Get Mystery Box with random crypto!

('አድጎ አለ...ማደግ')¡¿ አእምሮ ላሸቀ እውቀት ገደል ገባ፤ ሰብአዊነት ከስሞ | ሰላም አለይክ TUBE

("አድጎ አለ...ማደግ")¡¿


አእምሮ ላሸቀ እውቀት ገደል ገባ፤
ሰብአዊነት ከስሞ በድናችን ሰ'ባ።

በኔ ልታይ ጭዌ ኸልቁ ተሰድሮ፤
ቀብር ላይቀርለት ሊወርድ ተንደርድሮ።

ያረሂም በዝነትህ ከጥመቱ አቅናን፤
ሚበጀውን ማናውቅ ዝንጉ ምስኪኖች ነን።

ቀልባችን ፀለመ በሀሲድ ተሞልቶ፤
መቦረቅን ሻተ የወዳጁን በልቶ።

ምን ክፉ ዘመን ነው!? አልልም በጭራሽ፤
ዘመኑማ ደግ ነው እኛው ሆነን አፍራሽ፤
ጀሊሉማ ያዝናል አይበድል በጭራሽ።