Get Mystery Box with random crypto!

ሰሌዳ | Seleda

የቴሌግራም ቻናል አርማ seleda_business — ሰሌዳ | Seleda
የቴሌግራም ቻናል አርማ seleda_business — ሰሌዳ | Seleda
የሰርጥ አድራሻ: @seleda_business
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 80.41K
የሰርጥ መግለጫ

ጠንካራ በመረጃ የተደገፈ የቢዝነስ ውሳኔዎች!
ቢዝነስ እና ቴክ ተኮር መረጃዎች
ጨረታዎች እና ሃራጆች

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-10-13 09:57:37
ኤሎን መስክ "በርንት ሄር" ወይም "የተቃጠለ ፀጉር" ከተሰኘው አዲሱ ሽቶ ሽያጭ አንድ ሚሊዮን ዶላር ማግኘቱን አስታወቀ።

የዓለማችን ቁጥር አንዱ ባለጸጋ ኤሎን ማስክ "በርንት ሄር" የተሰኘውን ባለጥሩ መአዛ ሽቶ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ 10,000 ፍሬ ጠርሙሶች በመሸጥ አንድ ሚሊዮን ዶላር ማግኘቱን ተናግሯል። እንደ እኔ ያለ ዝነኛ ሰው ወደ ሽቶ ንግድ መግባት የማይቀር ነበር ያለው መስክ  ለምንድነው ይህን ያህል ጊዜ የለፋሁት ሲልም ጥያቄ አዘል ፅሁፉን በትዊተር ገጹ አስፍሯል።

via Reuters
3.5K views06:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-13 07:16:59
የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ ያለው ሦስተኛው ከግል ባንክ ሆነ

የ2015 የመጀመርያ የሩብ ዓመት አፈጻጸሙን የሚያመለክተው ከኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ የተገኘው መረጃ ፣ በዘንድሮው ሩብ ዓመት የባንኩ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ የደረሰ ሲሆን፣ ለዚህም ባለፉት ሦስት ወራት ከስድስት ቢሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ መቻሉ አስተዋጽኦ አድርጓል። ይህም በሩብ ዓመቱ መጨረሻ ላይ ባንኩ የደረሰበት ጠቅላላ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን 102 ቢሊዮን ብር እንዲሆን አስችሏል።

ባንኩ እስከ ሰኔ 2014 ዓ.ም. ድረስ ጠቅላላ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑ 96.77 ቢሊዮን ብር እንደነበር የሚያመለክተው የባንኩ መረጃ፣ የተቀማጭ ገንዘብ በማሰባሰቡ ረገድ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ከቀዳሚዎቹ ሦስት የግል ባንኮች አንዱ እንዳደረገው አመልክቷል፡፡ ባንኩ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ የነበረው ጠቅላላ የሀብት መጠን 114.3 ቢሊዮን ብር ሲሆን፣ በሦስት ወራት  ውስጥ ከሰባት ቢሊዮን ብር በላይ በመጨመር የሀብት መጠኑን ወደ 121 ቢሊዮን ብር ማድረስ ችሏል፡፡

ከኢትዮዮጵያ ንግድ ባንክ ቀጥሎ በአገሪቱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አስቀማጭ ደንበኞች ያሉት የኦሮሚያ የኅብረት ሥራ ባንክ፣ በሩብ ዓመቱ መጨረሻ ላይ አጠቃላይ የቁጠባ ሒሳብ የከፈቱ ደንበኞች ብዛት 9.3 ሚሊዮን ደርሰዋል፡፡ ይህ አኃዝ ባንኩ ከግል ባንኮች ከፍተኛ ቁጥር ያለው አስቀማጮች በመያዝ በአንደኛነት ይዞት የቆየውን ደረጃ አስቀጥሏል። የባንኩ ጠቅላላ የብድር ክምችትም የመጀመርያው ሩብ ዓመት ላይ 86 ቢሊዮን ብር መድረሱ ታውቋል፡፡

via Reporter
5.0K views04:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 20:16:39
አይኤምኤፍ የኢትዮጵያን የ2023 ምጣኔ ሀብት ትንበያ ወደ 5.3 በመቶ ዝቅ አደረገ።

