Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጲያውያኑ አትሌቶች በዳይመንድ ሊጉ ድል ቀንቷቸዋል ትላንት ምሽት በስቶኮልም በተደረገው የ1 | ሰሌዳ | Seleda

ኢትዮጲያውያኑ አትሌቶች በዳይመንድ ሊጉ ድል ቀንቷቸዋል

ትላንት ምሽት በስቶኮልም በተደረገው የ1500 ሜትር የሴቶች ዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጲያውያኑ ከ1ኛ እስከ 3ኛ በመውጣት አሸንፈዋል።

ፍሬወይኒ ኃይሉ ውድድሩን በ1ኛነት ያጠናቀቀች ሲሆን ድሪቤ ወልተጂ እና ሂሩት መሸሻ 2ኛ እና 3ኛ በመሆን አጠናቀዋል።

በዚሁ በስቶኮልም በተደረገው የሴቶች 5 ሺህ ሜትር የሴቶች ውድድር ለምለም ኃይሉ እና መዲና ኢሳ 2ኛ እና 3ኛ በመሆን ገብተዋ።

መዲና ኢሳ የግሏን ሰዓት ማሻሻሏም ታውቋል። በዚህ ውድድር 1ኛ የወጣችው ቢያትሪስ ቼቤት መሆኗን አትሌትክስ አፍሪካ ዘግቧል።