Get Mystery Box with random crypto!

ጥቂት ምክር ለኳስ ጨዋታ ተመልካቾች ~ ~ ~~ ~~~~ ~~~ 1. ኳስ እየተመለከትክ ወይም በኳስ | የምስራቅ እስቴ ወረዳ ሰለፍዮች ቻናል።

ጥቂት ምክር ለኳስ ጨዋታ ተመልካቾች
~ ~ ~~ ~~~~ ~~~
1. ኳስ እየተመለከትክ ወይም በኳስ ምክኒያት እንቅልፍህን አጥተህ ሰላት እንዳታሳልፍ!! ልብህ በህይወት ካለ ደወል እየተደወለ ነው፡፡ ስማ!!
فَخَلَفَ مِنْ بَعْدِهِمْ خَلْفٌ أَضَاعُوا الصَّلَاةَ وَاتَّبَعُوا الشَّهَوَاتِ فَسَوْفَ يَلْقَوْنَ غَيًّا
((ከእነርሱም (ከነቢያቱ) በኋላ ሰላትን ያጓደሉ፣ ከንቱ ፍላጎቶችንም የተከተሉ፣ መጥፎ ምትኮች ተተኩ! የጀሀነምንም ሸለቆ በእርግጥም ያገኛሉ!!)) (መርየም፡ 59) አስተውል! አይደለም ስንት አላስፈላጊ ኮተት አጭቆ በያዘው እግር ኳስ ምክኒያት ይቅርና አንድ ሰው በተራዊሕ ሰላት ምክኒያት ማምሸቱ የፈጅር ሰላትን በወቅቱ እንዳይሰግድ የሚያደርገው ከሆነ ተራዊሕ ሰላት መስገዱም አይፈቀድለትም፡፡ በኳስ ምክኒያት እያመሹ የፈጅር ሰላትን ማሳለፉስ ይቻል ይሆን? ብይኑን ለራስህ ትቼዋለሁ፡፡ እስኪ ህሊናህን አዳምጠው፡፡
2. ለኳስ ብለህ የወላጆችን ሐቅ አትጣስ! ቁርኣኑ “ ‘ኦፍ’ አትበሏቸው” ይላል ዛሬ ግን በጋጠ-ወጥ ልጃቸው ሰዐት እላፊ በራቸው ይደበደባል፣ ጎል ገባ ተብሎ ይጮህባቸዋል፡፡ የሚደግፈው ቡድን “ተሸነፈ” ብሎ እየተበሳጨ ይገባባቸዋል፡፡ ካሁን ካሁን ምን አግኝቶት ይሆን እያሉ በስጋት ይጨርሳቸዋል፡፡ … ኧረ ስንቱ! ጌታችን አላህ እንዲህ ይላል፡-
وَقَضَى رَبُّكَ أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا إِيَّاهُ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا إِمَّا يَبْلُغَنَّ عِنْدَكَ الْكِبَرَ أَحَدُهُمَا أَوْ كِلَاهُمَا فَلَا تَقُلْ لَهُمَا أُفٍّ وَلَا تَنْهَرْهُمَا وَقُلْ لَهُمَا قَوْلًا كَرِيمًا (23) وَاخْفِضْ لَهُمَا جَنَاحَ الذُّلِّ مِنَ الرَّحْمَةِ وَقُلْ رَبِّ ارْحَمْهُمَا كَمَا رَبَّيَانِي صَغِيرًا (24)
((ጌታህም (እንዲህ ሲል) አዘዘ፡- “እርሱን እንጂ ሌላን አትገዙ፡፡ በወላጆቻችሁም መልካምን ስሩ፡፡ በአንተ ዘንድ ሆነው አንዳቸው ወይም ሁለታቸው እርጅናን ቢደርሱ “ኦፍ” አትበላቸው፡፡ አትገላምጣቸውም፡፡ ለእነርሱም መልካምን ቃል ተናገራቸው፡፡)) (አልኢስራእ፡ 23-24) ለመሆኑ ልባችን በህይወት አለ? ቁርኣን ሲነበብ የሚደነግጥ ይኖር ይሆን?
