Get Mystery Box with random crypto!

የቱርክ አስመጪዎች ብረትና ብረት ነክ ዕቃዎችን ለኢትዮጵያ ሊያቀርቡ ነው ተባለ። የቱርክ ብረ | ሰሌዳ | Seleda

የቱርክ አስመጪዎች ብረትና ብረት ነክ ዕቃዎችን ለኢትዮጵያ ሊያቀርቡ ነው ተባለ።

የቱርክ ብረት አስመጪዎች ብረትና ብረት ነክ ዕቃዎችን ለኢትዮጵያ ለማቅረብ መስማማታቸውን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ገልጿል፡፡ አቅርቦቱ የሚከናወነው አሊጋስ፣ ኢዝሚርና እስክንድሪያ ከተሰኙ የቱርክ ወደቦች በመነሳት ብረትና ብረት ነክ ዕቃዎችን ከሚያቀርቡ ብረት አስመጭዎችና ወኪላቸው አርካስ ጋር የተደረሰ ስምምነት መሆኑ ታውቋል። 

ኢትዮጵያ በቂ የብረት ምርት ማቅረብ እስከምትችል ድረስ በቱርክ ሀገር ብረት ከሚያቀርቡ አስመጭዎች ፍላጎታችንን ያማከለ አቅርቦት እንዲኖር በማጓጓዝ ረገድ ምቹ ሁኔታ ይፈጠራልም ተብሏል። ኢትዮጵያ ወደ ቱርክ ወደቦች የራሷን መጫኛ መርከቦች በማሰማራት የአገልግሎት ተደራሽነቱን ለማሳደግ እየሰራች መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ድርጅቱ በመደበኛነት ወደ ቱርክ መጫኛ ወደቦች የራሱን መርከቦች እና ተጨማሪ ቻርተር መርከቦችን አሠማርቶ የአገልግሎት ተደራሽነቱን ለማሳደግ እየሠራ እነደሚገኝም ተጠቅሷል። የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በ2014 በጀት ዓመት 51 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ ከፍተኛ ገቢ ማስመዝገቡ ይታወሳል።

via - ENA