Get Mystery Box with random crypto!

የመቀሌው አይደር ሆስፒታል ሰራተኞቹ በውዝፍ የቤት ኪራይ መቸገራቸውን አስታወቀ፡፡ በሰሜኑ ጦር | ሰሌዳ | Seleda

የመቀሌው አይደር ሆስፒታል ሰራተኞቹ በውዝፍ የቤት ኪራይ መቸገራቸውን አስታወቀ፡፡

በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት በአይደር ሪፈራል ሆስፒታል ያገለግሉ የነበሩ የጤና ባለሙያዎች ለበርካታ ወራት ደሞዝ ስላልተከፈላቸው አሁን ላይ ውዝፍ የቤት ኪራይ ዕዳቸውን መክፈል አልቻሉም ተብሏል።

ሆስፒታሉ ታህሳስ 2015 የ ደሞዝ ክፍያ እስኪጀመር ድረስ ሰራተኞቹ ያለ ደሞዝ በመቆየታቸው ለተደራራቢ ችግር እንደተጋለጡ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል።

ሆስፒታሉ የሰራተኞቹን ችግር ለመፍታት ለፌደራል መንግስቱ ጥያቄያ ቢያቀርብም መፍትሄ እንዳልተሰጠው የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር አብረሃ ገብረመድን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።