቃላችሁ። አንዳቸው ለትዳር የደረሰ ልጅ ካለውና የሚመጣጠኑ፣ መስፈርቱን የሚያሟሉ ከሆነ በግልፅ «ልጅህን ለልጄ!» ማለት ምን ያሳፍራል? የሚያሳፍረውስ በዝሙት ድቃላ አርግዛ አስወረደች ሲባል ወይም ወለደች ሲባል! ፈልጎ ከመዳር ይልቅ ያ ተሻላችሁ እንደ? ነገሮች ከመከሰታቸው በፊት ለምን በአላህ ላይ ተመክታችሁ ሰዋዊ ሰበቦችን አታደርሱም?


ዘመኑ የፊትና ዘመን ነው። የፊትና አቅርቦት በ4ቱም አቅጣጫ የተሟላ ነው። ከቤታችን ሳንወጣ ቁጭ ባልንበት ሁሉ የፊትና አቅርቦት በሽ ነው። አንዳንዱ ፊትና ሲባል የግድ የተሟላውን ዝሙት መፈጸም ብቻ ይመስለዋል። እንደዛ አይደለም ነገሩ። ምላስ ዝሙት ይሠራል፣ እግር ዝሙት ይሠራል፣ እጅ ዝሙት ይሠራል፣ ዓይን ዝሙት ይሠራል፣ ጆሮ ዝሙት ይሠራል። እነዚህ የሰውነት ክፍሎቻችን በተናጠል የሚፈጽሙት ዝሙት ከተደጋገመና ድካውን ካለፈ፤ አንድ ቀን ሁላቸውም በጥምረት የሚፈጽሙት ኦርጂናሉ ዝሙት ይሠራል። ያ እስከሚሆን ነው የምትጠብቁት? አላህን አትፈሩትም?


ልጆቻችሁ ቢከበሩና በጊዜ ተሰትረው ለወግ ማዕረግ ቢበቁ፤ የምትከበሩት እናንተ ናችሁ። አላስፈላጊ ሙድ ውስጥ ገብተው ለብዙ ነገር ይበቃሉ ተብለው በጉጉት ሲጠበቁ የነበሩት ልጆች በዚህ ጉዳይ ተጨናግፈው መክነው ሲቀሩ ውርደቱ ለናንተም ነው። «የእገሌ ልጅ፣ የእግሌ እህት፣ የእገሌ ወንድም…» መባል አለ'ኮ! ታዲያ ምን ትጠብቃላችሁ? እነርሱ አፍ ወጥተው እንዳይነግሯችሁ አፈሩ። እንዳይተዋችሁ ያው ዝምም ሆነ። ጭራሽ ምንም አያሳስቧችሁ። ሐቂቃ አስቡበት!


በተጨማሪም ለገንዘብ ብላችሁ አታጋቡ። አዎ! ዛሬ ላይ ተመርቀሽ ሥራ ስታጪ፣ ዳግም ቤተሰብ ጋ መሆን ሲደብርሽ፣ ጓደኞችሽ ሥራ ይዘውም አግብተው ወልደውም ስትመለከቺ ሊከፋሽ ይችላል። ግን በዚያ ተነሳስተሽ አንድን ሰው ዱንያ ስላየሽበት ብቻ ዘው ብለሽ እሺ ብለሽ አታግቢ። ዱንያ ትሄዳለች፣ ትመጣለች። ለርሷ ብለሽ ዘላቂ መስፈርቶችሽ ላይ ከተንሸራተትሽ፤ ከጊዜ በኋላ ክፍተቶች ጎልተው ይታይሹና እስከ መፋታት ሊደረስ ስለሚችል አስቢበት።


በተረፈ ግን ወላጅ፣ ወንድምና እህት ወዘተ የሌለው ሰው ጓደኛንና መሰል አማራጮችን ይጠቀም። እንዲህ አይነት አማራጮች ከሌሏችሁ ግን፤ መልካም ሰው ብላችሁ ለምታስቡት/ቧት ሸሪዓውን ባማከለ መልኩ ቀጥታ መጠየቅ ትችላላችሁ። ግን በተለይ ሴት ከሆንሽ ከመጠየቅሽ በፊት ስለምትጠይቂው ሰው በቂ መረጃ ይኑርሽ።

