Get Mystery Box with random crypto!

የኤሌትሪክ መኪና አምራቹ ቴስላ የመኪና ሽያጩ ደርቶልኛል አለ ግዙፉ የኤሌትሪክ መኪና አምራች ቴ | ሰሌዳ | Seleda

የኤሌትሪክ መኪና አምራቹ ቴስላ የመኪና ሽያጩ ደርቶልኛል አለ

ግዙፉ የኤሌትሪክ መኪና አምራች ቴስላ ሽያጩን ለማሳደግ የዋጋ ቅናሽ ካደረገ በኋላ ባለፉት 3 ሶስት ወራት ከ450 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎችን መሸጡን አስታወቀ፡፡

ዋና ስራ አስፈጻሚው ኤሎን መስክን ጠቅሶ ቢቢሲ እንደዘገበው የኩባንያው ሽያጭ ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረ ቢሆንም የጥሬ ዕቃ እና ግብአቶች ወጪ መናር ዓመታዊ ትርፉን በ24 በመቶ እንዲቀንስ አድርጎታል፡፡

ኤሎን መስክ ሌሎች ከፍተኛ የሚባሉት የመኪና አምራቾችም የዋጋ ቅናሽ ያደረጉ ቢሆንም ለቴስላ ኩባንያ ዘላቂነትና ውጤታማነት ግን ብዙ በመሸጥ ዝቅተኛ ትርፍ ማግኘት “የምንጊዜም ትክክለኛ ምርጫ” ነው ማለታቸውን የቢቢሲ ዘገባ አስረድቷል፡፡