Get Mystery Box with random crypto!

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በባህር ዳርና ሀዋሳ ሆቴሎችን ለመክፈት ዉል ፈረመ። ሚድሮክ ኢንቨስ | ሰሌዳ | Seleda

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በባህር ዳርና ሀዋሳ ሆቴሎችን ለመክፈት ዉል ፈረመ።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ “ፕሮቴያ ማሪዮት”ን በባህር ዳር ከተማ፣ በጣና ሀይቅ እና በሀዋሳ ሀይቅ ደግሞ “ፎር ፖይንት ባይ ሸራተን”ን ለመክፈት የሚያስችሉ 3 የፍራንቻይዝ ስምምነቶችን ከማሪዮት ኢንተርናሽናል ጋር ተፈራርሟል። 

ሁለቱ ኩባንያዎች ባህርዳር ብሉ ናይል (አቫንቲ) ሪዞርትን በፕሪቶሪያ ማሪዮት ብራንድ ለመክፈት ከስምምነት ላይ ሲደርሱ በባህር ዳር የሚገኘውን ጣና ሆቴል እና በሃዋሳ የሚገኘውን ፕሮግረስ ኢንተርናሽናልን በአራት ነጥብ በሸራተን ብራንድ ለመክፈት ተስማምተዋል።

የሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በቅርቡ በመቻሬ ሜዳ በ50 ቢሊየን ብር በ250 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ላይ ለሚያስገነባው ዘመናዊ የመሀመዲያ መንደር ለመመስረት የመሰረተ ድንጋይ ማስቀመጡ ይታወሳል፡፡