Get Mystery Box with random crypto!

በፈረንጆቹ 2030 በከፍተኛ ሙቀት ምክንያት ከ2 ነጥብ 4 ትሪሊየን ዶላር በላይ ኪሳራ ይከሰታል ተ | ሰሌዳ | Seleda

በፈረንጆቹ 2030 በከፍተኛ ሙቀት ምክንያት ከ2 ነጥብ 4 ትሪሊየን ዶላር በላይ ኪሳራ ይከሰታል ተባለ።

ዓለማችን በፈረንጆቹ 2030 ከከፍተኛ ሙቀት መጨመር ጋር ተያይዞ ከ2 ነጥብ 4 ትሪሊየን ዶላር በላይ የኢኮኖሚያ ኪሳራ እንደሚያጋጥማት ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ እና የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽኅፈት ቤት (ኦቻ) ሰኞ ዕለት በጋራ ባወጡት ሰነድ ይፋ አድርገዋል፡፡

ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚኖሩባቸው ከተሞች ለሙቀት መጨመር የሚኖራቸው ተጋላጭነት ይበልጥ እንደሚጨምር ነው ሠነዱ በትንበያው ያመላከተው፡፡ እንደ ሠነዱ ትንበያ ከሆነ እስከ 2050ዎቹ ድረስ የእነዚሁ ከተሞች ነዋሪዎች ቁጥር በሰባት እጥፍ ይጨምራል፡፡

በሙቀት መጨመር እንዲሁም ከዓየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ በሚከሰቱ የካንሰር እና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች የሚከሰት ሞት በአሃዝ እንደሚጨምርና በተለይም ታዳጊ ሀገራት ይበልጥ የችግሩ ገፈት ቀማሽ እንደሚሆኑም ነው የተመላከተው። በዓየር ንብረት ለውጥ የሚከሰቱ የተፈጥሮ ሐብቶች መራቆት ፣ ሥደት እና የመሠረተ-ልማት ውድመቶችም ዓለማችን የምትጋፈጣቸው ችግሮች ናቸው ተብሏል፡፡