Get Mystery Box with random crypto!

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ ያለው ሦስተኛው ከግል ባንክ ሆነ። | ሰሌዳ | Seleda

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ ያለው ሦስተኛው ከግል ባንክ ሆነ

የ2015 የመጀመርያ የሩብ ዓመት አፈጻጸሙን የሚያመለክተው ከኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ የተገኘው መረጃ ፣ በዘንድሮው ሩብ ዓመት የባንኩ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ የደረሰ ሲሆን፣ ለዚህም ባለፉት ሦስት ወራት ከስድስት ቢሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ መቻሉ አስተዋጽኦ አድርጓል። ይህም በሩብ ዓመቱ መጨረሻ ላይ ባንኩ የደረሰበት ጠቅላላ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን 102 ቢሊዮን ብር እንዲሆን አስችሏል።

ባንኩ እስከ ሰኔ 2014 ዓ.ም. ድረስ ጠቅላላ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑ 96.77 ቢሊዮን ብር እንደነበር የሚያመለክተው የባንኩ መረጃ፣ የተቀማጭ ገንዘብ በማሰባሰቡ ረገድ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ከቀዳሚዎቹ ሦስት የግል ባንኮች አንዱ እንዳደረገው አመልክቷል፡፡ ባንኩ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ የነበረው ጠቅላላ የሀብት መጠን 114.3 ቢሊዮን ብር ሲሆን፣ በሦስት ወራት  ውስጥ ከሰባት ቢሊዮን ብር በላይ በመጨመር የሀብት መጠኑን ወደ 121 ቢሊዮን ብር ማድረስ ችሏል፡፡

ከኢትዮዮጵያ ንግድ ባንክ ቀጥሎ በአገሪቱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አስቀማጭ ደንበኞች ያሉት የኦሮሚያ የኅብረት ሥራ ባንክ፣ በሩብ ዓመቱ መጨረሻ ላይ አጠቃላይ የቁጠባ ሒሳብ የከፈቱ ደንበኞች ብዛት 9.3 ሚሊዮን ደርሰዋል፡፡ ይህ አኃዝ ባንኩ ከግል ባንኮች ከፍተኛ ቁጥር ያለው አስቀማጮች በመያዝ በአንደኛነት ይዞት የቆየውን ደረጃ አስቀጥሏል። የባንኩ ጠቅላላ የብድር ክምችትም የመጀመርያው ሩብ ዓመት ላይ 86 ቢሊዮን ብር መድረሱ ታውቋል፡፡

via Reporter