Get Mystery Box with random crypto!

ጣሊያናውያን በኑሮ ውድነት ሳቢያ ምግብ ለመቀነስ ተገደዋል ተባለ ጣሊያናውያን ከፍተኛ ከሆነ የዋ | ሰሌዳ | Seleda

ጣሊያናውያን በኑሮ ውድነት ሳቢያ ምግብ ለመቀነስ ተገደዋል ተባለ

ጣሊያናውያን ከፍተኛ ከሆነ የዋጋ ንረት የተነሳ የምግብ ፍጆታቸውን ለመቀነስ መገደዳቸውን አዲስ የወጣ ሪፖርት አመላክቷል።

የጣሊያን ኢንዱስትሪ ኮንፌዴሬሽን (ኮንፊንዱስትሪያ) ባወጣው ሪፖርት መሰረት እየጨመረ ያለው የዋጋ ንረት ጣሊያናውያን ቤተሰቦች ለምግብ የሚያወጡትን ወጪ እንዲቀንሱ እያደረጋቸው ነው ማለቱን አልአይን ፅፏል።

ሪፖርቱ የጣሊያናውያን ቤተሰቦች የምግብ ፍጆታ ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ መምጣቱን ያመላከተ ሲሆን፤ በፈረንጆቹ 2022 አራተኛ ሩብ ዓመት ላይ ብቻ የምግብ ወጪ ዋጋ በ8.7 በመቶ መቀነሱ ተመላክቷል።

የጣሊያን ብሔራዊ የሸማቾች ህብረት (ዩኤንሲ) ኃላፊ ማሲሚሊያኖ ዶና ሪፖርቱን ጣሊያናውያን መዋግ ንብረት ሳቢያ ምግብ ለመቀነስ መገደዳቸውን “አሳዛኝ” ሲሉ ገልጸዋል።