Get Mystery Box with random crypto!

ጥቂት ነጥቦች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ~ ~ ~ ~~~ ~~~~ ~~~~ 1- ቁርኣናችን ማንም የማንንም | የምስራቅ እስቴ ወረዳ ሰለፍዮች ቻናል።

ጥቂት ነጥቦች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ
~ ~ ~ ~~~ ~~~~ ~~~~
1- ቁርኣናችን ማንም የማንንም ወንጀል እንደማይሸከም በግልፅ ያስቀምጣል። የትኛውም ሰው ቢበድለን በዘር ሰንሰለት እያገናኘን በጅምላ ሌሎች ላይ አንፍረድ። በሌሎች ጉዳትም አንደሰት።
2- አቅማችንን እንወቅ። ከአቅማችን በላይ በሆነ ጉዳይ ውስጥ እየገባን አናቡካ። አደብ ይኑረን። እውነት ለመናገር ብዙዎቻችን ሚሊዮኖችን ስለሚያነካካ ጦርነት ቀርቶ በአንፃራዊነት ቀላል ስለሚባሉ የፊቅህ ርእሶች እንኳ ለማውራት አቅም የለንም። ሁሉ ነገር ላይ ሃሳብ ካልሰነዘርን አንበል።
3- ከየብሄሩ የግጭት ተዋንያን ያልሆኑ፣ ግና በግጭቱ ሳቢያ ዘመድ፣ ቤተሰብ የተጎዳባቸው ብዙ ምስኪን ወገኖች እዚሁ ማህበራዊ ሚዲያ ውስጥ አሉ። የምንፅፈውን ያያሉ፣ የምንናገረውን ይሰማሉ። ኢንሻአላህ ይሄ ቀን ያልፋል። ለሚያልፍ ቀን የማያልፍ ቃል አንናገር። ያመጣልንን እያወራን በቁስላቸው ላይ እንጨት እየሰደድን እንዳንጎዳቸው፣ ቅስማቸውን እንዳንሰብር እንጠንቀቅ።
4- በያካባቢው ለፖለቲካ ባይተዋር የሆኑ ወገኖች መርጠው ባልተፈጠሩበት ብሄር የተነሳ ሲሳደዱ ማየት የተለመደ ሆኗል። ከፊሎች ወቅታዊ ፍተሻዎችንና ክትትሎችን ተከትሎ ያለ ወንጀላቸው ለቂም በቀል ጥቃትና ለስግብግብ ጅቦች ሲሳይ ሆነዋል። እነዚህን ወገኖች ብንችል ልናግዛቸው፣ አጥፊዎችን ልናወግዝ ይገባል። እሱ ቢቀር በሞራል እንኳ ከጎናቸው ልንቆም ይገባል። እንጂ ፈፅሞ ለበደል አጋዥ እንዳንሆን መጠንቀቅ አለብን።
5- ከሞቱ፣ ከንብረት ውድመቱ ባሻገር በተለያዩ የሃገራችን ክፍል እልፍ አእላፍ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። ሌሎች ደግሞ መሸሸም ቅንጦት ሆኖ አጣብቂኝ ውስጥ ገብተው ከዛሬ ነገ እልቂትን እየጠበቁ የሰቀቀን ህይወት እየገፉ ነው። 30ሺ እና 40ሺ የሚያወጡ ንብረቶቻቸውን 2ሺ እና 3ሺ እንኳ እንዳይሸጡ ታድሞባቸው እየተንከራተቱ ነው። እነዚህን ወገኖች የምናግዝበት አቅሙ ካለን እናግዛቸው። እሱ ቢቀር ቢያንስ በዱዐ አንርሳቸው።
6- አሰሰ ገሰሱን ሁሉ እየተከታተልን ለጅላጅል የዩቲዩብ ቃራሚዎች መጠቀሚያ አንሁን። ጥላቻን የሚዘሩ ስራዎችን ከማሰራጨት እንቆጠብ። የሴራ ፖለቲካ ከሚተነትኑ ከንቱዎች እንራቅ። ይልቁንም ትኩረታችን ለዱያንም ሆነ ለአኺራ በሚጠቅመን ላይ ይሁን። በዱዓ ላይ እንበርታ።

የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor