Get Mystery Box with random crypto!

የፈረንሳይ አመፀኞች የ ' ቮልስ ዋገን ' ተሽከርካሪ ዘረፉ በፈረንሳይ ሀገር አንድ የ17 ዓመ | ሰሌዳ | Seleda

የፈረንሳይ አመፀኞች የ " ቮልስ ዋገን " ተሽከርካሪ ዘረፉ

በፈረንሳይ ሀገር አንድ የ17 ዓመት ታዳጊ በፖሊስ መገደለን ተከትሎ የተቀሰቀሰው አመፅ አሁንም ቀጥሏል። በዚሁ አመፅ በርካታ ተቋማት ተዘርፈዋል።

በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በታዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎች የአፕል፣ ዛራ፣ ናይክ የመሳሰሉ ትልልቅ ድርጅቶች ዘረፋ ሲፈፀምባቸው ታይቷል።

በተጨማሪም በማርሴ ከተማ አንድ  የ " ቮልስ ዋገን " ተሽከርካሪ መሸጫ በአመፀኞች ሲዘረፍ ታይቷል። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተሰራጨ ተንቀሳቃሽ ምስል ፤ የመኪና መሸጫ ውስጥ የገቡ አመፀኞች አዳዲስ መኪናዎችን እያሽከረከሩ ሲወጡ ይታያል።

ከዚህ ባለፈ በፈረንሳይ አመፀኞች የቤት አስቤዛ በሚሸጥባቸው መደብሮች እየገቡ ዘይትን እና ሌሎች አስቤዛዎችን ዘርፈው ሲወጡ ታይተዋል።