Get Mystery Box with random crypto!

አስር የኢትዮጵያ ስታርትአፖች በዱባይ ጂ አይ ቴክስ 2022 ለመጀመሪያ ጊዜ እየተሳተፉ ነው። | ሰሌዳ | Seleda

አስር የኢትዮጵያ ስታርትአፖች በዱባይ ጂ አይ ቴክስ 2022 ለመጀመሪያ ጊዜ እየተሳተፉ ነው።

የምርምርና ኢኖቬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ የተመራ የመንግሥት እና ስታርትአፖች ቡድን በኤክስፖው እየተሳተፈ ሲሆን ቡድኑ በጃፓን ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት አስተባባሪነት ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 5 ቀን 2015 ዓ.ም ለሚቆየው የዱባይ ቴክኖሎጂና ስታርትአፕ ኤክስፖ ለመሳተፍ ነው ያቀናው።

በኤክክፖው ከ170 በላይ ሀገራት የመጡ ታላላቅ ዓለምአቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እና ስታርትአፖች እየተሳተፉ ሲሆን ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የግብርና፣ የአይ ሲ ቲ እና የዲጂታል፣ ቴክኖሎጂዎችን መሰረት ያደረጉ አስር ስታርትአፖችን በማሳተፍ ምርትና አገልጎሎታቸውን እንዲያስተዋውቁ እያደረገች ነው፡፡ በዚህም በተለየዩ ዓለም አቀፍ ውድድሮች እንዲሳተፉና ባለሃብቶች ጋር እንዲገናኙ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል መባሉን የኢንቬሽንና ቴክኖሊጅ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