Get Mystery Box with random crypto!

የድምፃዊ ብስራት ሱራፌል አልበም የፊታችን አርብ እንደሚወጣ ተነገረ። በሀገራችን የሙዚቃው ኢንዱ | ሰሌዳ | Seleda

የድምፃዊ ብስራት ሱራፌል አልበም የፊታችን አርብ እንደሚወጣ ተነገረ።

በሀገራችን የሙዚቃው ኢንዱስትሪ ውስጥ ስራዎቹን ለሙዚቃ አፍቃሪያን በማድረስ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተደማጭና ታዋቂ ለመሆን የቻለው የበርካታ ግጥምና ዜማ ደራሲ የሆነው ድምፃዊ ብስራት ሱራፌል አበበ 2ተኛ የሙዚቃ አልበም ይዞ መቷል።

"ማለፊያ" የሚል መጠሪያ ያለው ይህ የሙዚቃ አልበም ከአራት አመት በላይ የፈጀ ሲሆን ድምፃዊ ሱራፌል አበበ እና ሌሎች  በኢንዱስትሪው ውስጥ ስመ ጥር የሆኑ ባለሙያዎች  በግጥም በዜማ እንዲሁም በቅንብር አሻራቸውን ያሳረፉበት በርካታ ዝግጅት ሲደረግበት የነበረ ስለመሆኑም በመግለጫው ተገልጿል።

በኤላ ሪከርድስ አማካኝነት ሀምሌ 14  ለአድማጭ ይደርሳል።በሁሉም ዲጂታል ኘላት ፎርም ይገኛል 12 ያክል ትራክ ያለው ሲሆን  አንዳንድ በምስል የተሰሩም እንዳሉ ተመላክቷል።

Via - fastmereja