Get Mystery Box with random crypto!

በመዲናዋ የቤት እና የህንፃ ኪራይ እንጨምራል የሚሉ አከራዮች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ቢሮው አሳሰበ | ሰሌዳ | Seleda

በመዲናዋ የቤት እና የህንፃ ኪራይ እንጨምራል የሚሉ አከራዮች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ቢሮው አሳሰበ፡፡

በመዲናዋ በቅርቡ የጋራ መኖሪያ ቤት እና የህንፃ ባለንብረቶች የግብር ክፍያ መጀመሩን ተከትሎ አንዳንድ የህንፃ ባለቤቶች እና አከራዮች በተከራዮች ላይ ጭማሪ ለማድረግ ሙከራ እያደረጉ እንደሚገኙ መረጃው እንደደረሰው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ አስታውቋል። 

የከተማ ቦታና ቤት ግብር አከፋፈሉ የግልና የንግድ በሚል ልዩነት ቢኖረውም  የጋራ መኖሪያ ቤቶች ብቻ ሳይሆን በከተማ  ውስጥ ያሉ ከመኖሪያ እስከ  ህንጻዎች ድረስ ያሉ ቤቶችን በሙሉ የሚመለከት መሆኑንም ጠቅሷል።

የከተማ አስተዳደሩ ይህን ህግ ተግባራዊ ማድረግ የጀመረው በተጠና እና ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ማዕከል ባደረገ መልኩ መሆኑን የገለፀው ቢሮው የቤት ኪራይ እንጨምራል የሚሉ አከራዮች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማሳሰቡን መናኸሪያ ሬዲዮ ዘግቧል፡፡