የአሁን ጊዜ ሰው ስትጠይቁት ይኮራል፣ ይንቃችኋል። ምናልባትም'ኮ ሌላ ወንድ እንኳን ጠይቀሽው በየት በኩል በጠየቅኳት/ባስጠየቅኳት እያለ ጠብ እርግፍ እያለልሽ ይሆናል። ይሄኛው ግን ቀጥታ ስለጠየቅሽው ብቻ፣ ሳይወጣ ሳይወርድ ስላገኘሽ ብቻ፣ ይንቅሻል። እንዲህ አይነቱ ወንድ ቀድሞውኑም ብስለት ይጎድለዋልና ሞራልሽን እንዳይጎዳው ተቆጠቢ።


ዋናው ቁልፍ ነገር ዱዓእ ነው። ጉዳይን ወደ አላህ ማስጠጋት። ከናንተ የሚጠበቀው ሰበብ ማድረስ ብቻ! ውር ውር ስላላችሁ የሚፈጠር ነገር የለም። ቢፈጠርም አያዋጣም።



አላህ ሸባቦቻችንን ከሐራም ነገር ቆጥቦ በሐላሉ ያብቃቃልን።
112 viewsSelewatulah Aleyk, 18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 19:31:24 ("አድጎ አለ...ማደግ")¡¿


አእምሮ ላሸቀ እውቀት ገደል ገባ፤
ሰብአዊነት ከስሞ በድናችን ሰ'ባ።

በኔ ልታይ ጭዌ ኸልቁ ተሰድሮ፤
ቀብር ላይቀርለት ሊወርድ ተንደርድሮ።

ያረሂም በዝነትህ ከጥመቱ አቅናን፤
ሚበጀውን ማናውቅ ዝንጉ ምስኪኖች ነን።

ቀልባችን ፀለመ በሀሲድ ተሞልቶ፤
መቦረቅን ሻተ የወዳጁን በልቶ።

ምን ክፉ ዘመን ነው!? አልልም በጭራሽ፤
ዘመኑማ ደግ ነው እኛው ሆነን አፍራሽ፤
ጀሊሉማ ያዝናል አይበድል በጭራሽ።
97 viewsSelewatulah Aleyk, 16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 10:00:14
«የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

«በጁምዓ ሌሊትና በጁምዓ ቀን ላይ በእኔ ላይ ሰለዋት ማውረድ አብዙ፣ በእኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ አላህ በእርሱ ላይ አስር ሰለዋት ያወርድለታል።»

ኢማሙ አልባኒ ሀዲሱን ፦ " ሐሰን " ብለውታል።»

@Selewatulah_Aleyk
141 viewsSelewatulah Aleyk, 07:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 09:55:15 ሀያቱ ረሱል ﷺ ክፍል 1

የዘር ሐረጋቸው፡- ሙሐመድ : የዐብደላህ ልጅ፣ የአብዱል
ሙጦሊብ ልጅ፣ የሃሽም ልጅ፣ የመናፍ ልጅ፣ የፈህር (ቁረይሽ) ልጅ፣
የማሊክ ልጅ፣ የነድር ልጅ፣ የኪናነህ ልጅ፣ የዐድናን ልጅ፣ የአላህ ነብይ
እስማዒል ልጅ፣ የአላህ ወዳጅ የኢብራሂም ልጅ።

አላህ ከጥሩ ጎሳ መረጣቸው። የመሐይምነት ዘመን ቆሻሻ ወደ ዘር ግንዳቸው አልገባም። ሙስሊም እንደዘገቡት የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡

አላህ ከእስማዒል ልጆች ፣ ከኪናናህ ልጆች ውስጥም ቁረይሽን፣ ከቁረይሽ ሃሽምን፣ ከበኒ ሃሽም በኩል ደግሞ እኔን መርጧል።' (ሙስሊም ዘግበውታል)

@Selewatulah_Aleyk
INBOX on telegram @ibn_suleyman01
119 viewsSelewatulah Aleyk, edited  06:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 09:15:56
111 viewsSelewatulah Aleyk, 06:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