Get Mystery Box with random crypto!

ገና ሊለቀቅ ጥቂት ቀናት የቀረውን 'ባርቢ' የተሰኘውን ፊልም ቬትናም በሃገሪቷ እንዳይታይ ከልክላለ | ሰሌዳ | Seleda

ገና ሊለቀቅ ጥቂት ቀናት የቀረውን "ባርቢ" የተሰኘውን ፊልም ቬትናም በሃገሪቷ እንዳይታይ ከልክላለች።

ለምን ሲባል:-

ይህ ምናባዊ-አስቂኝ ፊልም ሊለቀቅ የታሰበው ሐምሌ 14, 2015 ነበር ነገር ግን ከ ፊልም ማስታወቅያው ላይ ባለው አንድ ትእይንት ሊከለከል ችሏል።

ታዲያ ይህ ትእይንት የሚያሳየው የ ቻይናን ካርታ ነበር እናም በካርታው ላይ ዘጠኝ ሰረዞች በቻይና ባህር ላይ አርፈው ይታያሉ እነዚህም ዘጠኝ ሰረዞች የሚያመለክቱት 3 ሚሊዮን ካሬ ኪሎሜትር የሚሸፍን ሃሌታው "ሀ" ቅርጽ ያለው የባህር ክፍል ሲሆን ይህ አካባቢ በ ነዳጅ እና በ ተፈጥሮ ጋዝ የበለጸገ ነው፤ ሆኖም ይህንኑ አከባቢ ቬትናም፣ ፊሊፒንስ፣ ብሩኔይ፣ ማሌዥያ እና ታይዋን ይገባኛል ጥያቄ ለረጅም ጊዜ ሲያቀቡ የቆዩ ቢሆንም ጉልቤዋ ቻይና ግን ጥያቄያቸውን ችላ በማለት በተለያዩ ታላላቅ ሚዲያዎች ላይ እነዚህ መሰመሮች እንዲታዩ እና የቻይና ባለቤትነቱን እንዲለመድ ግፊት እያደረገች ትገኛለች።

በዚህ ትእይንት ደስተኛ ያልሆነው የ ቬትናም ባህልና ቱሪዝም ሚንስቴር ይህ ፊልም በሃገሪቷ ውስጥ ጨርሶ እንዳይታይ አግዷል።