Get Mystery Box with random crypto!

ከዘመዶቼ ይልቅ የምወደው ኔይማር ሀብቴን ይውረስ ያለው ሚሊየነር አንድ ብራዚል ውስጥ የሚገኝ | ሰሌዳ | Seleda

ከዘመዶቼ ይልቅ የምወደው ኔይማር ሀብቴን ይውረስ ያለው ሚሊየነር

አንድ ብራዚል ውስጥ የሚገኝ ልጥጥ ባለሃብት ለኔይማር ካለው ፍቅር የተነሳ ሲሞት ኔይማር ሙሉ ሃብቱን እንዲወርስ መናዘዙ ተሰምቷል።

ባለሀብቱ አጠቃላይ ያለው ንብረት በገንዘብ ሲተመን ወደ 200 ሚሊየን ዶላር  የሚደርስ ሲሆን በኔይማር ላይ የሚደርሱ ትችቶችንም በመቃወም ይታወቃል ተብሏል።

ያለው ይጨመርለታል እንዲሉ አበው ኔይማር አሁን ላይ የገንዘብ እጥረት ያለበት ሰው አይደለም ከፈረንሳዩ ሃብታም ክለብ ፒኤስጂ እንኳ በአመት ወደ 85 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ወደ ካዝናው ያስገባል።

Via - daily mail