Get Mystery Box with random crypto!

በተንቀሳቃሽ ንብረት ዋስትና ለሚገኝ ብድር የኤሌክትሮኒክ የምዝገባ ሥርዓት መዘርጋቱ ተገለጸ። የ | ሰሌዳ | Seleda

በተንቀሳቃሽ ንብረት ዋስትና ለሚገኝ ብድር የኤሌክትሮኒክ የምዝገባ ሥርዓት መዘርጋቱ ተገለጸ።

የኤሌክትሮኒክ የምዝገባ ሥርዓቱ በዋናነት የፋይናንስ ዘርፉን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን የፋይናንስ ተቋማት ለሰጡት ብድር ዋስትና ብለው በያዙት ንብረት፣ ማንኛውም አካል ያለመዝጋቢው እውቅና ሊገበያይ ቢሞክር በራሱ ላይ ኪሳራ ያደርሳል ተብሏል። ምክንያቱም አስቀድሞ ለብድር ዋስትና የተመዘገበውን ንብረት ሌላ ሰው ቢገዛው፣ አበዳሪው ንብረቱን አድኖ የመውሰድ መብት ስላለው። ይህ የሚሆነው ግን ተንቀሳቃሽ ንብረቱ በዚህ ሥርዓት ከተመዘገበ ነው።

አበዳሪው የፋይናንስ ተቋም ንብረቱ ይያዝልኝ ብሎ ቢጠይቅ፣ ብሔራዊ ባንክ ተበዳሪው የወሰደውን ብድር መመለስ ባለመቻሉ ያስያዘው ንብረት እንዲያዝ ብሎ ለፖሊስ ደብዳቤ መፃፍ ይችላል። ይህም በአዋጅ የተቀመጠው ሕግ የሚለው ማንኛውም አበዳሪ ተንቀሳቃሽ ንብረት መያዣ አድርጎ ብድር ከሰጠ፣ ሕጉ በሦስተኛ ወግን ላይ ተፈጻሚ ይሆናል ስለሚል፣ በዚያ ንብረት ላይ እገዳ ተደርጓል።

ምዝገባ ካልተከናወነ ግን ሕጉ በሦስተኛ ወገን ላይ ተፈጻሚ እንደማይሆን ጠቁመው፣ የምዝገባ ሥርዓቱ ይህን ንብረት አስመዝግቤ ከዚህኛው አበዳሪ ይህን ያህል መጠን ገንዘብ ተበድሬያለሁ የሚለውና የተበዳሪው ማንነት የሚመዘገብበት ኤሌክትሮኒክ መዝገብ (collateral registration system) ነው ብለዋል።