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) እ.ኤ.አ. የ2023 የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት 5.7 በመቶ እንደሚያድግ ተንብዮ የነበረ ቢሆንም፣ ትላንት አዲስ ባወጣው የዓለም ምጣኔ ሀብት ዳሰሳ ሪፖርት ትንበያ በ0.4 ቀንሶ 5.3 በመቶ አድርጓል፡፡  

አይኤምኤፍ በአዲሱ ሪፖርቱ ለኢትዮጵያ ያስቀመጠው ትንበያ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አገሮች በ2023 ያድጋሉ ብሎ ካስቀመጠው ትንበያ ጋር እኩል ነው፡፡ በሚያዝያ ወር 2014 ዓ.ም. ላይ አስቀምጦት የነበረው ትንበያ ግን ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው አገሮች ካስቀመጠው 5.6 በመቶ ዕድገት የሚበልጥ ነበር፡፡

ትናንት የወጣው ሪፖርት የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት ዕድገት ትንበያው ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ተብለው ከተዘረዘሩት ሰባት አገሮች የኢኮኖሚ ዕድገት ትንበያ ጋር ሲነፃፀር፣ ሦስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ የሚችል ነው፡፡ ከታዳጊ አገሮች ከፍተኛውን ዕድገት እንደሚኖራት የተተነበየላት ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ኮንጎ ስትሆን፣ የተተነበየው ዕድገት 6.7 በመቶ ነው፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት የተጠናቀቀውን የ2014 በጀት ዓመት ሲጀምር፣ የአገሪቱ ምጣኔ ሀብት በ8.7 በመቶ ያድጋል የሚል ግምቱን አስቀምጦ የነበረ ቢሆንም፣ በበጀት ዓመቱ ማጠናቀቂያ ይኼ እንደማይሳካ አስታውቋል፡፡ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ግንቦት 30 ቀን 2014 ዓ.ም. የ2015 አጠቃላይ በጀትን ሲያቀርቡ፣ የ2014 በጀት ዓመት ዕድገት ከሰባት በመቶ የዘለለ እንደማይሆን ተናግረው ነበር፡፡

via - reporter
7.3K views17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 19:09:01
የቱርክ አስመጪዎች ብረትና ብረት ነክ ዕቃዎችን ለኢትዮጵያ ሊያቀርቡ ነው ተባለ።

የቱርክ ብረት አስመጪዎች ብረትና ብረት ነክ ዕቃዎችን ለኢትዮጵያ ለማቅረብ መስማማታቸውን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ገልጿል፡፡ አቅርቦቱ የሚከናወነው አሊጋስ፣ ኢዝሚርና እስክንድሪያ ከተሰኙ የቱርክ ወደቦች በመነሳት ብረትና ብረት ነክ ዕቃዎችን ከሚያቀርቡ ብረት አስመጭዎችና ወኪላቸው አርካስ ጋር የተደረሰ ስምምነት መሆኑ ታውቋል። 

ኢትዮጵያ በቂ የብረት ምርት ማቅረብ እስከምትችል ድረስ በቱርክ ሀገር ብረት ከሚያቀርቡ አስመጭዎች ፍላጎታችንን ያማከለ አቅርቦት እንዲኖር በማጓጓዝ ረገድ ምቹ ሁኔታ ይፈጠራልም ተብሏል። ኢትዮጵያ ወደ ቱርክ ወደቦች የራሷን መጫኛ መርከቦች በማሰማራት የአገልግሎት ተደራሽነቱን ለማሳደግ እየሰራች መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ድርጅቱ በመደበኛነት ወደ ቱርክ መጫኛ ወደቦች የራሱን መርከቦች እና ተጨማሪ ቻርተር መርከቦችን አሠማርቶ የአገልግሎት ተደራሽነቱን ለማሳደግ እየሠራ እነደሚገኝም ተጠቅሷል። የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በ2014 በጀት ዓመት 51 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ ከፍተኛ ገቢ ማስመዝገቡ ይታወሳል።

via - ENA
6.9K viewsedited  16:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 18:57:18
በተጠናቀቀው በጀት አመት ከቤቲንግ ድርጅቶች ከ180 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ።

በተጠናቀቀው የ2014 በጀት ዓመት ከስፖርት ዉርርድ (ቤቲንግ) ድርጅቶች 181 ሚሊዮን ብር ገቢ በኮሚሽን ማግኘቱን የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አስታዉቋል። አስተዳደሩ እድሜያቸው ከ 21 ዓመት በታች የሆኑ ወጣቶች በእጣ ጨዋታዉ ላይ እንዳይሳተፉ የቁጥጥር እና የክትትል ሥራ እንደሚሰራ አሳውቋል።