3. መሰረታዊ የእምነትህን ድንጋጌዎች ሳትለይ ነጋ ጠባ ኳስ ላይ የምታፈጥ ከሆነ አትጠራጠር ኪሳራ ላይ ነው ያለኸው!! እርግጥ ነው ሸሪዐችን ሐላል በሆኑ ነገር እራስን ዘና ማድረግን አይከለክልም፡፡ ነገር ግን ሐላል በሆነ ነገር ከዋጂብ መዘናጋትን አይፈቅድም፡፡ የእምነቱ ምሰሶ የሆነውን ተውሒድና ከአደጋው ሁሉ የከፋውን የሺርክ አደጋ በቅጡ ሳይለይ፣ ሰለሰላት፣ ሰለፆም፣… ስለሌሎችም መሰረታዊ የዲኑ ክፍሎች እዚህ ግባ የሚባል እውቀት የሌለው ሰው በኳስ ላይ ጊዜውን እንዲያጠፋ የሚፈቅድለት እምነቱ ይቅርና የትኛው ህሊና ነው?! ይሄ ችላ ካላሉት በቀር ብዙም ማሰብ አይጠይቅም፡፡ ማንም የሚደርስበት ግልፅ የሆነ ስሌት ነውና፡፡ “ነገ ከመመርመራችሁ በፊት ዛሬ እራሳችሁን መርምሩ” ይላል ዑመር ኢብኑልኸጣብ፡፡ ከአላህ ፊት ስላጠፋሃው ጊዜ፣ ገንዘብና ወጣትነትህ እንደምትጠየቅ አትርሳ፡፡ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡-
لاَ تَزُولُ قَدَمَا عَبْدٍ يوم القيامة حَتَّى يُسْأَلَ عَنْ خمس، عَنْ عُمْرِهِ فِيمَا أَفْنَاهُ؟ وعن شبابه فيما أبلاه؟ وَمَالِهِ مِنْ أَيْنَ اكْتَسَبَهُ؟ وَفِيمَا أَنْفَقَهُ؟ وماذا عمل فيما علم؟
((የቂያማ እለት ከአምስት ነገሮች ሳይጠየቅ የአንድ ባሪያ እግሮች አይንቀሳቀሱም! እድሜውን በምን እንዳጠፋው፤ ወጣትነቱን በምን እንደጨረሰው፣ ገንዘቡን ከየት እንዳገኘው፤ እና በምን ላይ እንዳዋለው፤ በእውቀቱ ምን እንደሰራበት፤)) አልባኒ “ሰሒሕ ብለውታል፡፡ (አስ-ሰሒሐህ፡ 946)
4. ኳስ እመለከታለሁ ብለህ ከዐጅነቢ ሴቶች ላይ ጋር ተቀላቅለህ አትቀመጥ፣ ከአጅነቢም ላይ አታፍጥጥ!
قُلْ لِلْمُؤْمِنِينَ يَغُضُّوا مِنْ أَبْصَارِهِمْ وَيَحْفَظُوا فُرُوجَهُمْ ذَلِكَ أَزْكَى لَهُمْ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا يَصْنَعُونَ
((ለአማኞችም ንገራቸው፡- ዐይኖቻችሁን (ያልተገባ ነገር ከማየት) ይስበሩ፣ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፣ ይህ ለነሱ የተሻለ ነው፡፡ አላህ በሚሰሩት ሁሉ ውስጥ አዋቂ ነው፡፡)) (አን-ኑር፡ 30) ውድድሩ የሴቶች እግር ኳስ ከሆነ ግን አትጠራጠር በሐራም እየተጨማለቅክ ነው!! ሀፍረተ-ገላቸውን ያልሸፈኑ ሰዎችን እየተከታተልክ ከሆነም ስሜትህ ልቦናህን ሸፍኖት ካልሆነ በስተቀር ሐቁ አይሰወርህም፡፡ ባይሆን እኔ የወንድምነት ሃላፊነቴን አድርሻለሁ! “አላህን ፍራ!!” ብያለሁ፡፡
5. ላንቃህ እስኪበጠስ አትጩህ! ድምፅህን ዝቅ አድርግ፡፡ ወከባ ቀንስ፡፡ ጎረቤት አትረብሽ! ሀያሉ ጌታ አላህ ምን እንደሚል ረጋ ብለህ አስተውል!
