Get Mystery Box with random crypto!

አትሌት ሰለሞን ባረጋ ቃል የተገባለትን የመኪና ሽልማት ተረከበ። በቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ በ10 | ሰሌዳ | Seleda

አትሌት ሰለሞን ባረጋ ቃል የተገባለትን የመኪና ሽልማት ተረከበ።

በቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ በ10 ሺሕ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘው አትሌት ሰለሞን ባረጋ ቃል የተገባለትን መኪና ዛሬ ተረክቧል። ሽልማቱ በተለያየ ምክንያት ለሰለሞን እንዳልተሰጠው የሚታወስ ሲሆን በዛሬው ዕለት ግን ከመንግስት የመኪና ሽልማቱን ተረክቧል።

ሰለሞን ዛሬ የተረከበው ቶዮታ ላንድ ክሩዘር Twin Turbo V6 መኪና የዛሬ ሁለት አመት ቃል ከተገባለት ቶዮታ Rush ሞዴል መኪና ከ5 እጥፍ የሚበልጥ ዋጋ አለው (Rush ዱባይ ላይ 18,000 ዶላር ገደማ ሲሆን Twin Turbo 98,000 ዶላር ነው)። አትሌቱ ከሽልማቱ መኪና የተለየ ሞዴል ስለፈለገ ጭማሬውን ከፍሎ ከቀረጥ ነፃ በተሰጠው እድል ገዝቶ ንብረቱን ተረክቧል። ሆኖም የደቡብ ክልል ወልቂጤ ከተማ ላይ የሸለመው 10 ሺህ ካ.ሜ. መሬት እስካሁን እጁ እንዳልገባ ኤልያስ መሰረት አረጋግጧል።