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ቴድሮስ ንዋይ ለብስራት ራዲዮ እንደተናገሩት፤ ከአራት አመት በፊት በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች ከአዋጭነት ጋር በተያያዘ ትርፋማ ባለመሆናቸዉ ከዘርፉ የወጡ ተቋማት የነበሩ ቢሆንም ከ 2011 ጀምሮ ግን በርካታ ተቋማት በህጋዊ የስፖርት ዉርርድ የእድል ጨዋታዎች በመላዉ ኢትዮጵያ ህጋዊ ፍቃድ አዉጥተዉ በሥራ ላይ መሆናቸዉን ገልጸዋል።
6.7K views15:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 14:11:17
በተንቀሳቃሽ ንብረት ዋስትና ለሚገኝ ብድር የኤሌክትሮኒክ የምዝገባ ሥርዓት መዘርጋቱ ተገለጸ።

የኤሌክትሮኒክ የምዝገባ ሥርዓቱ በዋናነት የፋይናንስ ዘርፉን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን የፋይናንስ ተቋማት ለሰጡት ብድር ዋስትና ብለው በያዙት ንብረት፣ ማንኛውም አካል ያለመዝጋቢው እውቅና ሊገበያይ ቢሞክር በራሱ ላይ ኪሳራ ያደርሳል ተብሏል። ምክንያቱም አስቀድሞ ለብድር ዋስትና የተመዘገበውን ንብረት ሌላ ሰው ቢገዛው፣ አበዳሪው ንብረቱን አድኖ የመውሰድ መብት ስላለው። ይህ የሚሆነው ግን ተንቀሳቃሽ ንብረቱ በዚህ ሥርዓት ከተመዘገበ ነው።

አበዳሪው የፋይናንስ ተቋም ንብረቱ ይያዝልኝ ብሎ ቢጠይቅ፣ ብሔራዊ ባንክ ተበዳሪው የወሰደውን ብድር መመለስ ባለመቻሉ ያስያዘው ንብረት እንዲያዝ ብሎ ለፖሊስ ደብዳቤ መፃፍ ይችላል። ይህም በአዋጅ የተቀመጠው ሕግ የሚለው ማንኛውም አበዳሪ ተንቀሳቃሽ ንብረት መያዣ አድርጎ ብድር ከሰጠ፣ ሕጉ በሦስተኛ ወግን ላይ ተፈጻሚ ይሆናል ስለሚል፣ በዚያ ንብረት ላይ እገዳ ተደርጓል።

ምዝገባ ካልተከናወነ ግን ሕጉ በሦስተኛ ወገን ላይ ተፈጻሚ እንደማይሆን ጠቁመው፣ የምዝገባ ሥርዓቱ ይህን ንብረት አስመዝግቤ ከዚህኛው አበዳሪ ይህን ያህል መጠን ገንዘብ ተበድሬያለሁ የሚለውና የተበዳሪው ማንነት የሚመዘገብበት ኤሌክትሮኒክ መዝገብ (collateral registration system) ነው ብለዋል።
7.7K views11:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 12:58:40
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በባህር ዳርና ሀዋሳ ሆቴሎችን ለመክፈት ዉል ፈረመ።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ “ፕሮቴያ ማሪዮት”ን በባህር ዳር ከተማ፣ በጣና ሀይቅ እና በሀዋሳ ሀይቅ ደግሞ “ፎር ፖይንት ባይ ሸራተን”ን ለመክፈት የሚያስችሉ 3 የፍራንቻይዝ ስምምነቶችን ከማሪዮት ኢንተርናሽናል ጋር ተፈራርሟል። 

ሁለቱ ኩባንያዎች ባህርዳር ብሉ ናይል (አቫንቲ) ሪዞርትን በፕሪቶሪያ ማሪዮት ብራንድ ለመክፈት ከስምምነት ላይ ሲደርሱ በባህር ዳር የሚገኘውን ጣና ሆቴል እና በሃዋሳ የሚገኘውን ፕሮግረስ ኢንተርናሽናልን በአራት ነጥብ በሸራተን ብራንድ ለመክፈት ተስማምተዋል።

የሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በቅርቡ በመቻሬ ሜዳ በ50 ቢሊየን ብር በ250 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ላይ ለሚያስገነባው ዘመናዊ የመሀመዲያ መንደር ለመመስረት የመሰረተ ድንጋይ ማስቀመጡ ይታወሳል፡፡
7.5K views09:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 12:15:00
አስር የኢትዮጵያ ስታርትአፖች በዱባይ ጂ አይ ቴክስ 2022 ለመጀመሪያ ጊዜ እየተሳተፉ ነው።

የምርምርና ኢኖቬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ የተመራ የመንግሥት እና ስታርትአፖች ቡድን በኤክስፖው እየተሳተፈ ሲሆን ቡድኑ በጃፓን ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት አስተባባሪነት ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 5 ቀን 2015 ዓ.ም ለሚቆየው የዱባይ ቴክኖሎጂና ስታርትአፕ ኤክስፖ ለመሳተፍ ነው ያቀናው።

በኤክክፖው ከ170 በላይ ሀገራት የመጡ ታላላቅ ዓለምአቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እና ስታርትአፖች እየተሳተፉ ሲሆን ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የግብርና፣ የአይ ሲ ቲ እና የዲጂታል፣ ቴክኖሎጂዎችን መሰረት ያደረጉ አስር ስታርትአፖችን በማሳተፍ ምርትና አገልጎሎታቸውን እንዲያስተዋውቁ እያደረገች ነው፡፡ በዚህም በተለየዩ ዓለም አቀፍ ውድድሮች እንዲሳተፉና ባለሃብቶች ጋር እንዲገናኙ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል መባሉን የኢንቬሽንና ቴክኖሊጅ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
7.8K views09:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 20:00:32
ኒሳን በሩሲያ የሚገኘዉን ንብረቱን ሊሸጥ መሆኑን አስታወቀ

የጃፓኑ የመኪና አምራች ኒሳን በሩሲያና ዩክሬን ጦርነት መነሻነት በሩሲያ ሴንት ፒተርስበርግ የሚገኘውን ፋብሪካ ጨምሮ ንብረቶቹን ለሩሲያ ፌዴሬሽን እንደሚሸጥ አስታዉቋል። በሽያጭ በስምምነቱ መሠረት ኒሳን በሚቀጥሉት ስድስት ዓመታት ውስጥ ፋብሪካውን እንደገና መግዛት ይችላል።

በዚህም ኩባንያው በሩሲያ ወደ 100 ቢሊዮን የን ኪሳራ እንደሚደርስበት አስታዉቋል፡፡ይሁን እንጂ በሩሲያ ውስጥ ከ2,000 በላይ ሰራተኞቹ ለ 12 ወራት ያህል "የሥራ ጥበቃ" እንደሚያገኙ ኒሳን አክሏል፡፡
9.5K views17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 17:41:59
አትሌት ሰለሞን ባረጋ ቃል የተገባለትን የመኪና ሽልማት ተረከበ።

በቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ በ10 ሺሕ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘው አትሌት ሰለሞን ባረጋ ቃል የተገባለትን መኪና ዛሬ ተረክቧል። ሽልማቱ በተለያየ ምክንያት ለሰለሞን እንዳልተሰጠው የሚታወስ ሲሆን በዛሬው ዕለት ግን ከመንግስት የመኪና ሽልማቱን ተረክቧል።

ሰለሞን ዛሬ የተረከበው ቶዮታ ላንድ ክሩዘር Twin Turbo V6 መኪና የዛሬ ሁለት አመት ቃል ከተገባለት ቶዮታ Rush ሞዴል መኪና ከ5 እጥፍ የሚበልጥ ዋጋ አለው (Rush ዱባይ ላይ 18,000 ዶላር ገደማ ሲሆን Twin Turbo 98,000 ዶላር ነው)። አትሌቱ ከሽልማቱ መኪና የተለየ ሞዴል ስለፈለገ ጭማሬውን ከፍሎ ከቀረጥ ነፃ በተሰጠው እድል ገዝቶ ንብረቱን ተረክቧል። ሆኖም የደቡብ ክልል ወልቂጤ ከተማ ላይ የሸለመው 10 ሺህ ካ.ሜ. መሬት እስካሁን እጁ እንዳልገባ ኤልያስ መሰረት አረጋግጧል።
9.9K viewsedited  14:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