وَاقْصِدْ فِي مَشْيِكَ وَاغْضُضْ مِنْ صَوْتِكَ إِنَّ أَنْكَرَ الْأَصْوَاتِ لَصَوْتُ الْحَمِيرِ
((በአካሄድህም መካከለኛ ሁን፡፡ ከድምፅህም ዝቅ አድርግ፡፡ ከድምፆች ሁሉ አስቀያሚው የአህዮች ድምፅ ነውና!!)) (ሉቅማን፡ 19) የቤት ስራ ሰጥቼሃለሁ፡፡ በጮህክ ቁጥር የአህዮችን አስቀያሚ ድምፅ አስታውስ፡፡ ጯሂዎችን አላህ በምን እንደመሰላቸውም በህሊናህ ያዝ፡፡
6. ተረጋጋ!! የምትደግፈው ቡድን ስላሸነፈ አትንቀባረር፡፡ አትጎረር፡፡ ስርኣት አልባ አትሁን! ሀያ ምናምን ወጠምሾች ከሆነ ሜዳ ውስጥ አንዲት ቅሪላ ተከትለው ከመሯሯጣቸው ውጭ ይህን ያክል ጮቤ የሚያስረግጥ ምንም ነገር የለም፡፡
وَلَا تُصَعِّرْ خَدَّكَ لِلنَّاسِ وَلَا تَمْشِ فِي الْأَرْضِ مَرَحًا إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ كُلَّ مُخْتَالٍ فَخُورٍ
((ጉንጭህንም (በኩራት) ከሰዎች አታዙር፡፡ በምድርም ላይ ተንበጥርረህ አትሂድ፡፡ አላህ ተንበጣራሪን ጉረኛን ሁሉ አይወድምና!!) (ሉቅማን፡ 18)
7. ከቡድንና ከጨዋታ ጋር በተያያዘ ለቀልድና ለተረብ እያልክ አትዋሽ!! ውሸት አስቀያሚ ነቀርሳ ነው!! ሰሚ ጆሮ ካለህ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡-
وَيْلٌ لِلَّذِي يُحَدِّثُ بِالْحَدِيثِ لِيُضْحِكَ بِهِ الْقَوْمَ فَيَكْذِبُ وَيْلٌ لَهُ وَيْلٌ لَهُ
((ሰዎችን ለማሳቅ ብሎ እየዋሸ ወሬን የሚያወራ ሰው ወዮለት! ወዮለት! ወዮለት!!)) አልባኒ “ሐሰን” ብለውታል፡፡
8. የኳስ ፍቅርህን ለከት አርግለት፡፡ ለኳስ ብለህ የምትጠላ፣ ለኳስ ብለህ የምትወድ፣ በኳስ ምክኒያት ሐራም ላይ የምትወድቅ፣ በኳስ ምክኒያት እምነታዊ ግዴታዎችን የማትፈፅም ከሆንክ አትጠራጠር ኳሱን ጣኦት አድርገህ ይዘኸዋል ማለት ነው፡፡ መልእክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “የዲናር ባሪያ ጠፋ! የዲርሃም ባሪያ ጠፋ! … ሲሰጡት ይወዳል! ካልሰጡት ይጠላል” ይላሉ፡፡ ዛሬ ኳስ ከገንዘብ ባልተናነሰ ምናልባትም በባሰ ሁኔታ ጣኦት ሆኖ በገሃድ እየታየ ነው፡፡ ይሄ ስሜትን አምላክ ማድረግ ካልሆነ ምን ሊሆን ነው! በሚከተለው አንቀፅ ከተገለፁት