Get Mystery Box with random crypto!

“የልጄን ሕይወት በአንድ ሚሊዮን ብር ገዛሁ” - ልጃቸውን ከእገታ ያስለቀቁ አባት ገንዘብ ለማግ | ሰሌዳ | Seleda

“የልጄን ሕይወት በአንድ ሚሊዮን ብር ገዛሁ” - ልጃቸውን ከእገታ ያስለቀቁ አባት

ገንዘብ ለማግኘት ሲባል ስለሚፈጸሙ እገታዎች መስማት በተለይ በሀገራችን አስደንጋጭነቱ እየቀረ ይመስላል። ተደጋግሞ እየተከሰተ ቤተሰብ ያለውን ሁሉ በማሟጠጥ ከፍሎ ሲያስለቅቅ፣ በአጋቾች እጅ ወጥተው የቀሩ ሰዎችም አሉ።

ልጃቸው የታገተባቸው የምሥራቅ ጎጃሙ ጡረተኛ መምህር ቤታቸውን እንኳን ሸጠው የማይመልሱት ዕዳ ውስጥ በመግባት ልጃቸውን አስለቅቀዋል። እንዴት ልጃቸውን በእጃቸው እንዳስገቡ ሲያስገዱም “በአንድ ሚሊዮን ብር የልጄን ነፍስ ገዛሁ” ብለዋል ለቢቢሲ በሰጡት ቃል።