Get Mystery Box with random crypto!

በተጠናቀቀው በጀት አመት ከቤቲንግ ድርጅቶች ከ180 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ። በተጠና | ሰሌዳ | Seleda

በተጠናቀቀው በጀት አመት ከቤቲንግ ድርጅቶች ከ180 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ።

በተጠናቀቀው የ2014 በጀት ዓመት ከስፖርት ዉርርድ (ቤቲንግ) ድርጅቶች 181 ሚሊዮን ብር ገቢ በኮሚሽን ማግኘቱን የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አስታዉቋል። አስተዳደሩ እድሜያቸው ከ 21 ዓመት በታች የሆኑ ወጣቶች በእጣ ጨዋታዉ ላይ እንዳይሳተፉ የቁጥጥር እና የክትትል ሥራ እንደሚሰራ አሳውቋል።

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ቴድሮስ ንዋይ ለብስራት ራዲዮ እንደተናገሩት፤ ከአራት አመት በፊት በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች ከአዋጭነት ጋር በተያያዘ ትርፋማ ባለመሆናቸዉ ከዘርፉ የወጡ ተቋማት የነበሩ ቢሆንም ከ 2011 ጀምሮ ግን በርካታ ተቋማት በህጋዊ የስፖርት ዉርርድ የእድል ጨዋታዎች በመላዉ ኢትዮጵያ ህጋዊ ፍቃድ አዉጥተዉ በሥራ ላይ መሆናቸዉን ገልጸዋል።