Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 10ኛ ድሪም ላይነር አውሮፕላኑን መረከቡን አስታወቀ። አየር መንገዱ | ሰሌዳ | Seleda

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 10ኛ ድሪም ላይነር አውሮፕላኑን መረከቡን አስታወቀ።

አየር መንገዱ በድረ ገጹ እንዳመለከተው Boeing 787-9 ድሪም ላይነር አውሮፕላኑ ከቦይንግ ኩባንያ ተረክቦ የዛሬ 3 ቀን አዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሷል።

አዲሱ ድሪምላይነር አውሮፕላን የመጀመሪያ በረራውን ወደ ዱባይ ማድረጉንም አየር መንገዱ አሳውቋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት ክፍሉ ለቻይና ብድር በመያዣነት ሊተላለፍ ነው የሚል ትችት በስፋት ቀርቦበት የነበረ ሲሆን አየርመንገዱ ግን ውንጀላውን "የሐሰት ወሬ" ሲል አስተባብሏል።