Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ ያለችበት ወቅታዊ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ የሰራተኞችን ጥያቄ ከመመለስ የሚያግድ እንዳልሆነ ኢሰማ | ሰሌዳ | Seleda

ኢትዮጵያ ያለችበት ወቅታዊ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ የሰራተኞችን ጥያቄ ከመመለስ የሚያግድ እንዳልሆነ ኢሰማኮ አስታወቀ፡፡

ተቀጥረዉ በሚሰሩ ሰራተኞች በርካታ ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች አሉባቸው በሚል በመንግስት በኩል ማስተካከያዎች እዲደረጉ  ጥያቄ ያቀረበው የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት የኢኮኖሚ ሁኔታ የሰራተኞችን ጥያቄ ከመመለስ የሚያግድ እዳልሆነ ለመናኸሪያ ሬድዮ አስታውቋል፡፡

ገንዘብ ሚኒስቴር ለ2016 የበጀት ዓመት ረቂቅ በጀቱን ይፋ ሲያደርግ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ቅጥርን ማስቀረት ጨምሮ ወጪ የሚቀንሱ እርምጃዎችን እንደሚወስድ ማስታወቁን ተከትሎ፤ በኮንፌደሬሽኑ የቀረቡ ጥያቄዎች የሚመለሱበት መንገድ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል ወይ በሚል መናኸሪያ ሬዲዮ ለኮንፌደሬሽኑ ጥያቄ አቅርቧል፡፡ የኮንፌደሬሽኑ ፕሬዘዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ በዚህ ምክንያት መልስ ላያገኝ የማይችል ጥያቄ እንደሌለ ገልጸዋል፡፡

አቶ ካሳሁን አክለውም ከሰራተኞች የሚቆረጠው የገቢ ግብር እንዲቀነስ መጠየቁ መንግስት የሚያገኘው ገቢ ላይ በቀጥታ ተጽዕኖ ቢያሳድርም ጉድለቱን በሌሎች መንገዶች መሙላት ይችላል ብለዉ በዚህም የሰራተኞችን ጥያቄ ለመመለስ የበጀት ጉዳይ ምክንያት ሆኖ መቅረብ እንደሌለበት ጠቁመዋል፡፡